Rising Ethio

Rising Ethio ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም

 #ፓለቲካን      ➡️  ሰከንድ      ➡️   ደቂቃ      ➡️   ቀን      ➡️   ልክንህን።          መቀየር አለብህ ያለብዚያ ይቆሽሻል።everyone Rising Ethio
16/07/2025

#ፓለቲካን
➡️ ሰከንድ
➡️ ደቂቃ
➡️ ቀን
➡️ ልክንህን።

መቀየር አለብህ ያለብዚያ ይቆሽሻል።
everyone Rising Ethio

30/06/2025
30/05/2025

ልናውቋቸው የሚገቡ 17 የእስያ ሀገራት አባባሎች

1. #ቻይና: "ዛፍ ለመትከል ምርጡ ጊዜ ከ20 ዓመት በፊት ነበር። ሁለተኛው ምርጥ ጊዜ ግን አሁን ነው።"
(ማብራሪያ: አንድን ነገር ለማድረግ ጊዜው አሁን መሆኑንና መዘግየት እንደሌለበት ያሳያል።)

2. #ጃፓን: "ሰባት ጊዜ ውደቅ፣ በስምንተኛው ተነስ።"
(ማብራሪያ: በችግር ውስጥ መጽናትንና ተስፋ አለመቁረጥን ያበረታታል።)

3. #ህንድ: "ዛፍ ስለሚረግፉ አበቦች አይጨነቅም።"
(ማብራሪያ: ከቁጥጥር ውጪ በሆኑ ነገሮች ላይ አለመጨነቅንና ነገሮችን መተው/መልቀቅን ያስተምራል።)

4. #ኮሪያ: "ዝንጀሮም እንኳ ከዛፍ ላይ ይወድቃል።"
(ማብራሪያ: ማንም ሰው ፍጹም እንዳልሆነና ስህተት ሊሰራ እንደሚችል ያመለክታል።)

5. #ቬትናም: "ወንድሞችና እህቶች እንደ እጅና እግር ቅርብ ናቸው።"
(ማብራሪያ: የቤተሰብን የጠበቀ ትስስርና ቅርበት ያጎላል።)

6 #ታይላንድ: "የዱላን አንዱን ጫፍ ስታነሳ፣ ሌላኛውንም ጫፍ አብረህ ታነሳለህ።"
(ማብራሪያ: ማንኛውም ድርጊት የራሱ የሆነ መዘዝ ወይም ውጤት እንዳለው ያስረዳል።)

7. #ፋርስ (ፐርሺያ): "በተሳሳተ ጊዜ ከሚሰጥ ወርቅ፣ በተገቢው ጊዜ የተወረወረ ድንጋይ ይሻላል።"
(ማብራሪያ: የጊዜን አስፈላጊነትና ትክክለኛ ወቅት ላይ የሚደረግ ነገር ዋጋ እንዳለው ያሳያል።)

8. #ፊሊፒንስ: "ከየት እንደመጣ ወደ ኋላ የማያይ፣ መድረሻው ላይ መቼም አይደርስም።"
(ማብራሪያ: ምስጋናን፣ ትህትናንና ያለፉበትን መንገድ ማስታወስ ያለውን ዋጋ ያሳያል።)

9. #ቻይና: "ወደፊት ያለውን መንገድ ለማወቅ፣ ወደ ኋላ የሚመለሱትን ጠይቅ።"
(ማብራሪያ: ከሌሎች ሰዎች ልምድ መማር ጠቃሚ መሆኑን ያሳስባል።)

10. #ጃፓን: "አንድ ፍላጻ በቀላሉ ይሰበራል፣ በአንድ ላይ የታሰሩ አስር ፍላጻዎች ግን አይሰበሩም።"
(ማብራሪያ: የአንድነትን ኃይልና አስፈላጊነት ያሳያል።)

11. #ህንድ: "ትምህርት ባለቤቱን በሄደበት ሁሉ የሚከተል ውድ ሀብት ነው።"
(ማብራሪያ: ለትምህርትና ለእውቀት ዋጋ መስጠትና ዘላቂነታቸውን ያሳያል።)

12. #ኮሪያ: "የነብር ዝንጉርጉርነቱ ውጪ ነው፣ የሰው (ባህሪው) ግን ውስጡ ነው።"
(ማብራሪያ: የአንድን ሰው እውነተኛ ማንነት የሚወስነው ውስጣዊ ባህሪው እንጂ ውጫዊ ገጽታው እንዳልሆነ ይናገራል።)

13. #ቬትናም: "ፍሬ ስትበላ፣ ዛፉን የተከለውን ሰው አስታውስ።"
(ማብራሪያ: ለቀደሙት ሰዎች ጥረትና ላገኘነው በረከት ምስጋና ማቅረብን ያስተምራል።)

14. #ታይላንድ: "ጥላህ እንዲመራህ አትፍቀድ።"
(ማብራሪያ: ፍርሃት ወይም ያለፈው ህይወትህ የአሁኑን ውሳኔህንና አካሄድህን እንዲቆጣጠረው አትፍቀድ።)

15. #ሞንጎሊያ: "የመጀመሪያው ብርጭቆ ለእንግዳ ነው፣ ሁለተኛው ለመደሰቻ፣ ሶስተኛው ለትርምስ።"
(ማብራሪያ: በሁሉም ነገር ልክንና መጠንን ማወቅ ቁልፍ መሆኑን ያሳያል፤ ከልክ ማለፍ ወደ ችግር ይመራል።)

16. #ቲቤት: "መቶ የወንድና መቶ የሴት (የተለያዩ) ባህሪያቶች ፍጹም ሰውን ይፈጥራሉ።"
(ማብራሪያ: ሚዛናዊነትና የተለያዩ በጎ ባህሪያትን በአንድ ላይ መያዝ ወደ ፍጹምነት እንደሚያደርስ ያሳያል።)

17. #ቻይና: "የሺህ ማይል መንገድ በአንድ እርምጃ ይጀምራል።"
(ማብራሪያ: ማንኛውም ትልቅ ነገር የሚጀምረው በትንሽ እርምጃ መሆኑንና መጀመር በራሱ ቁልፍ መሆኑን ያሳያል።)

everyone

29/05/2025

The 1960s will remember
The 1970s will remember
The 1980s will remember
The 1990s will remember
The 2000s will remember
The 2010s will remember
The 2020s will remember

The Football history always remember

🚨𝗢𝗙𝗙𝗜𝗖𝗜𝗔𝗟: በ 𝟮𝟬𝟮𝟰/𝟮𝟱 𝗧𝗼𝗽 𝟲 𝗣𝗿𝗲𝗺𝗶𝗲𝗿 𝗟𝗲𝗮𝗴𝘂𝗲 𝗖𝗹𝘂𝗯𝘀 (𝗜𝗻𝗰𝗹𝘂𝗱𝗶𝗻𝗴 𝗨𝗘𝗙𝗔) ያገኙት ገቢ ክለባችን አርሰናል በአንደኝነት ተቀምጧል 1. Arsenal – ከሊጉ £177...
27/05/2025

🚨𝗢𝗙𝗙𝗜𝗖𝗜𝗔𝗟: በ 𝟮𝟬𝟮𝟰/𝟮𝟱 𝗧𝗼𝗽 𝟲 𝗣𝗿𝗲𝗺𝗶𝗲𝗿 𝗟𝗲𝗮𝗴𝘂𝗲 𝗖𝗹𝘂𝗯𝘀 (𝗜𝗻𝗰𝗹𝘂𝗱𝗶𝗻𝗴 𝗨𝗘𝗙𝗔) ያገኙት ገቢ ክለባችን አርሰናል በአንደኝነት ተቀምጧል

1. Arsenal – ከሊጉ £177M + ከቻምፒዮንስ ሊጉ £101M = አጠቃላይ £278M

2. Liverpool – ከሊጉ £181M + ከቻምፒዮንስ ሊጉ £96M = አጠቃላይ £277M

3. Man City – £171M + £63M = £234M

4. Chelsea – £169M + £19M = £188M

5. Man Utd – £139M + £36M = £175M

6. Tottenham – £130M + £39M = £169M

Rain Across the Solar System 🌧️Rain across the solar system comes in many forms – some familiar, others truly bizarre.Ta...
27/05/2025

Rain Across the Solar System 🌧️

Rain across the solar system comes in many forms – some familiar, others truly bizarre.

Take Venus, for example. Its thick atmosphere is laden with clouds of sulfuric acid, a highly corrosive compound. If it were to rain on Venus, it wouldn’t be the life-sustaining water we’re used to. Instead, it would be sulfuric acid rain, a deadly downpour that evaporates before reaching the surface due to Venus’ extreme surface temperatures. Despite the harsh conditions, these acid clouds continue to swirl, perpetuating the cycle of vaporizing rain.

On Earth, the rain we rely on is made of water, essential for sustaining life. The Earth’s water cycle, driven by solar heat, allows rain to fall, nourish the land, and return to the atmosphere, forming clouds again. This constant cycle sustains ecosystems and keeps the planet habitable for countless species.

Farther out, the rain gets even stranger. On Jupiter, extreme pressure deep within its atmosphere causes helium to condense into liquid, resulting in helium rain falling through the dense clouds. Even more incredible, at certain depths, carbon-based compounds may experience so much pressure that they crystallize into diamonds, essentially creating a rain of gems. It’s a surreal phenomenon that adds to Jupiter’s chaotic storm systems.

In the outer solar system, Saturn, Uranus, and Neptune also experience diamond rain. The immense pressure in their atmospheres forces carbon atoms to bond together, forming diamond crystals that then fall down through the gas layers. These gas giants, with their icy compositions and extreme conditions, create a surreal, almost alien precipitation that’s unlike anything we could imagine on Earth.

27/05/2025

እውነትን በግልጥ የማይናገር ሰው ሁከትን ይፈጥራል፣
በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል፡፡
የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፣
የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው፡፡
ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፣
ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ዐይታ በይቅርታ ታልፋለች፡፡ …
እውነትን በምትናገርበት ጊዜ ቅን ፍርድ ታደር

ከሰጠሽኝ ስጭኝ ባሰጭኝ ይቀራልእቃሽ ወራሽ የለው አብሮሽ ይቀበራል
27/05/2025

ከሰጠሽኝ ስጭኝ ባሰጭኝ ይቀራል
እቃሽ ወራሽ የለው አብሮሽ ይቀበራል

ማንኛውም የዘውግ ፖለቲከኛ ተግቶ እያጠፋን ያለው የእርሱን  ሪፑብሊክ መመስረት አማራ ነው የሚደናቅፈን ብሎ ስለሚሰጋ ነው፡፡ ከአያያዛቸው እንደምናየው ከሃምሳ አመት በፊት ጀምሮ ይዘፍኑ የነበ...
25/07/2024

ማንኛውም የዘውግ ፖለቲከኛ ተግቶ እያጠፋን ያለው የእርሱን ሪፑብሊክ መመስረት አማራ ነው የሚደናቅፈን ብሎ ስለሚሰጋ ነው፡፡ ከአያያዛቸው እንደምናየው ከሃምሳ አመት በፊት ጀምሮ ይዘፍኑ የነበረውን ዘፈን አልቀየሩም፡፡
የድርጅታቸውም ማንፌስቶ ፤ክልላዊ መዝሙረሰቸው፣አላማቸው አልተቀየረም፡፡
ይህ ማለት ደግሞ በአማራ መቃብር ላይ የሚመኟትን ሪፑብሊክ ትገነባለች የሚለው የጥፋት አላማ እስከነነፍሱ አለ ማለት ነው፡፡
ጠቅላላ የአየሩ ሽታም አደገኝነት አለው፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰአት እየተባባሰ መምጣቱም ለመጨረሻው ጥፋት እያዘጋጁን ይመስላል፡፡

➡️

Link to my blog and to learning money things

25/07/2024

ማንኛውም የዘውግ ፖለቲከኛ ተግቶ እያጠፋን ያለው የእርሱን ሪፑብሊክ መመስረት አማራ ነው የሚደናቅፈን ብሎ ስለሚሰጋ ነው፡፡ ከአያያዛቸው እንደምናየው ከሃምሳ አመት በፊት ጀምሮ ይዘፍኑ የነበረውን ዘፈን አልቀየሩም፡፡
የድርጅታቸውም ማንፌስቶ ፤ክልላዊ መዝሙረሰቸው፣አላማቸው አልተቀየረም፡፡
ይህ ማለት ደግሞ በአማራ መቃብር ላይ የሚመኟትን ሪፑብሊክ ትገነባለች የሚለው የጥፋት አላማ እስከነነፍሱ አለ ማለት ነው፡፡
ጠቅላላ የአየሩ ሽታም አደገኝነት አለው፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰአት እየተባባሰ መምጣቱም ለመጨረሻው ጥፋት እያዘጋጁን ይመስላል፡፡

21/07/2024

,ነው፡፡
አሁን ባለቺው ኢትዮጵያ ‹ይቻላል› እንጂ ‹ይገባል› ተገቢውን ቦታ አላገኘም፡፡
የሚገባውን መሥራት ግን የሕግና የሞራል ጉዳይ ነው፡፡ ኃይልን ለመጠቀም የሚያስችል ትምህርት ለሚማሩ ሰዎች በጥብቅ የሚነገራቸው ነገር ቢኖር የተገቢነት ጉዳይ ነው፡፡ ካራቴ፣ ጂዶ፣ ቦክስ፣ ውትድርና፣ ፖሊስነት የተማሩ ሰዎች ኃይልን ለመጠቀም ቅርብ ናቸው፡፡ በእጃቸው ማጠናፈር፣ በእግራቸው መዘረር፣ በጉልበታቸው ማርገፍ፣ በመሣሪያቸው ማንጠፍ፣ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በባረቀባቸው፣ በፈላባቸውና በነደዳቸው ቁጥር ኃይል እንዳይጠቀሙ የተገቢነትን ጉዳይ እንዲያስቡበት ይመከራሉ፤ ይሠለጥናሉ፡፡ ይቻላል ሳይሆን ይገባል ወይ? ብለው እንዲጠይቁ፡፡
አሁን ባለቺው ኢትዮጵያ ‹ይቻላል› እንጂ ‹ይገባል› ተገቢውን ቦታ አላገኘም፡፡ ሁሉም የሚችለውን ለማድረግ ነው የተነሣው፡፡ ‹ይህንን ማድረግኮ ይቻላል፤ እነ እንትናን መቀስቀስኮ ይቻላል፤ እንዲህ አድርገን ልናሳያቸውኮ እንችላለን፤ እንዲህ ብሎ መከራከርኮ ይቻላል፤ እንዲህ አድርጎ ምላሽ መስጠት ይቻላል፤ እንዲህ ሠርቶ መበሻሸቅ ይቻላል› የሚሉ ነገሮችን ነው የምንሰማው፡፡ ባለ ሥልጣኑም፣ ፖለቲከኛውም፣ አክቲቪስቱም፣ ጸሐፊውም፣ ጋዜጠኛውም ምን ማድረግ እንደሚችል እየነገረን ነው፡፡ ሁሉም የጉልበቱን ልክ እያሳየን ነው፡፡ ‹ይህንን ማድረግ ተገቢ ነው?› ብሎ የሚጠይቅ ግን ብዙም የለም፡፡

ሁላችንም የምንችለውን ብቻ ካደረግን የሚተርፍ አይኖርም፡፡ የሚያኗኑረን ተገቢውን ብቻ ለማድረግ ያለን የአእምሮ መለኪያ ነው፡፡ ኃይልንና ጉልበትን ከማን አለብኝነት የማቀቢያው መንገድ ‹ተገቢነት› ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከሕግና ከሞራል አንፃር የሚታይ ነው፡፡ ለጊዜው ዐቅም ወይም ሥልጣን ወይም ዕድል የላቸውም ብለን በምናስባቸው ወገኖች ላይ ‹እንችላለን› በሚል ስሜት ብቻ የምናከናውነው ተግባር ሌላ ‹እችላለሁ ባይ› ይፈጥራል፡፡ የማሸነፊያው ኃይል ሐሳብ መሆኑ ይቀርና ጉልበት ይሆናል፡፡ ጉልበት ማጠራቀም ደግሞ ሐሳብን ከማጠራቀም ይልቅ ቀላል ነው፡፡ ሂደታችንም ያረጀን ጉልበታም በአፍለኛ ጉልበታም የመተካት ሂደት ይሆናል፡፡ የሰው ልጅ ዛሬ ዛሬ ዛፎችን የማይቆርጠው፣ እንስሳትን የማያድነው፣ በካይ ጋዝ ወደ አየር የማይለቀው ዐቅም አንሶት አይደለም፡፡ ይህን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡ ግን አይገባውም፡፡
ማኅበረሰብን በሰላምና በጤና የሚያኑዋኑረው ‹ተገቢነት› ነው፡፡ ይህን ነገር መናገር፣ መጻፍ፣ ማሠር፣ መግደል፣ መከልከል፣ መውሰድ፣ መስጠት፣ ተገቢ ነው ወይ? የሚያስገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ያኗኑራል ወይ? በዜጎች ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ምንድን ነው? የሚሉት ጉዳዮች መታየት አለባቸው፡፡ ማድረግ የምችለውን ሁሉ ማድረግ፣ መናገር የምንችለውን ሁሉ መናገር፣ መጻፍ የምንችለውን ሁሉ መጻፍ፣ ማባረር የምንለውን ሁሉ ማባረር፣ ማፍረስ የምንችለውን ሁሉ ማፍረስ፣ መገንባት የምንችለውን ሁሉ መገንባት አለብን? ተገቢ ነው?
የሰው ልጅ አካላት በሦስት መልክ ይገለጣሉ፡፡ በአንድ በኩል ለሕዝብ ሁሉ የሚገለጡ የአካል ክፍሎች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚገለጡ የአካል ክፍሎች አሉ፡፡ ሦስተኛዎቹ ደግሞ ለማንም የማይገለጡ የአካል ክፍሎች ናቸው፡፡ በፎቶ ግራፎቻችን ላይ በብዛት የምናገኛቸው ለሕዝብ ሁሉ የሚገለጡትን የአካል ክፍሎቻችንን ነው፡፡ እነዚህ የአካል ክፍሎች ብዙ ጊዜ ልብስ አይለብሱም፡፡ ቢለብሱም በአደባባይ ልብሳቸው ሊወልቅ የሚችል ነው፡፡ ለቅርብ ሰዎቻችን ብቻ የምናሳያቸው የአካል ክፍሎችም አሉን፡፡ እነዚህ ብዙ ጊዜ በልብስ ተሸፍነው የሚውሉ ናቸው፡፡ እነዚህን ለሰው ሁሉ መግለጥ የጤናም፣ የሞራልም፣ የባሕልም፣ የሥነ ምግባርም ቀውስ ያመጣል፡፡ ሦስተኛዎቹ በቆዳችን ተሸፍነው የሚኖሩ የሰውነት ክፍሎች ናቸው፡፡ እነዚህን ለማየት የውስጥ አካልን የሚያሳዩ መሣሪያዎች ያስፈልጋሉ፡፡ በቀዶ ጥገና ለማየትም የተለየ ሞያና ሥነ ምግባር ይጠይቃሉ፡፡ እነዚህ በቆዳ ተሸፍነው የሚኖሩ የሰውነት ክፍሎቻችንን ከፍተን ብንተዋቸው በሰውዬው ላይ አደጋ ይከሠታል፡፡ መጨረሻውም ሞት ነው፡፡
የሰው ልጅ ጉዳዮችም እንዲሁ ናቸው፡፡ ለሁሉም የሚገለጡ አሉ፡፡ ለተመረጡ ብቻ የሚገለጡ አሉ፡፡ ለማንም የማይገለጡም አሉ፡፡ አሁን በሀገራችን እያየን ያለነው ግን ከዚህ በተለየ ነው፡፡ ሁሉንም በአደባባይ የመዘርገፍ አባዜ ውስጥ ወድቀናል፡፡ ይህንን የምናደርገው ደግሞ ‹ማድረግ እንችላለን› በሚል ጉልበተኛ ስሜት ነው፡፡ ‹ማድረግ ተገቢ ነውን?› በሚል የጠቢብነት መንፈስ አይደለም፡፡ ከሕዝብ ሁሉ ጋር የምናደርጋቸው ነገሮች አሉ፤ ከተመረጡ ወገኖች ጋር መነጋገር፣ መከራከር መወያት ያለብን ነገሮችም አሉ፡፡ አንዳንድ ነገሮች ግን ስሜታችንን ቢገፋፉትም፣ ውስጣችንን በል በል ቢለንም፣ ጉልበታችን ቢሞግተንም፣ እንኳን ይዘን መኖር ያሉብንም ነገሮች አሉ፡፡ ይገለጡ ቢባሉ እንኳን በተገቢው መንገድ ለመያዝ የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ ተገቢነት ይህን ይጠይቃልና፡፡
እስኪ የሀገራችን ኃያላን - የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ ተውና የሚገባችሁን ብቻ አድርጉ፡፡

Address

Gonder

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rising Ethio posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Rising Ethio:

Share