
18/07/2025
በዳንሻ ከተማ አስተዳደር የተቋማት ዳሰሳ ግብረ መልስ እና የ90 ቀን እቅድ የውይይት መድረክ ተካሂዷል
ዳንሻ:- ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም)በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ስቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ ከተማ አስተዳደር የተቋማት የሱፐርቪዥን ግብረ መልስ እና የ90 ቀን እቅድ የውይይት መድረክ ተካሄደ ።
በመድረኩ የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልዋሀብ ማሞ፣የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ማሩ፣የወረዳው ሰራ አስፈፃሚዎች ፣የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል ።
በዳንሻ ከተማ አስተዳደር የስቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት የሪፎርምና ክትትል ቡድን መሪ በአቶ መከተ ፈንታ፣በዋና ኮምሽነር መ/ር አላቸው ብርሀኑና በአቶ ሁሴን አህመድ በተቋማት የተደረገው ዳሰሳ ለተሳተፊዎች በጥንካሬና በድክመት የተገኘው ውጤት ገለፃ አድርገዋል ።
በነበረው ዳሰሳ ከንቲባ ጽ/ቤት፣የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት እንዲሁም መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤቶች ከ1-3 ደረጃ ይዘዋል ።
በተቋማት ከታዩ ክፍተቶች የበጀት አለመኖርና የቁሳቁስ እጥረት፣የሰራተኞች አለመሟላት፣ልዩ ልዩ ሙያዊ ስልጠናዎችና የተሞክሮ ልውውጥ አለመኖር ፣መርህ በመከተል ስራን ቆጥሮ ከመስራት ውሱንነት መኖር ፤ኃላፊነት አለመወጣትና ትኩረት አድርጎ አለመስራት፣የእቅድና ሪፖርት መዛነፍ በተወሰኑ ተቋማት በክፍተት ታይቷል።
አቶ ሀብታሙ ማሩ በውይይት መድረኩ ተቋማት ያላቸው ጠንካራ ጎን በማጠናከርና ክፍቶችን በማስተካከል፤የአመራርና የሙያተኛ አቅም በማሳደግ ተረባርበን የተሻለ ተቋም መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣የልማትና የፀጥታ ስራዎች፣የመልካም አስተዳደር እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመፈፀም የሚያስችል የ3 ወር እቅድ በዳንሻ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ሀብታሙ ማሩ ለአለመራሮች አቅርበዋል ።