Quara Communication Affairs Office

Quara Communication Affairs Office ትክክለኛ መረጃን ለአገራችንና ለህዝባችን ተጠቃሚነት ስንል ተደራሽ እናደርጋለን!!
(1)

ቋራ ወረዳ በምግብ እራስን ለመቻል እየለማ ያለ የአኩሪ አተር ሰብል ያለበት ሁኔታ በከፊል!!       ቋራ:- ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም(ቋራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
10/08/2026

ቋራ ወረዳ በምግብ እራስን ለመቻል እየለማ ያለ የአኩሪ አተር ሰብል ያለበት ሁኔታ በከፊል!!

ቋራ:- ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም
(ቋራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

📌 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት የት ደረሰ? የኮሚሽኑ አሁናዊ መረጃ፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እየተጠናከረ እና ወደ ተሻለ ደረጃ እየተሸጋገረ መኾኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮ...
10/08/2026

📌 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት የት ደረሰ?

የኮሚሽኑ አሁናዊ መረጃ፦

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እየተጠናከረ እና ወደ ተሻለ ደረጃ እየተሸጋገረ መኾኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ስለ ሂደቱ አሁናዊ ሁኔታ እና በምክክሩ ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች፦

👉የምክክር ሂደቱ እና የ500ዎቹ ቡድን ሥራ፦

ከዚህ ቀደም በሁለት የ250 ቡድኖች የተነሱ ሀሳቦችን ለማጠናቀር ከእያንዳንዱ 15 አባላት የተወጣጡ 30 አጠናቃሪዎች ሃሳቦችን ሰንደው 500 አባላት ላሉት ቡድኖች ማቅረብ ጀምረዋል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም 3 እና 4 የሚኾኑ የአጀንዳ ቡድኖች በ500 አባላት ደረጃ ምክክራቸውን የጀመሩ መኾኑን እና ቀሪዎቹ እስከነገ ድረስ ሂደቱን እንደሚቀላቀሉ ገልጸዋል።

👉ስለ አለመግባባቶች እና ጭቅጭቆች የተሰጠ ማብራሪያ፦

በምክክሩ የመጀመሪያ ምዕራፎች ላይ አለመግባባቶች፣ ክርክሮች እና ስሜታዊነት መንጸባረቃቸው ተፈጥሯዊ እና በውይይት ሂደት ውስጥ የሚጠበቅ እንደኾነም ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ሂደቱ ከታች ከ10 ተመካካሪዎች ጀምሮ እያደገ የመጣ ሲኾን አሁን ላይ የግል እና የቡድን ሃሳቦችን በመተው ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረጉ የጋራ ሃሳቦች ወደ መሀል እየመጡ ይገኛሉ ብለዋል።

👉ውሳኔ ወይስ የምክር ሀሳብ?

እስካሁን ድረስ በአንድም አጀንዳ ላይ የተሰጠ ውሳኔ የለም፤ ወደፊትም አይኖርም ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ ውሳኔ የሚያሳልፍ ሳይኾን በሕግ አውጭው፣ ሕግ አሥፈጻሚው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሃይማኖት ተቋማት ተባብረው ሀገርን የሚደግፉ የምክር ሃሳቦችን እንዲያዘጋጁ ማገዝ መኾኑን አስገንዝበዋል። በድምጽ ብልጫ ውሳኔ ሊሰጥ ነው ወይም ከውጭ እና ከውስጥ ጫና ተደርጎ ሊወሰን ነው የሚሉ ወሬዎች ሙሉ በሙሉ አሉባልታ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

👉የሥነ-ምግባር ደንብ እና የቅሬታ አፈታት፦

ተሳታፊዎች ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሚኒስትሮች፣ አርሶአደሮች እና አርብቶ አደሮች የተካተቱበት የ120 እና 130 ሚሊዮን ሕዝብ ስሜት ይዘው የመጡ በመኾናቸው ኮሚሽኑ ሂደቱን በትዕግሥት እና በትህትና እየመራ ይገኛል ብለዋል። በምክክሩ ላይ ሀሳብን መደፍጠጥ፣ ማሳፈር ወይም ማንጓጠጥ በሥነምግባር ደንቡ በጥብቅ የተከለከለ እንደኾነም ጠቁመዋል።

የሚነሱ ቅሬታዎችን ለማስተናገድ ኮሚሽኑ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች ያሉበት አሠራር ዘርግቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ እየሰጠ ይገኛልም ብለዋል።

👉የቀጣይ ጊዜያት ተስፋ፦

የምክክር ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝ እና በተቀሩት 1እና 2 ሳምንታት ውስጥ ከ4ሺህ ተሳታፊዎች ጋር የሚደረገው የውይይት ምዕራፍ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል። በመጨረሻም የተሠበሠቡትን 4ሺህ ሃሳቦች አጠናቅሮ ለተግባሪ አካላት በማስረከብ ትግበራቸውን የመከታተል ሥራ እንደሚከናወንም ዋና ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ፕላን ኢንተርናሽናል በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዳው ለመተማ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ​ገንዳ ውኃ ፣ነሐሴ 04/2018 ዓ...
10/08/2026

ፕላን ኢንተርናሽናል በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዳው ለመተማ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

​ገንዳ ውኃ ፣ነሐሴ 04/2018 ዓ.ም ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት በምዕራብ ጎንደር ዞን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰበት ለመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል።

በድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፕላን ኢንተርናሽናል፣ የRRS እና UNHCR ተወካዮች፣ የምዕራብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያና የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የመተማ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ተወካዮች፣ የት/ቤቱ ርዕሰ-መምህር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ እርጥባን መስፈን ፕላን ኢንተርናሽናል ላደረገው ትብብርና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ባለፉት ግንቦትና ሰኔ ወራት በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጥሮ አደጋ መከሰቱን አስታውሰው፤ የዛሬው ድጋፍ በመተማ ዮሐንስ ለሚገኘው ትምህርት ቤት ትልቅ የግብዓት ማሟያ እንደሚሆን ገልጸዋል።

​ይህ ድጋፍ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለማቋቋም ከማስቻሉም በላይ በቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

አቶ እርጥባን አክለውም የትምህርትን ስብራት ለመጠገን መሰል ድጋፎች ወሳኝ በመሆናቸው፣ ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ተቋማትም ይህን በጎ ተግባር አብነት በማድረግ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

​የፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የመተማ ቅርንጫፍ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ትዕዛዙ ይዘንገው በበኩላቸው፤ ድርጅቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅና በግጭት ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሲረዳ መቆየቱን ገልጸዋል።

በመተማ ዮሐንስ ደርሶ የነበረውን የተፈጥሮ አደጋ አስመልክቶ የUN-OCHA የዳሰሳ ጥናት መሠረት በማድረግ፣ ለመጀመሪያ ደረጃ አስቸኳይ ምላሽ የሚሆን ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል።

በፕላን ኢንተርናሽናል አስተባባሪነት የቀረበው የትምህርት ቁሳቁስ የገንዘብ ድጋፍ የተገኘው ከUNHCR እና ከECHO-IHOPE ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

​እንደ አቶ ትዕዛዙ ገለጻ፤ ድጋፉ ድርጅቱ ለሰው ተኮር ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፣ በቀጣይም ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ብቁ እንዲሆኑ የሚደረገው እገዛ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ለትምህርት ቤቱ ከተደረጉት ድጋፎች መካከል የተማሪዎችና የመምህራን መቀመጫ ወንበሮች፣ ትልልቅ ጠረጴዛዎች፣ ደብተሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች የሚገኙበት ሲሆን፤ በሁለተኛው ዙርም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

​የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ እንዳለው ተፈራ፤ በከተማ አስተዳደሩ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ በማቋቋም ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተፈጥሮ አደጋው ምክንያት በርካታ ቁሳቁሶች የወደሙ በመሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግና የፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ እርዳታ የትምህርት ቤቱንና የተማሪዎችን ወቅታዊ ችግር የሚፈታ መሆኑን ተናግረዋል።

​በዞኑ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ቋራ ወረዳ ገለጉ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከግልና ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ውይይት አካሄደገለጉ:- ነሐሴ 4/2018 በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ገለጉ ቀበሌ በወቅታ...
10/08/2026

ቋራ ወረዳ ገለጉ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከግልና ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ውይይት አካሄደ

ገለጉ:- ነሐሴ 4/2018 በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ገለጉ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከግልና ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በወረዳው ያለውን ወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በመገምገም፣ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ በጋራ ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ነው።

በውይይቱ የቋራ ወረዳ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይላቅ ግድየለም እንደገለጹት፣ የአካባቢውን ሰላም በማስከበር የግልና የመንግስት ታጣቂዎች ሚና ከፍተኛ ነው። ታጣቂዎች አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ባለፈ ለሰላምና ፀጥታ አካላት አስፈላጊ መረጃዎችን በማቅረብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኢ/ር ወርቅየ ዋለልኝ እንደገለጹት፣ የጦር መሳሪያ የአካባቢያችንንና የሀገራችንን ደህንነት ለመጠበቅ መጠቀም የሚገባ መሆኑን በመገንዘብ፣ ታጣቂዎች ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በውይይቱም በአካባቢው ያለው የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ፣ ሰላምን በማጠናከር የታጣቂዎች ሚና፣ እንዲሁም በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገቡ የጋራ እርምጃዎች ዙሪያ ሰፊ ሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል።

በመጨረሻም፣ ሰላምና ፀጥታን ማስጠበቅ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ፣ በትብብር፣ በመተማመንና በጋራ ተግባር ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጿል።

ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላላ አሽከርካሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደገለጉ:- ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀ...
10/08/2026

ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላላ አሽከርካሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ

ገለጉ:- ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላላ አሽከርካሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ የቀጠናችንን ሰላም ለማስጠበቅ የአሽከርካሪዎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የወረዳውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ሰላምን ማፅናት አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አያና በውይይት መድረኩ ተገኝተው እንደገለጹት፣ በክልላችን በተከሰተው የፀጥታና ሰላም መደፍረስ ችግር ቀጥተኛ ተጎጂዎች ሹፌሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍና የአካባቢያችንን ህዝብ ሰላም ለማስጠበቅ ፅንፈኝነትን አምርሮ መታገል የወጣቶችና የአሽከርካሪዎች ሚና ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።

አቶ ደሳለኝ በመቀጠልም የወረዳው አሽከርካሪዎች ለሥራ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ስለሚንቀሳቀሱ፣ የአካባቢውን ሰላም ለማወክና ሰላምና ልማትን ለማደናቀፍ የሚመጣ ማንኛውንም አካል ለፀጥታ ኃይሉ ጥቆማ በመስጠት፣ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሰለፍ የታቀደውን የጥፋት ዕቅድ ማክሸፍ ይገባል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ለህዝብ ጥብቅና ቁመናል እያሉ እየተገዘቱ፣ ወረዳው ላይ ሰርገው በመግባት የህዝብንና የመንግሥትን ሀብትና ንብረት አወደሙ እንጂ ለህዝቡ የፈየዱለት አንድም ነገር የለም ብለዋል።

በመሆኑም በህዝባቸው ላይ ሊቃጣ የሚችልን በማንኛውም ዓይነት ጥቃት ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን ተሰልፈው፣ በሁሉም መስክ ተደራጅተው ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ኢንስፔክተር አለልኝ ተዘራ፣ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የማኔጅመንት አባል፣ የህዝባችንን ሰላም ለማናጋትና ልማትን ለማደናቀፍ ያለእረፍት እየሰራ ያለውን ፅንፈኛ ኃይል በመደራጀት ያቀደውን እኩይ ዓላማ በአጭር ማስቀረት ይገባል ብለዋል።

የአማራን ህዝብ ስቃይና መከራ ለመጨመር፣ ከአገር አፍራሹ ኃይል ከህወሃት ጋር ጋብቻ ፈፅመው ህዝቡን በጦርነት ለማንበርከክ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ሹፌሮች በአንድነት ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን ለሰላም ዘብ በመቆም መመከት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ በበኩላቸው፣ በህዝባዊነት ካባ ፅንፈኝነትን ያነገቡ፣ በዱር ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ክልላችንን፣ ዞናችንንና ወረዳችንን እየበጠበጡና እያሸበሩ እንዳሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ይህ ታጣቂ ኃይል ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመጣመር የጥፋት ተልዕኳቸውን ለመፈፀም በዝግጅት ላይ ስላሉ፣ በመላው የወረዳችን ህዝብ፣ ወጣቱና አሽከርካሪዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጎን በመሰለፍ ማክሸፍና መመከት ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም አሽከርካሪዎች በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለሰላምና ፀጥታ መጠበቅ የሚያበረክቱት ሚና፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሊያደርጉ የሚገባቸው ተግባራትና በወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘው ስፓርታዊ እንቅስቃሴ በዛሬው የእግር ኳስ ጨዋታ በአግሮ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀገለጉ፣ ነሃሴ 3/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱ...
09/08/2026

ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘው ስፓርታዊ እንቅስቃሴ በዛሬው የእግር ኳስ ጨዋታ በአግሮ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ገለጉ፣ ነሃሴ 3/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘውና በድምቀት እየተካሄደ የሚገኘው ስፓርታዊ እንቅስቃሴ በዛሬው አግሮ ባንክን ከፖሊስ ያገናኘው የእግር ኳስ ጨዋታ በአግሮ ባንክ 5 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ጨዋታው በመሃል ዳኛ ዳኔል የኔሰው እና በመስመር ዳኞች አድባየር ፀጋ እና መሳፍንት (ኢቦይ) በመመራት ተካሂዷል።

አግሮ ባንክ የድሉን ጎሎች በይሃለም አቤ ሁለት ጎል፣ በይታየው አብነት ሁለት ጎል እና በሀብታሙ አየናቸው አንድ ጎሎች በማስቆጠር ፖሊስን 5 ለ 0 በማሸነፍ የጨዋታውን ድል ተቀዳጅቷል።

ከሰዓት በተካሄደው አራት ቡድኖችን ያገናኘው የመረብ ኳስ ጨዋታ መከላከያን ከኢትዮ ቻይና፣ አግሮ ባንክን ከፖሊስ ያገናኘው ጨዋታ በመከላከያ እና በፖሊስ አሸናፊነት ተጠናቋል።

የጨዋታው ዓላማ የስፓርታዊ እንቅስቃሴው ዋና ዓላማ ማህበረሰቡን በስፖርት እንቅስቃሴ በማሳተፍ ጤናማ አካልና አእምሮ እንዲኖር ከማገዝ ባለፈ፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ወዳጅነትንና አንድነትን ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የቋራ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ ውቤ ጨዋታውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፣ ስፓርታዊ እንቅስቃሴው ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ማህበረሰቡ በንቃት እየተሳተፈበት መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ የስፖርት እንቅስቃሴው ወጣቶችን በአንድ መድረክ በማሰባሰብ ጤናማ የመዝናኛ አማራጭ ከመፍጠሩም በላይ በመካከላቸው ያለውን ወዳጅነትና አንድነት ለማጠናከር የላቀ ሚና እየተጫወተ ነው።

በቀጣይም የስፓርታዊ እንቅስቃሴውን በተሻለ መልኩ በማስቀጠል፣ ብዙ ወጣቶችና የማህበረሰብ ክፍሎች በስፖርቱ እንዲሳተፉ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላትና ከስፖርት ወዳዶች ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


ቋራ ወረዳ ገለጉ ከተማ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።ገለጉ:- ነሐሴ 3/2018 በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረ...
09/08/2026

ቋራ ወረዳ ገለጉ ከተማ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።

ገለጉ:- ነሐሴ 3/2018 በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ገለጉ ከተማ ቀበሌ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን በመረዳት፣ በአካባቢው የሚስተዋሉ የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን በጋራ በመለየት እንዲሁም ለዘላቂ ሰላም ሊወሰዱ ስለሚገቡ የጋራ እርምጃዎች ትኩረት ያደረገ ነበር።

በመድረኩ ተሳታፊዎች በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ እንዲጠበቅ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች የሚኖራቸውን ሚና በማጠናከር፣ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ በማድረስና አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ተጠይቋል።

በውይይቱ የተገኙት የምዕራብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አያና እንደተናገሩት፣ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሚና በመወጣት ለሰላም መስፈን መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ በበኩላቸው፣ የሰላም መረጋገጥ ለአካባቢው ልማትና ለህብረተሰቡ ዕለታዊ ኑሮ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ በአግባቡ በመጠቀም ለሰላም መጠናከር አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ተሳታፊዎቹም በአካባቢው የሚስተዋሉ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን በማካፈል፣ የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በቀጣይ ሊደረጉ በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ ጠቃሚ ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል።

!
/ቤት

ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘው ስፓርታዊ እንቅስቃሴ በመከላከያ አሸናፊነት ተጠናቀቀገለጉ፣ ነሃሴ 2/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘውና በድምቀት እየተካሄ...
08/08/2026

ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘው ስፓርታዊ እንቅስቃሴ በመከላከያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ገለጉ፣ ነሃሴ 2/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ 5ኛ ሳምንቱን የያዘውና በድምቀት እየተካሄደ የሚገኘው ስፓርታዊ እንቅስቃሴ፣ መከላከያን ከኢትዮ ቻይና ያገናኘው የእግር ኳስ ጨዋታ በመከላከያ 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ጨዋታው በመሃል ዳኛ አድባየር ፀጋ እና በመስመር ዳኞች ዳንኤል የኔሰው እና መሳፍንት (ኢቦይ) በመመራት ተካሂዷል።

መከላከያ የድሉን ጎሎች በሙሉጌታ ሲሳይ አንድ ጎል እና በኢሳያስ እያሱ ሁለት ጎሎች በማስቆጠር ኢትዮ ቻይናን 3 ለ 0 በማሸነፍ የጨዋታውን ድል ተቀዳጅቷል።

የስፓርታዊ እንቅስቃሴው ዋና ዓላማ ማህበረሰቡን በስፖርት እንቅስቃሴ በማሳተፍ ጤናማ አካልና አእምሮ እንዲኖር ከማገዝ ባለፈ፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ወዳጅነትንና አንድነትን ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የቋራ ወረዳ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ ውቤ ጨዋታውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፣ ስፓርታዊ እንቅስቃሴው ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ማህበረሰቡ በንቃት እየተሳተፈበት መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ የስፖርት እንቅስቃሴው ወጣቶችን በአንድ መድረክ በማሰባሰብ ጤናማ የመዝናኛ አማራጭ ከመፍጠሩም በላይ በመካከላቸው ያለውን ወዳጅነትና አንድነት ለማጠናከር የላቀ ሚና እየተጫወተ ነው።

በቀጣይም የስፓርታዊ እንቅስቃሴውን በተሻለ መልኩ በማስቀጠል፣ ብዙ ወጣቶችና የማህበረሰብ ክፍሎች በስፖርቱ እንዲሳተፉ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላትና ከስፖርት ወዳዶች ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


በቋራ ወረዳ ገለጉ ዙሪያ ቀበሌ ሙዝ በክላስተር እየለማ መሆኑ ተገለፀገለጉ:- ነሃሴ 2/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ገለጉ ዙሪያ ቀበሌ ሙዝ በክላስተር እየለማ እንደሚገኝ የ...
08/08/2026

በቋራ ወረዳ ገለጉ ዙሪያ ቀበሌ ሙዝ በክላስተር እየለማ መሆኑ ተገለፀ

ገለጉ:- ነሃሴ 2/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ገለጉ ዙሪያ ቀበሌ ሙዝ በክላስተር እየለማ እንደሚገኝ የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለፀ።

የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማስረሻ አስፋው እንደተናገሩት፣ በወረዳው ለሙዝ ልማት ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት ምርታማነቱንና የገበሬዎችን ገቢ ለማሳደግ የሙዝ ልማት በክላስተር እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አለበል መኳንት በበኩላቸው፣ የሙዝ ልማትን በክላስተር ማስፋፋት የአካባቢውን የግብርና ምርት ለማሳደግና አርሶ አደሩን ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለውን ሚና ጠቁመዋል።

በገለጉ ዙሪያ ቀበሌ በክላስተር የሚካሄደው የሙዝ ልማት በቀጣይ ጊዜ የምርት መጠንን በማሳደግ የአካባቢውን የገቢ ምንጭ ከማስፋፋት ባለፈ ለወረዳው የግብርና ልማት አጠቃላይ አቅም አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።


ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከወረዳው መንግሥት ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደገለጉ:- ነሃሴ 1/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላም...
07/08/2026

ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከወረዳው መንግሥት ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ

ገለጉ:- ነሃሴ 1/2018 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከወረዳው መንግሥት ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል። መድረኩ ወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታዎችን በመገምገም ቀጣይ የሚወሰዱ የጋራ እርምጃዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነበር።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቋራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው፣ ሰላምና ፀጥታ የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ፣ መንግሥት ሠራተኞች በሕግ ማስከበር፣ በሕዝብ ግንኙነት እና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ የተገኙት የምዕራብ ጎንደር ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርዳው ካሳሁን በበኩላቸው፣ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግሥት አካላትና ሕዝቡ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልጸው፣ የልማት ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የተረጋጋ የሰላም ሁኔታ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

እንዲሁም የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ ባደረጉት ገለጻ፣ የወረዳውን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሁሉም መንግሥት ሠራተኞች የሕዝብ አገልጋይነታቸውን በኃላፊነት በመወጣት ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም በተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የወረዳውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ ረገድ ሁሉም አካላት በጋራ በመተባበር እንዲሰሩ የጋራ ግንዛቤ ተወስዷል።

በውይይቱ የምዕራብ ጎንደር ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርዳው ካሳሁን፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አያና፣ የቋራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው፣ የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ እና ሌሎች የወረዳ አመራሮችና የተቋማት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

!!!

Address

Quara
Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Quara Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Quara Communication Affairs Office:

Shortcuts

Share