Quara communication affairs office

Quara communication affairs office ትክክለኛ መረጃን ለአገራችንና ለህዝባችን ተጠቃሚነት ስንል ተደራሽ እናደርጋለን!!

ሰላምን ለመገንባት ሃይማኖታዊ አስተምሮዋችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ክትትላችንን ማጠናከር ይኖርብናል - የቋራ ወረዳ የሃይማኖት አባቶች ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኬሽን...
20/07/2025

ሰላምን ለመገንባት ሃይማኖታዊ አስተምሮዋችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ክትትላችንን ማጠናከር ይኖርብናል - የቋራ ወረዳ የሃይማኖት አባቶች

ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 13/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኬሽን) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች ጋር የሰላም ኮንፈረስ ተካሄደ።

በውይይቱ የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው እንደተናገሩት ሰላምን ለመገንባት የሃይማኖት አባቶች ሃይማኖታዊ አስተምሮዋቸውን በማጠናከር ለሰላም ማጣት ምክንያት የሆኑ ወንድሞችን ወደ ሰላሙ እንዲመጡ ጥብቅ የሆነ ምክራቸውን መምከር መቻል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ሰላም ስለፈለግን ብቻ ማምጣት አንችልም ስላምን ለማምጣት የሀይማኖት አባቶ አይማኖታዊ አስተምሮትን በማጠናከር በዕምነቱ የተከለከሉ ተግባራትን አትግደል አትስረቅ የሚለውን ተግባራዊ እንዲሆን አጥብቀው ሲሰሩ፣ የሃገር ሽማግሌዎች ነፍጥ አንግበው ወደ ጫካ የወጡ ወንድሞችን መክረው ወደ ቤታቸው ሲመልሱ መሆኑን በመረዳት ለተግባሩ መሳካት ያላለሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል ብለዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ በወረዳችን ሙሉ ሰላማዊ አካባቢን ለመገንባትና ማህበረሰባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም የሚገበበትን መንገድ ለመፍጠር የሀይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በሰላም ግንባታ ላይ እርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በሰላም ዕጦት ምክንያት ባሳለፍነው በጀት ዓመት በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይገቡ በማድረግ፣ በጤናው ዘርፍ ወላድ እናቶች በአግባቡ ወደ ህክምና ደርሰው እንዳይወልዱ በማድረግ ማህበረሰባችን በተለያዩ ችግሮች እንዲወድ ሆኗል ይህንን ለመከላከል የሀይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ኃላፊነት የተሞላበት ሰላም በአካባቢው እንዲፈጠር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የቋራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ሳጅን በሪሁን ጥላሁን የወረደችንን ሰላም ለማረጋገጥ የሃማኖች አባቶ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሰዎች ላይ ተግባራዊ በማድረግ የሃገር ሽማግሌዎች በየአከባቢው የወጡ ወንድሞች እንዲገቡ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በተለይ የከተማ ሮንድ ጥበቃን በተነለከተ የብሎክ አደረጃጀቱን ተግባራዊ በማድረግ በየአካባቢው የሚፈጠሩ ስርቆትን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳተፊ የሃይማኖት አባቶች ሰላምን ለመገንባት ሃይማኖታዊ አስተምሮዋችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ክትትላችንን ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።

በውይይቱ የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው፣ የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ፣ የቋራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ሳጅን በሪሁን ጥላሁን፣ የቋራ ወረዳ ፖሊስ ኢንስፔክተር ካሳው እና ሌሎች የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

"ከግጭት አዙሪት ወጥተን ሰላምንና ልማትን የሚያስቀጥል ትውልድ የመፍጠር ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን"። የመተማ ዮሀንስ ከተማ ኗሪዎች********************መተማ ዮሐንሥ፣ሐምሌ12፣ 20...
19/07/2025

"ከግጭት አዙሪት ወጥተን ሰላምንና ልማትን የሚያስቀጥል ትውልድ የመፍጠር ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን"። የመተማ ዮሀንስ ከተማ ኗሪዎች

********************
መተማ ዮሐንሥ፣ሐምሌ12፣ 2017 (ምዕ/ጎን/ኮምዩኒኬሽን)፡የክልል ፣የዞንና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ከመተማ ዮኋንሥ ከተማ ኗሪዎች ጋር "ሠላም ለሁሉም ፤ሁሉም ለሠላም" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ አካሄዱ።

በውይይቱ ከወቅታዊ ሠላም ደህንነት፣ከልማት፣ከመልካም አሥተዳደር ከተማዋንና ቀጠናውን በተመለከቱ ጉዳዮች ሠፊ ውይይት ተደርጓል።

"እንደ ህዝብ በችግሮች ተተብትበናል ፣ወጥተን ገብተን አርሠን፣ነግደንና በጉልበታችን ሠርተን ማደር አላቻልንም በመሆኑም የህዝብን ደጀንነት ይዞ መንግሥት ህግ ሊያሥከብርልን ይገባል" ሢሉ ጠይቀዋል።

"ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ሊፈቱ ይገባል እንጅ በጦርነት የተፈታ ችግር በእኛም ይሁን የአለም ተሞክሮ አናውቅም" በማለት በአጽንኦት ኗሪዎቹ አሣሥበዋል።

በተጨማሪም የውይይቱ ተሣታፊዎች በከተማዋ እያጋጠመ ያለውን የውሃ፣የመብራት፣የኢንተርኔትአገልግሎት መቆራረጥ መንግሥት ሊፈታልን ይገባል በማለት ጠይቀዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአብክመ ባህል ቱሪዝም ም/ቢሮ ሃላፊ አየለ አናውጤ(ዶ/ር) እንደህዝብ ከችግሮቻችን በቂ ትምህርት ወሥደናል፤ሠላምን ለማምጣትና ለመጠበቅ ጊዜው አሁንና የሁላችንም ጥረት ነው ብለዋል።

የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አቶ እያሡ ይላቅ በበኩላቸው የከተማው ህዝብ ለሠላም እየከፈለው ያለውን ዋጋ እውቅና ሠጠው የህዝባችን መከራና ሥቃይ የምናሥቆመው ህዝብና መንግሥት ተሠናሥኖ ሲሠራ ነው። ለዚህም በጠመንጃ የሚመለሥ የህዝብ ችግር እሥከሌለ ድርሥ የታጠቁ ሃይሎች ሠላምን መርጠው ለከተማው ሠላምና ልማት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የምዕ/ጎን/ዞን/ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳለው ማሩ በበኩላቸው አሁን በክልላችንና ከተማችን ላይ ሠላም እንዳይሠፍን እንዳናለማ እያደረገ ያለው የታጠቀ ሃይል የራሱን የጠበበ ቡድናዊ ፍላጎት ለማሣካት የሚታተር እንጅ ምንም አይነት እርባና ያለው ህዝብ ጥያቄዎች የሌለው መሆኑን አውሥተው ሠላም እንዲመጣ፣በሙሉ አቅማችን እንድናለማ ደህንነታችን እንዲጠበቅ የከተማው ህዝብ የበኩሉን እንዲወጣ አሣሥበዋል።

የከተማው ከንቲቫ አቶ ሃብቴ አዲሡ በበኩላቸው ከተሣታፊዎች ለተነሡ የመልካም አሥተዳደር፣የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት ጥያቄዎች እንደ ከተማ አሥተዳደር ብዙ የመልማት ጥያቄን እየፈቱ መሆኑን ጠቅሠው ከመብራት አገልግሎት አኳያ ችግሮችን ለማቃለል እየሠሩ መሆኑን ገልጸው ከውሃና የኢንተርኔት አኳያም ችግሩ እንዲሥተካከል ከሚመለከታቸው ጋር እየሠሩ መሆኑን አሥረድተዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ የሀገር ሽማግሌ ሲራጅ ሙሃመድና ወ/ሮ ሃና ጥላሁን፥በበኩላቸው ማኅበረሰቡ ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት አካባቢያችን መጠበቅ ቀዳሚው ተግባራችን ነው ብለዋል።

ከጸብ ይልቅ ሰላምን፣ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርና አንድነትን ተላብሶ ልማትን የሚያስቀጥል ትውልድ የመፍጠር ታሪካዊ ሃላፊነት አለብን ብለዋል።

በመድረኩ የክልል፣የዞን ከፍተኛ አሥተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣የመምሪያ ሃላፊዎችና የከተማ አሥተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም

📷 West Gondar zone Communication/ምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን

  ‼   በቋራ ወረዳ ለ27 ዓመታት የቋራ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ጽ/ቤት ባለሙያ በመሆን በመንግስት ሰራተኛነት የወረዳውን ማህበረሰብ ሲያገለግሉ የነበሩ ታላቅና አንጋፋ ባለሙያ ሲሆኑ  ...
19/07/2025



በቋራ ወረዳ ለ27 ዓመታት የቋራ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ጽ/ቤት ባለሙያ
በመሆን በመንግስት ሰራተኛነት የወረዳውን ማህበረሰብ ሲያገለግሉ የነበሩ ታላቅና አንጋፋ ባለሙያ ሲሆኑ ባደረባቸው ፅኑ ህመም ህክምናቸውን ለመከታተል ወደ ባህርዳር እንዳቀኑ በዛሬው ዕለት ማለትም ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ቆላድባ ላይ ተፈፅሟል።

ለቤተሰቦቹ፣ ለስራ ባለደረቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ተመኝተናል።
የቋራ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የአኩሪ አተር ዘር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማስረሻ አስፋው በእርሻ ልማቱ ተገኝተው የድገፍና ክትትል ስራ መስራታቸው ...
19/07/2025

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የአኩሪ አተር ዘር ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማስረሻ አስፋው በእርሻ ልማቱ ተገኝተው የድገፍና ክትትል ስራ መስራታቸው ተገልፃዋል።

ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም
ቋራ ኮሙኒኬሽን

ለረጅም ጊዜ በውሃ እጦት ችግር የቆየው የቋራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአልማ እና በአይ ኤም ኤስ(IMC) የተቀናጀ ድጋፍ በዛሬው ዕለት የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑ ተገለፀ።ቋራ/ገለጉ:...
18/07/2025

ለረጅም ጊዜ በውሃ እጦት ችግር የቆየው የቋራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአልማ እና በአይ ኤም ኤስ(IMC) የተቀናጀ ድጋፍ በዛሬው ዕለት የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑ ተገለፀ።

ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኬሽን) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ለረጅም ጊዜ በውሃ እጦት ችግር የቆየው የቋራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአልማ እና በአይ ኤም ኤስ(IMC) የተቀናጀ ድጋፍ በዛሬው ዕለት የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆኑ ተገለፀ።

ሆስፒታሉ የውሃ አገልግሎት ችግሩ ተፈቶ ወደ ተግባር መገባቱን የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው፣ የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ፣ የቋራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ደሴ እና የሆስፒተሉ ተወካይ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ተገኝተው አረጋግጠዋል።

የውሃ ጉድጓዱ የውሃ ንጽህናው እንዲጠበቅና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲኖረው በማሣብ በሞለድ ተገንብቶ የወጣ ሲሆን ለሆስፒታሉ ከ200 ሜትር ርቀት በላይ በመሆኑ ተጨማሪ አክሠሠሪዎች እንደሚያስፈልገውና ሠርፊስ ፓምፕ፣ ጀኔሪተሮችና ሌሎች ከመጠየቁ የተነሣ ከ300,000 ሺ ብር በላይ ወጪ መደረጉን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ተናግረዋል

የቋራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በወረዳው በርካታ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ እያደረግ የሚገኝ መሆኑን የገለፁት የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው የውሃ አገልግሎት ሳያገኝ በመቅረቱ በስራ ሁኔታው ላይ ከባድ ተፅኖ ፈጥሮ የቆየ ቢሆንም ዛሬ ላይ የሆስፒታሉን የውሃ ችግር ሙሉ በሙሉ መፍታት የተቻለበትን ሂደት መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።

ለሆስፒታሉ የውሃ ችግር መፈታት ድጋፍ ላደረጉ አልማ/የአማራ ልማት ማህበርንና አይመሲ(IMC) ድርጅቶች ታላቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ በበኩላቸው በሆስፒታሉ የውሃ ችግር መፈታት ታላቅ ደስታቸውን ገልፀው ሆስፒታሉ የህዝባችንን የጤንነት ችግር እየፈታ ያለ ተቋም በመሆኑ እንደ ተቋም ከሚያስፈልጉት ነገሮች መካከል አንዱ ውሃን ዛሬ ላይ ችግሩ መፈታቱን በቦተው ተገኝተው ማረጋገጥ መቻላቸውን አንስተዋል።

የቋራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ደሴ የቋራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እንደ ወረዳ በጤናው ዘርፍ በርከታ ተግባራትን እየፈፀመ የሚገኝ ተቋም መሆኑን አንስተው ሆስፒታሉን ለበርካታ ጊዚያት ችግር ሆኖበት የቆየውን የውሃ ችግር በአልማና በአይኤም ሲ በዚህ ልክ በመፈታቱ ታላቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

እንደ አቶ አብነት ደሴ ገለፃ ሆስፒታሉ ዛሬ ላይ የውሃ ችግሩን በዚህ መልኩ መፍታት ብንችልም አሁንም ሌሎች ለሆስፒታሉ የሚያስፈልጉ ከባለሙያ እስከ ልዩ ድክተሮ ድረስ እንዲሁም ሌሎች ማቴሪያሎችን የሚመለከተው አካል ችግሮችን ከስር ከስር እያየ እንዲፈታና ለህዝባችን ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ማረጋገጥ የምንችልበትን ሁኔታ መፍጠር መቻል እንዳለበት አሳስበዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቀድ አገልግሎት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ።ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኮሽን) በጎ ፈቃድ ሲባል...
18/07/2025

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቀድ አገልግሎት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ።

ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኮሽን) በጎ ፈቃድ ሲባል ከስሙ እንደምንረዳው የማንንም ግፊት የማይሻ በባለቤቱ ውስጣዊ ተነሳሽነት የሚፈፀም ትውልድ ከሚቀረፅባቸው አወንታዊ አመለካከቶች ከሚዳብርባቸው በርካታ መንገዶች ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጉልህ ስፍራ እንደሚይዝ ይታወቃል።

" በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል የቋራ ወረዳ አረንጓዴ ዘብ የደን አስተዳደር ተብሎ በተሰየመው ግሪን ኤሪያ የቦታ ስፋት 3500 ካሬ ሜትር ስፋት ካለው ቦታ ላይ 750 ችግኝ የተተከለ ሲሆን በተከላ ፕሮግራሙ ሚም፣ ማንጎ፣ ኩመር እና ግራር ችግኞች የተከሉ መሆናቸውን የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አለበል መኳንት ገልፃዋል።

የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደተናገሩት ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞችን መፅደቅና አለመፅደቃቸውን የድጋፍ ክትትል ስራ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አሁን ላይ በጎነታችንን በችግኝ ተከላ ፕሮግራም እንደጀመርነው ሁሉ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት መቻል ይኖርብናል ብለዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ በጎነት ለሃገራችን ህዝቦች አንድነትን፣ መተዛዘንና መረዳዳትን የምናጎላበት መሆኑን ገልፀው ዛሬ ላይ በጎነታችንን በችግኝ ተከላ ተግባር ያሳየንበት መሆኑን አንስተዋል።

በወረዳችን በበጎ ፈቃድ የምናከናውናቸው በርካታ ተግባራት እንዳሉ የገለፁት አቶ አንዳርጋቸው ማሬ ዛሬ ላይ በችግኝ ተከላ እንደጀመርነው ሁሉ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ማለትም በጉልበት፣ በገንዘብና በሌሎች የበጎ ፈቃድ ተግባራት በንቃት መሳተፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ዛሬ ላይ የበጎ ፈቃድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለተካሄደበት 3500 ካሬ ሜትር ቦታ የገለጉ ከተማ መሪ መዘጋጃ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልፃዋል

ፌዝ ኢን አክሽን ከቋራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ገለጉ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ስለ ኮሌራ/አተት በሽታ መነሻ መንስኤ፣ መተላለፊያና መከላከያ መንገዶችን በተደራጁ የቴክኒክ ኮሚቴዎች...
17/07/2025

ፌዝ ኢን አክሽን ከቋራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ገለጉ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ስለ ኮሌራ/አተት በሽታ መነሻ መንስኤ፣ መተላለፊያና መከላከያ መንገዶችን በተደራጁ የቴክኒክ ኮሚቴዎች አማካኝነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራቱ ተገለፀ።

ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኬሽን)

ሰላምን ለመገንባት ለሚሰሩ ስራዎች የሃይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ  መሆኑ ተገለፀ።በምዕራብ ጎንደር ዞን በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ዙሪያ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል። ሰላምን ለመገ...
16/07/2025

ሰላምን ለመገንባት ለሚሰሩ ስራዎች የሃይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ዙሪያ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

ሰላምን ለመገንባት ለሚሰሩ ስራዎች የሃይማኖት አባቶች ከመንግስት ጋር በመሆንና ሰላምን ለማስፈን የሚያደርጉትን ጥረት በማጠናከር የተጀመረው ሀገራዊ የሰላም ግንባታ እንዲቀጥል የበኩላቸውን እንዲሚወጡ ገልፀዋል።

በውይይቱ የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ፣ የክልሉ ባህል ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አየለ አናውጤ(ደ/ር)፣ አቶ አባይነህ ጌጡ የአብክመ የህዳሴ ግድብ ማሥተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ፣ በብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎንደር ዞን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለው ማሩና ሌሎች የዞን አሥተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ አባ ኃ/ማሪያም ያሳይን ጨምሮ ሌሎች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱም ለዞናችን ሠላም መረጋገጥ የሃይማኖት አባቶች ከመንግሥት ጋር ሁነው እንደሚሠሩ ተግባቦት ላይ ተደርሧል።

09/11/2017ዓም
የምዕ/ጎን/ኮሙንኬሽን መምሪያ
ገንዳ-ውሃ

የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ ለቋራ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ኤስ ኤ ኤስ ሲ ኦ(SASCO) በተባለ ድርጅት አማካኝነት 5.1 ሚሊየን ብር ፈጅተው የመጡ ሎት 3 የፈርኒቸር ማሰልጠኛ መሳሪዎችን...
16/07/2025

የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ ለቋራ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ኤስ ኤ ኤስ ሲ ኦ(SASCO) በተባለ ድርጅት አማካኝነት 5.1 ሚሊየን ብር ፈጅተው የመጡ ሎት 3 የፈርኒቸር ማሰልጠኛ መሳሪዎችን የወረዳው ኮር አመራሮች ማቴሪያሎችን ጉብኝት አደረጉ።

የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ ለቋራ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ኤስ ኤ ኤስ ሲ ኦ(SASCO) በተባለ ድርጅት አማካኝነት 5.1 ሚሊየን ብር ፈጅተው የመጡ ልዩ ልዩ 29 አይነት ሎት 3 የፈርኒቸር ማሰልጠኛ መሳሪዎችን የወረዳው ኮር አመራሮች ኮሌጁ ድረስ በመገኘት ማቴሪያሎችን ጉብኝት አደርገዋል።

የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው ቴክኒክና ሙያ ኮሌጁ በፅንፈኛው አማካኝነት በርካታ የኮሌጁ ማቴሪያሎች የወደሙ ቢሆንም የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ በSASCO ድርጅት አማካኝነት ከውጭ ድረስ ማቴሪየሎችን በማስመጣ ለኮሌጁ እርክክብ በማድረጉ ታላቅ ምስጋናቸውን አቅርበው ኮሌጁ ስራ በሚጀምርበት ወቅት ማቴሪያሎችን በአግባቡ በመጠቀም በሙያው የበቁ ተማሪዎችን ማፍራት ላይ እርብርብ ማድረግ መቻል እንዳለበት ገልፃዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ የመጡት ማቴሪያሎች በኮሌጁ ስር የሚሰለጥኑ ተማሪዎችን በፈርኒቸር ሙያ ብቁ የሚያደርግ ማቴሪያል በመሆኑ አሰልጣኝ ባለሙያዎች ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት ሙያዊ ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በጉብኝቱ የቋራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አስማረ አንዳርጋቸው፣ የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ማሬ፣ የኮሌጁ ተወካይ ኃላፊ አቶ ቸሩ አምባቸው እና የወረዳው ስራና ስልጠና ኃላፊ አቶ ሞላ እንዲሁም ሌሎች የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

የማቴሪያሎች አይነት
1.መሠንጠቂያ ማሽን 2.ጠርዝ መምቻ ማሽን 3.መቁረጫ ማሽን 4.ሁለትናከሁለት በላይ ስራዎችን የሚሠራ መላጊና መሠንጠቂያ ማሽን 5.ጌጣጊጥ ማውጫ 6.አራት ማዕዘን መቦርቦሪያ 7.የቁም መሠንጠቂያ 8.ምላስ ማውጫ 9.መሞጃ ማሽን 10.ቅርፅ ማውጫ ማሽን 11.የጠረጴዛ መሞረጃ ማሽን 12.ተንቀሳቃሽ የእጅ መሞረጃ
13.ተንቀሳቃሽ ጌጣጌጥ ማውጫ 14.የእንጨት እርጥበት መለኪያ ማሽን 15.የእጅ ማሸጊያ ማሽን 16.የፕላስቲክ መዶሻ 17.የብረት መዶሻ 18.የቁልፍ መብሻ 19.መሠንጠቄያ መጋዝ 20.ጠፍጣፋ መሮ
21.ሹል መሮ 22.መቀስ 23.ጠፍጣፋ ሞረድ 24.የጠረጴዛ ቅርፃቅርፅ ማውጫ 25.ምላጭ መበየጃ ማሽን 26.ማለስለሻ ማሽን 27.የቁም መብሻ ማሽን 28.የአቧራ ማስወጃ ማሽን 29.የእንጨት ስቴፕለር መምቻ ናቸው።

የቋራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የግብር ዘመን ሃምሌና ግብሩ በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው የደረጃ "ሐ" የግብር ንቅናቄ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ።ቋራ/ገለጉ:-...
16/07/2025

የቋራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የግብር ዘመን ሃምሌና ግብሩ በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው የደረጃ "ሐ" የግብር ንቅናቄ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ።

ቋራ/ገለጉ:- ሐምሌ 9/2017 ዓ.ም (ቋራ ኮሙኒኬሽን) አዲሱ በጀት አመት የሚጀምርበት ወርሃ ሃምሌ ለገቢ ተቋሙ ልዩ ትኩረት በመስጠት ግብር የሚሰበሰብበት ወቅት ሲሆን የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮችን ልዩ ንቅናቄ በመፍጠር አመታዊ ግብራቸዉን የሚከፍሉበት ጊዜ ነዉ።

ሃምሌና ግብሩ በሚል መሪ ቃል ከሐምሌ 01/2017 እስከ 08/11/2017 ዓ.ም ድረስ ከንግድ ግብርና ከአከራይ ተከራይ 4 ሚሊየን 126 ሺህ 141.36 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 5 ሚሊየን 49 ሺህ 914 .12 ብር ገቢ የዕቅዱን 110.36% መሰብሰቡ መቻሉን የቋራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግሰዉ በቀለ ገልፀዋል።

ኃላፊዉ አያይዘው እንደገለጹት በተለይ የዘንድሮዉ ሐምሌና ግብሩን ለየት የሚያደርገዉ የክልሉ መንግስት ባስለማዉ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ አስተዳደር ስርአት በመዘርጋቱ ተቋሙ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥና ገቢዉን በትክክል መሰብሰብ እንዲችል ግብር ከፋዮች ጊዜያቸዉን ጉልበታቸዉን እንዲቆጥቡ አድርጓል ብለዋል።

አቶ ደገሰዉ በመቀጠል በወረደችን ተፈጥሮ በነበረዉ የፀጥታ ችግር የ2015 እና የ2016 ዓ.ም የአከራይ ተከራይ ግብር ዘገይቶ በመከፈሉና ቀበሌዎች ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ማድረግ አለመቻሉን አንስተዉ በቀጣይ ግብሩን ሙሉ ለሙሉ በማስከፈል ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የተቋሙ ሰራተኞች ኃላፊነታቸዉን በብቃት መወጣት መቻል እንዳለባቸው ገልፃዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በተያዘው የመኸር እርሻ እስከአሁን በተደረገ የዘር እንቅስቃሴ ከ400 ሺህ 698 ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።በዞኑ በተያዘው የመ...
16/07/2025

በምዕራብ ጎንደር ዞን በተያዘው የመኸር እርሻ እስከአሁን በተደረገ የዘር እንቅስቃሴ ከ400 ሺህ 698 ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በዞኑ በተያዘው የመኸር እርሻ እስከአሁን በተደረገ የዘር እንቅስቃሴ ከ400 ሺህ 698 ሄክታር በላይ መሬት በባለሃበትና በአርሶ አደሮች በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ እንደገለፁት፤በዞኑ የኤክስፖርት እና የኢንዱስትሪ ግብዓትን ጨምሮ የምግብ ነክ ሰብሎችም በስፋት እየለሙ ነው።

በዚህም በተያዘው መኸር ምርት ዘመን 529 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል አይነቶች ለማልማት ታቅዶ እየተስራ ሲሆን እስከ አሁንም 400 ሺህ 600 በላይ ሄክታር መሬት የእቅዱን 79% በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ከነዚህም ውስጥ ሰሊጥ፣ጥጥ፣ማሽላ፣አኩሪ አተር፣በቆሎ፣ማሾና ሌሎች ሰብሎች በስፋት እየለሙ ሥለመኾናቸው ተናግረዋል።

በዞኑ የግብርና የልማት ሥራዎች በሁሉም መስክ ተጠናክረው
መቀጠላቸውን የጠቁሞቱ ኃላፊው፣የተለያዩ የሰብል ልማት ስራው ተጠናክሮ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አርሶአዱሩና አልሚ ባለኃባቱ በቴክኖሎጅና በባለሙያ በመታገዝ ሰብሉን በየጊዜው በመንከባከብና በማሰስ ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር ከወዲሁ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በዞኑ ገንዳ ውሃ ከተማም ከ4 ሺህ 447 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እስካአሁን 3ሺህ 218 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የከተማ አስተዳደሩ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ስዩም አየለ ተናግረዋል።

በከተማው እየለማ ካለው ሰብል የተሻለ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸው የታቀደውን ምርት ለማግኘት በየደረጃ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስተያየታቸውን የሰጡ የመተማ፣ የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳና ገንዳ ውሃ ባለኃብቶች እና አርሶ አደሮች በበኩላቸው ሰሊጥ አኩሪተርና ሌሎች ለውጭ ገቢያ የሚቀርቡ የቅባት እህሎችን በማምረት ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

የገንዳ ውሃ ከተማ ዙሪያ ነዋሪ አርሶ አደር ሰለምን ባየ፤በሰጡት አስትያየት ሰሊጥና አኩሪ አተርን በግብርና ባለሙያዎች በመታገዝ እያለሙ ነው።

ባለፈው ዓመት የዝናብ መጠን በመቀነሱ ምርት ቀንሶባቸው እንደነበር አስታውሰው፣በዘንድሮው የመኸር እርሻ ከባለፈው ዓመት የተሻለ ምርት ለማግኘት በትጋት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመኸር አዝመራው በ10 ሄክታር መሬት ላይ ሰሊጥና በ7 ሄክታር በቆሎ እያለሙ መሆኑን ጠቁመው፤ ከሄክታር 25 እስከ 30 ኩንታል ምርት እንደሚያገኙ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በዞኑ ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በኮርደም የእርሻ ልማት ቀጠና የኢንቨስተመንት ልማት ሰራ አስኪያጅ አቶ አለሙ ሙለው በበኩላቸው በተለይ የኤክስቦርት፣የኢንዱስትሪ ግባትና ሌሎች ምግብ ነክ ሰብሎች በስፋት ለማምረት አቀደው ከ1ሺህ 80 ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈናቸውን ተናግረዋል።

በምርት ዘመኑም ካለፈው አመት የተሻለ ገቢና ምርት ለማግኛት የመኸር እርሻቸውን የዘመናዊ የእርሻ መካናይዝን በመጠቀም እያከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የመተማ ወረዳ አርሶ አደር ሲሳይ እንየው በበኩላቸው ሰሊጥ፣አኩሪ አተር እና በቆሎ ማምረት ከጀመሩ 10 ዓመታት እንደሆናቸው ገልጸው ሌሎች ገበያ ተኮር ምርቶችን እያመረቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ሐምሌ 9/2017
📷 West Gondar Communication/ምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን

በምዕራብ ጎንደር ዞን 5.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎ የተገነባው ተንጠልጣይ ድልድይ አገልግሎት መጀመሩ ተገለፀ።በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የገንዳ-ዉሃ ወንዝ ተንጠልጣይ ድልድይ...
15/07/2025

በምዕራብ ጎንደር ዞን 5.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎ የተገነባው ተንጠልጣይ ድልድይ አገልግሎት መጀመሩ ተገለፀ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የገንዳ-ዉሃ ወንዝ ተንጠልጣይ ድልድይ ተገንብቶ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን የምዕ/ ጎንደር ዞን መንገድ መምሪያ ኃላፊ አቶ አባይነህ ወረታ ገልፀዋል ። እንደመምሪያ ሃላፊው ገለጻ
ድልድዩ ሠዎችን፣ እንሠሣትንና ሞተር ብሥክሌቶችን ማሻገር እንደሚችልና ለ50 አመት አገልግሎት ታሣቢ ተደርጎ መሠራቱን አሥረድተዋል።

በጉብኝት ፕሮግራሙ የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ እያሡ ይላቅ፣የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ም/ቢሮ ሃላፊ አየለ አናውጤ(ዶ/ር)፣በአብክመ የህዳሤ ግድብ ማሥተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አባይነህ ጌጡ፣የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳለው ማሩን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ አሥተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣የመምሪያ ሃላፊዎችና የገንዳውሃ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

08/11/2017ዓ.ም
የምዕ/ጎን/ኮምዩኒኬሽን መምሪያ
ገንዳ-ውሃ

Address

Gonder

Telephone

+251918318183

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Quara communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Quara communication affairs office:

Share