03/05/2023
አማራው ላይ የሚደረገው ዘመቻ ከአቶ ግርማ የሺጥላ ሞት ጋር ግንኙነት የለውም። የአቶ ግርማን ሞት አማራው ላይ የጀመሩትን ዘመቻ ማጠናከሪያ ነው ያደረጉት።
#አማራው ላይ ዘመቻ የተጀመረው በጦርነቱ ወቅት ያሳየው ስነልቦና ስላስፈራቸው ነው። ብርሃኑ ጁላ መሃል አገር እየተዝናና ከባድ መሳርያ አዘርፎ አገር ሲያስወጋ የአማራ አርሶ አደር በዱላና መጥረቢያ ጭምር ከሰራዊቱ የተቀማ መሳርያ አስመልሷል።
#ገዥዎቹ ሁለት ልብ ሲሆኑ አገር ቤት ያለው ብቻ ሳይሆን በውጭ ይኖር የነበረው አማራ ወደ ጦር ሜዳ መጥቷል።
#በጦርነቱ ወቅት የአማራውን አቅም የተመለከቱት ገዥዎች አማራ ከጦርነት ማግስት በዚህ ስነ ልቦናው ከተመለሰ አደገኛ ነው ብለው ፈርተዋል። ሰላማዊውን ዜጋ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ በመከልከል "ፅንፈኛ ፋኖ፣ኤርትራ ያሰለጠነችው" ማለት የጀመሩት በዚህ ፍርሃት ምክንያት ነው።
#አማራው የጠነከረ ስነ ልቦና እንዳለው ቢያውቁም የአማራ ብልፅግና አብሯቸው የሚውል እንኩቶ ጥርቅም እንደሆነ ያውቁታል። አንድ ቀን "ትግል ወዘተ" ብሎ መግለጫ አወጣ። ከዛ በኋላ የት እንዳለ አይታወቅም።
#ገዥዎቹ ዘመቻውን በጦርኑ ስነ ልቦና ሰግተው ቢጀምሩትም የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቁርጥ ቀን ማን አብሮት እንደነበር ያውቃል። ምንም እንኳ ዕዙ በአማራ ህዝብ ላይ የጥላቻ ወዝ በጠገቡት የሚመራ ቢሆንም በደንብ ከተሰራበት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት የህዝብን ውለታ ያውቁታል። በዚህ ዘመቻ በርካታ ምልክቶች ታይተዋል።
#አሁንም መታወቅ ያለበት ህዝብ ሲፈጅ የከረመን ኦነግ በዓለም አቀፍ መድረክ እየተደራደረ፣ አገር ያዳነን ኃይል ለመምታት የሚደረገው አካሄድ አገር ከማፍረስ ውጭ አላማውም ውጤቱም አያምርም። ገዥዎቹ አማራውን ከየ አቅጣጫው አዳክመው ርስቶቹን አስረክበው አንገቱን አስደፍተው "ስልጣናችን ቀና ብሎ እንዳያይ እናደርገዋለን" ብለው አስበዋል። የዘመቻው አላማ ይሄ ነው። የሚሆን አይደለም።
shifrew