
20/07/2025
ሰላምን ለመገንባት ሃይማኖታዊ አስተምሮዋችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ክትትላችንን ማጠናከር ይኖርብናል - የቋራ ወረዳ የሃይማኖት አባቶች
ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኬሽን) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር የሰላም ኮንፈረስ ተካሄደ።
በውይይቱ የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው እንደተናገሩት ሰላምን ለመገንባት የሃይማኖት አባቶች ሃይማኖታዊ አስተምሮዋቸውን በማጠናከር ለሰላም ማጣት ምክንያት የሆኑ ወንድሞችን ወደ ሰላሙ እንዲመጡ ጥብቅ የሆነ ምክራቸውን መምከር መቻል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ሰላም ስለፈለግን ብቻ ማምጣት አንችልም ስላምን ለማምጣት የሀይማኖት አባቶ አይማኖታዊ አስተምሮትን በማጠናከር በዕምነቱ የተከለከሉ ተግባራትን አትግደል አትስረቅ የሚለውን ተግባራዊ እንዲሆን አጥብቀው ሲሰሩ፣ የሃገር ሽማግሌዎች ነፍጥ አንግበው ወደ ጫካ የወጡ ወንድሞችን መክረው ወደ ቤታቸው ሲመልሱ መሆኑን በመረዳት ለተግባሩ መሳካት ያላለሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል ብለዋል።
የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ በወረዳችን ሙሉ ሰላማዊ አካባቢን ለመገንባትና ማህበረሰባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም የሚገበበትን መንገድ ለመፍጠር የሀይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በሰላም ግንባታ ላይ እርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በሰላም ዕጦት ምክንያት ባሳለፍነው በጀት ዓመት በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይገቡ በማድረግ፣ በጤናው ዘርፍ ወላድ እናቶች በአግባቡ ወደ ህክምና ደርሰው እንዳይወልዱ በማድረግ ማህበረሰባችን በተለያዩ ችግሮች እንዲወድ ሆኗል ይህንን ለመከላከል የሀይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ኃላፊነት የተሞላበት ሰላም በአካባቢው እንዲፈጠር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የቋራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ሳጅን በሪሁን ጥላሁን የወረደችንን ሰላም ለማረጋገጥ የሃማኖች አባቶ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሰዎች ላይ ተግባራዊ በማድረግ የሃገር ሽማግሌዎች በየአከባቢው የወጡ ወንድሞች እንዲገቡ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በተለይ የከተማ ሮንድ ጥበቃን በተነለከተ የብሎክ አደረጃጀቱን ተግባራዊ በማድረግ በየአካባቢው የሚፈጠሩ ስርቆትን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳተፊ የሃይማኖት አባቶች ሰላምን ለመገንባት ሃይማኖታዊ አስተምሮዋችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ክትትላችንን ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።
በውይይቱ የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው፣ የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ፣ የቋራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ሳጅን በሪሁን ጥላሁን፣ የቋራ ወረዳ ፖሊስ ኢንስፔክተር ካሳው እና ሌሎች የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።