ጎህ ሚዲያ Gohi media

ጎህ ሚዲያ Gohi media ጎህ ንጋት ፍካት ይከተሉን

06/12/2022

ወይም በሌላኛው አጠራሩ በጥቂቱ

✍ በምድር ላይ ካሉት ሚስጥራዊ ስፍራዎች አንዱ የቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ፡፡ ቤርሙዳ ትሪያንግል በአትላንቲክ ውቅያኖሶች ውስጥ ይገኛል ፤ ከአሜሪካ ፍለሎሪዳ ግዛት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በስተደቡብ በኩል ካሪቢያን ደሴት ያዋስነዋል ፡፡

✍ ቤርሙዳ ትሪያንግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ክርስቶፈር ኮሎምበስ ሲሆን ዘመኑም በ1449 ነበር ፡፡ ተጓዡ ክርስቶፈር ዓለምን በሚያስስበት ወቅት በዚህ ስፍራ ደርሶ አንድ ነገር ተመለከተና በማስታወሻው እንዲህ ሲል ፃፈ

"በአድማስ ላይ የሚደንስ እንግዳ የሆነ የብርሃን ጮራ ፤ በሰማይ ላይ የነገሰ የእሳት ነበልባል ፤ የአቅጣጫ መጠቆሚያን ኮመምፓስን የሚያመሰቃቅል ሀይል" ብሎት ነበር ፡፡

✍ እንደ ብዙዎች አነጋገር ከዛ ከቤርሙዳ ትሪያንግል ቡሃላ ያለውን የምድር ክፍል አዲስ አለም ወይም አዲስ ምድር ብለው ይጠሩታል

✍ ቤርሙዳ ትሪያንግል ባለልታወቀ ሚስጥር በርካታ መርከቦች እና የሰውን ልጅ ህይወት እና ሀብት እንደያዙ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጠፍቷል ! በአለማችን ላይ ከፍተኛ የመርከብና የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ የሚደረግበት በዚህ ስፍራ ላይ እንዲ አይነት እንቅስቃሴ ወይም እንግዳ የሆነ እና ሁሉን ውጦ የሚያስቀር ገደል መገኘቱ የሰውን ልጅ እስካሁን ግራ አጋብቷል ፡፡

✍ በቤርሙያ ትሪያንግል አካባቢ እንደ ወጡ ከቀሩት ውስጥ በጥቂቱ በ1812 ቲዎዶስያ በር አልስተን የተባለች የወቅቱ የአሜሪካን ም/ፕሬዝደንት የነበሩት የአሮን በር ልጅ ዲሴምበር 30 በተጠቀሰው አመት ፓትሮዎት በተባለች መርከብ ስትጓዝ በዚያው ቀርታለች ፡፡ በ1945 ፍላይት 19 የተባለች አውሮፕላን ከ14 ተጓዥ ጋር ጠፍታለች ፡፡ በዛኑ ወቅት ፍላይት 19 ፍለጋ የተላኩ 6 አውሮፕላኖች እና 27 ሰዎች እንደወጡ በዛው ቀርተዋል ፡፡ በ1948 ስታር ታይገር 19 የተባለች አውሮፕላን ከ6 አብራሪዎች እና ከ25 ተሳፋሪዎች ጋር ልትጠፋም ችላለች ፡፡ ከ65 አመታትቶች በፊት በዚ በቤርሙዳ ተትሪያንግል በየእለቱ 5 አውሮፕላኖች በዚህ አካባቢ ላይ ሲያልፉ የመስመጥ አደጋ ደርሶባቸዋል መስመጥ ብቻ ሳይሆን ደብዛቸውም ጠፍቷል ብዙ መርከቦች ከነተሳፋሪያቸው ላይመለሱ ቤርሙዳ ትሪያንግል ውስጥ ሊሰምጡ ችለዋል !!

✍ ለቤርሙዳ ትሪያንግል እንዲ መሆን ብዙ መላምቶች ተቀምጠዋል በጥቂቱ

1, ከፍተኛ የማግኔት እና የኤሌክትሮኒክስ ሃይል ያለው ደመና በአካባቢው ሰማይ ላይ መኖር የመርከቦችንና የአውሮፕላኖችን እንቅስቃሴ ያግዳል

2,ያልታወቁ በራሪ ፍጥረታት (UFO) በአካባቢው ሰፍረዋል

3, ሁሪካን የሚባለው ሃይለኛ አውሎ ንፋስ በአካባቢው ሊኖር ይችላል

4,በውቅያኖሱ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዝ አደገኛ ወንዝ ስላለ መርከቦችን እና ፕሌኖችን ጠራርጎ ይወስዳል

5, ሚቴን ሃይድሬት የተባለ ንጥረ ነገር በባህር ውስጥ በከፍተኛ መጠን ስላለ የውሃውን እፍጋት (ዴንሲቲ) ይቀንሰዋል የውሃው ዴንሲቲ በሚቀንስበት ወቅት መርከቦችን የመሸከም አቅሙ ስለሚወርድ መርከቦቹ በቀላሉ ይሰምጣሉ ፡፡

6,ሰይጣናዊ ቦታ ነው ተብሎም ይገመታል ! ! !
Share share

06/12/2022

ጎህ ሲቀድ ማለዳ በንጋቱ ፍካት፣
ደምቁ ሊታይ ጥዋት፣ጎህ ጠበቃ ሊሆን
ለኢትዮጵያዊነት።
ከጎህ ጋራ ታሪኮችን፣ባህላዌ እሳቢዎችን፣ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን እና አንገብጋቢ ዜናዎችን እያቀረበ ይጓዛል አብረዉን ይሁኑ።

05/12/2022

አባ ይፍቱኝ
Bewketu Seyoum

አባ ይፍቱኝ !
ሲዖል አለ ሲሉኝ፤ የለም ብየ ክጄ
የባልቴት ተረት ነው፤ በማለት ቀልጄ
አውቄ በድፍረት፤ በድያለሁና
ያንጹኝ በንስሐ ፤ ያንሱኝ በቀኖና
ሲዖል ከነጭፍራው፤ በጉም ተሸፍኖ
እንዴት ሳላየው ኖርኩ፤ ካጠገቤ ሆኖ?

አባ ይፍቱኝ

ሰይጣን ብሎ ነገር፤ የተጭበረበረ
ዋዛ ነው ቧልት ነው፤ ብየ አስብ ነበረ
ይሄው እውነት ሆኖ፤ ዋዛና ተረቱ
ባይኔ በብረቱ
ዲያብሎስን አየሁ፤ በሸሚዝ ዘንጦ
እልፍ ግዳይ ጥሎ፤ ቸብቸቦ ጨብጦ፡፡

አባ
ልክ እንደ ብርሌ ፤አጥንት ሲከሰከስ
አባይን አዋሽን ፤ የሚያስንቅ ደም ሲፈስ
ለምለም ፍጥረት ሁላ፤ ወደ አመድ ሲመለስ
ልክ እንደ ጧፍ ሐውልት ፤ ምስኪኖች ሲጋዩ
ምድጃው ዳር ሆነው፤ ይሄንን እያዩ
ገሃነም ከላይ ነው፤ ብለው መሳትዎ
እርስዎ እንደፈቱኝ ፤ እግዚሐር ይፍታዎ

“ፑቲን እውነታው እየተነገራቸው አይደለም”እንግሊዝ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለዩክሬኑ ጦርነት እውነታው እየተነገራቸው አይደለም ተባለ ፡፡የብሪታንያ የሳይበር እና ደኅንነት ኤጄንሲ...
31/03/2022

“ፑቲን እውነታው እየተነገራቸው አይደለም”እንግሊዝ
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለዩክሬኑ ጦርነት እውነታው እየተነገራቸው አይደለም ተባለ ፡፡
የብሪታንያ የሳይበር እና ደኅንነት ኤጄንሲ ኃላፊ የተወሰኑ የፑቲን አማካሪዎች መሬት ላይ ስላለው ሀቅ ለፕሬዚዳንቱ እየነገሯቸው አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል ፡፡
ፑቲን የስህተት መረጃዎች እንደሚደርሷቸው ጭምር ተነግሯል ፡፡
ጀርሚ ፍሌሚንግ እንደሚሉት የሩሲያ ወታደሮች ትዕዛዝ እየፈጸሙ አይደለም ፤በአጋጣሚ ጭምር የራሳቸውን የጦር ጀቶች መትተው እስከመጣል ደርሰዋል ፡፡
የፕሬዚደንቱ አማካሪዎች እውነታውን ለማሳት እንደማይደፍሩም ይነገራል፡፡
በእርግጥ የእንግሊዝ የደኅንነት ኃይሎች በሩሲያው እና በዩክሬኑ ጦርነት ለዜሌንሰኪ መንግስት ያዳላሉ የሚል ትችት ይሰነዘርባቸዋል፡፡
ጀርሚ እንደሚሉት ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላት ጥምረት ከፍተኛ ቀውስ እና ስጋት እንዲጋረጥ ያደረገ ነው ፡፡
ሞስኮ በኪዬቭ አከባቢ ጥቃት የመሰንዘር ወታደራዊ ዒላማዋን ችላ በማለት ወደ ምስራቃዊ ዩክሬን ፊቷን አዙራለች ቢባልም ጥቃቶች መቀጠላቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ናቸው ፡፡

እንደምትወዳት ንገራት ============== ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወስዳል ።   ቀለበት፥አምባር...
29/03/2022

እንደምትወዳት ንገራት
==============
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወስዳል ።

ቀለበት፥አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁል ጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት።

አበቡች ሁሉ ሳይርግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጣፍ
ያጸደ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላባ መብራት
አሁኑኑ ዛሬዉኑ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግሰ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀበዉ አመድ
ወደማትስበዉ አየር
ሳትቀየር
አንተም አንደበትህ ሳለህ፥እሷም ጀሮ ሳያጥራት
ዛሬዉኑ፥አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።
𝑣𝑖𝑎 𝑏𝑒𝑤𝑘𝑒𝑡𝑢 𝑠𝑒𝑦𝑜𝑢𝑚
𝑚𝑒𝑔𝑎𝑏𝑒𝑡 2014𝑒𝑐

ከትራሴ ግድም፥በተደፋው ሰማይ  ኮከብ እያበራ፥በመከዳየ ላይ ምንም አለነበብኩ፥ከህዋው ሰሌዳ እውነትና ንጋት፥እያደረ እንግዳ።       (ኗሪ አልባ ጎጆዎች)
24/03/2022

ከትራሴ ግድም፥በተደፋው ሰማይ
ኮከብ እያበራ፥በመከዳየ ላይ
ምንም አለነበብኩ፥ከህዋው ሰሌዳ
እውነትና ንጋት፥እያደረ እንግዳ።
(ኗሪ አልባ ጎጆዎች)

⚔️ 3 ተኛው የአለም ጦርነት ሊቀሰቀሰ ጫፋ ደረሰ ⚔️“ነጻ የአየር ቀጠና ማለት የ3ኛው ዓለም ጦርነት ልመና ነው”የአሜሪካ ሴናተሮች የሩሲያን እና የዩክሬን ጦርነት አስመልክቶ ነጻ የአየር ክ...
09/03/2022

⚔️ 3 ተኛው የአለም ጦርነት ሊቀሰቀሰ ጫፋ ደረሰ ⚔️

“ነጻ የአየር ቀጠና ማለት የ3ኛው ዓለም ጦርነት ልመና ነው”የአሜሪካ ሴናተሮች

የሩሲያን እና የዩክሬን ጦርነት አስመልክቶ ነጻ የአየር ክልልን ገቢራዊ ማድረግ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እንዲመጣ በር መክፈት ነው ተባለ፡፡

የዩናይትድ ስቴትሱ ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ነጻ የአየር ክልልን ዓለም የምትተገብር ከሆነ ሶስተኛው የፕላኔቷ ጦርነት ይቀሰቀሳል ባይ ናቸው ፡፡

በዩክሬን ሰማይ ስር የአየር ቀጠናውን ከበረራ ነጻ ለማድረግ መሞከር አደጋው የከፋ ነውም ይላሉ ::
ከዚህ በተጨማሪም ከሰሞኑ የአሜሪካዉ ፕሪዝዳንት ንግግር ሩሲያን አሰቆጥቷል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ከሩስያ ወደ ሀገራቸው በሚገባ ነዳጅ እና ጋዝ ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቀዋል።

አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ ካሳለፈች ሩሲያ ለአውሮጳ የምታቀብለውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ መዛቷ ይታወቃል።

ሩስያ የነዳጅ ማዕቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ እንደሚሆን እና ዳፋውም ለዓለም እንደሚተርፍ ማስጠንቀቋ አይዘነጋም።

የምዕራባውያን መንግስታት ከሩስያ በሚገባው የነዳጅ አቅርቦት ላይ ክልከላ ከጣሉ የነዳጅ ዋጋ 300 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ሩስያ መግለጿ ይታወሳል።

በአሁን ሰዓት በዓለም ገበያ ላይ የ1 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 140 ዶላር ደርሷል።

ፕረስ ቲቪ ነው፡፡

ለተጨባጭ መረጃ ጎህ ሚዲያን ላይክ በማድረግ ይከተሉን

Address

West
Gurbete

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጎህ ሚዲያ Gohi media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share