Habte hope

Habte hope Romans 15:13- May the God of hope fill you with all joy and peace as you trust in him, so that you may overflow with hope by the power of the Holy Spirit.

15/05/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።

-------------------------- // -------------------------

(ግንቦት 07/2018 ዓ.ም) ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል።
በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

ስልጣኑን አልተቀበለውም ... !በደቡብ ሱዳን Steward Sorobo Budia ለተባለ ካረፈ 5 አመት ለሞላው ግለሰብ ስልጣን ተሰጠ።መንግስት ስህተቱ የተፈጠረው እንዲሾሙ የገባልኝ ሰዎች ስም...
04/02/2026

ስልጣኑን አልተቀበለውም ... !

በደቡብ ሱዳን Steward Sorobo Budia ለተባለ ካረፈ 5 አመት ለሞላው ግለሰብ ስልጣን ተሰጠ።

መንግስት ስህተቱ የተፈጠረው እንዲሾሙ የገባልኝ ሰዎች ስም ዝርዝር በማመኔና ሳላጣራ በመሾሜ ነው ብሏል። ለዚህም ይቅርታ ጠይቋል።

የጎረቤታችን ደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች ግን ይቅርታው አልተዋጠላቸውም ፤ መንግስት ያገኘውን ስም Select All ብሎ ለየግለሰቡ እንደወጣለት እጣ በቦታው የሚሾም ነው እያሉ እየተቹት ነው።

የ2026  የዓለም ዋንጫ ድልድልየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል ! አሜሪካ ፣ካናዳ፣ሜክሲኮ በጋራ የሚያዘጋጁት የ2026 እኤአ የዓለም...
05/12/2025

የ2026 የዓለም ዋንጫ ድልድል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል ! አሜሪካ ፣ካናዳ፣ሜክሲኮ በጋራ የሚያዘጋጁት የ2026 እኤአ የዓለም ዋንጫ ድልድሉ ከደቂቃዎች በፊት በአሜሪካ ወጥቷል ።

AFCON 2025 draw resultGroup A1)- Morocco 🇲🇦2)- Mali 🇲🇱3)-Zambia 🇿🇲4)- Comoros 🇰🇲Group B 1)- Egypt 🇪🇬2)- South Africa 🇿🇦3...
27/01/2025

AFCON 2025 draw result

Group A

1)- Morocco 🇲🇦

2)- Mali 🇲🇱

3)-Zambia 🇿🇲

4)- Comoros 🇰🇲

Group B

1)- Egypt 🇪🇬

2)- South Africa 🇿🇦

3)- Angola 🇦🇴

4)- Zambia 🇿🇲

Group C

1)- Nigeria 🇳🇬

2)- Tunisia 🇹🇳

3)- Uganda 🇺🇬

4)- Tanzania 🇹🇿

Group D

1)- Senegal 🇸🇳

2)- DR Congo 🇨🇩

3)- Benin 🇧🇯

4)- Botswana 🇧🇼

Group E

1)- Algeria 🇩🇿

2)- Burkina Faso 🇧🇫

3)- Equatorial Guinea 🇬🇶

4)- Sudan 🇸🇩

Group F

1)- Ivory Coast 🇨🇮

2)- Cameroon 🇨🇲

3)- Gabon 🇬🇦

4)- Mozambique 🇲🇿

© GREAT AFRICA ✍🏿

23/01/2025
"ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በቅርቡ እገናኛለሁ"፦ ዶናልድ ትራምፕ ********የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ሊያደርጉ እ...
21/01/2025

"ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በቅርቡ እገናኛለሁ"፦ ዶናልድ ትራምፕ
********

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ሊያደርጉ እንደሆነ ተገልጿል።

ትራምፕ "ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በቅርቡ እገናኛለሁ፤ መቼ እንደሆነ ግን አላውቅም" ማለታቸውን ስፑቲንክ አስነብቧል።

አክለውም፥ የሩስያ - ዩክሬን ግጭትን ለማስቆም ከፑቲን ጋር ተገናኝተው በመምከር የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

ይህ መቼ እንደሚሳካ መገመት የሚቻለው ግን ከፑቲን ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ ብቻ መሆኑን ትራምፕ አመላክተዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩስያ ጋር ስምምነት በመፈረም ሰላም ለማውረድ ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ትራምፕ የጠቆሙት።

በሜሮን ንብረት

 የትኛሁ እምነት ተከታይ ሁኑ ይህ ግን የመቻቻል እሴታችንን ሊያደፈርስ የሚችል መጥፎ ልምምድ ነዉ።ሠዉ የሆነ ሁሉ ይቃወም
20/01/2025


የትኛሁ እምነት ተከታይ ሁኑ ይህ ግን የመቻቻል እሴታችንን ሊያደፈርስ የሚችል መጥፎ ልምምድ ነዉ።

ሠዉ የሆነ ሁሉ ይቃወም

 ይድረስ ለሚመለከተዉ ሁሉይህ መጥፎ ልምምድ ነዉ። ሁላችንም በዚህ ይብቃ ማለት አለብን😭ሼር አድርጉት ለአምቦ ዩኒቨርስቲየሀማኖት መቻቻል እና እኩልነት ባለባት ኢትዮጵያ ምድር ላይ.....እነዚ...
20/01/2025


ይድረስ ለሚመለከተዉ ሁሉ
ይህ መጥፎ ልምምድ ነዉ። ሁላችንም በዚህ ይብቃ ማለት አለብን
😭

ሼር አድርጉት ለአምቦ ዩኒቨርስቲ

የሀማኖት መቻቻል እና እኩልነት ባለባት ኢትዮጵያ ምድር ላይ.....

እነዚህ 3 ልጆች

* ነገ ሀገር ይገነባሉ
* ነገ ተምረው ለህብረተቡም ሆነ ለሀገር ይጠቅማሉ ሲባሉ

እነሱ ግን ከኢትዮጵያዊነት ባፈነገጠ መልኩ ብዙ ሚሊዮን ተከታዬች ያለውን የኦሮቶዶክ እምነት የሆነው የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት በማሾፍ ቬዝ በሚመስል መልኩ ቪዲዮ ሰርተው ቢቲክ ቶክ በሚባለው አፕ ለቀዋል::

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህ ልጆች በአምቦ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ እንደሆኑ ሲሆን

* የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት
* የአምቦ ዩኒቨርስቲ አላፊዎች

አጣርተው እነዚህ ልጆችን ለህግ እንዲያቀርብ ብዙ ኢትዮጵያውያን እየተማፀኑ ይገኛል::

እናንተም ይሄ ነገር ሼር በማድረግ እንድትተባበሩ
ጥሪ ቀርቧል::

😭

🌴🌴🌴

Footballers if they were bald part 1😂
20/01/2025

Footballers if they were bald part 1😂

በአሜሪካ ተቋርጦ የነበረው ቲክቶክ ተመለሰ********************በአሜሪካ ለሰዓታት አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው የቲክቶክ መተግበሪያ አሁን መልሶ መጀመሩ ታውቋል።ቲክቶክ አገልግሎቱን ...
19/01/2025

በአሜሪካ ተቋርጦ የነበረው ቲክቶክ ተመለሰ
********************

በአሜሪካ ለሰዓታት አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው የቲክቶክ መተግበሪያ አሁን መልሶ መጀመሩ ታውቋል።

ቲክቶክ አገልግሎቱን የመለሰው ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን በሚቀበሉባት የመጀመርያ ቀን ቲክቶክ የአሜሪካ ይዞታውን በተመለከተ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ሳይዘጋ እንዲቆይ እንደሚፈቅዱ ሃሳብ በመስጠታቸው ነው ተብሏል፡፡

ቲክቶክ ለአሜሪካ ገዥ የማይሸጥ ከሆነ መተግበሪያው በሀገሪቱ የሚኖረው የአገልግሎት የመጨረሻ ቀን ዛሬ እንዲሆን ተቀጥሮ የነበረ ሲሆን በዚሁ መሰረትም የቲክቶክ አገልግሎት በመላ ሃገሪቱ ለሰዓታት ቋርጦ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ዶናልድ ትራምፕ የህጉን አፈፃፀም ለማዘግየት እና ስምምነት ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት ቃል ከገቡ በኋላ ቲክቶክ አገልግሎትን ወደነበረበት ለመመለስ በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም ከ170 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ እንደተመለሰላቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Address

Moyale, Kenya Road
Hagere Mariam

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habte hope posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share