
25/04/2025
ደቡብ ወሎ ዞን ወታደራዊ አመራሮችን የአዋጊነት ስልጠና መስጠቱን በFB ገፁ አንብቤያለሁ።ነገር ግን ዱላ ይዞ አይደለም ሰው ከብት መጠበቅ የሚቀርበትን ሁኔታ መፍጠር ግድ ይለናል። ውጭ አገር ላይ ያለውን ቴክኖሎጅ ሳየው ኢትዮጵያ ታሳዝነኛለች።ከተማ ላይ ዱላ ይዞ ፖሊስ ሰው ሲጠብቅ ጎዳና ለጎዳና ግዳጅ ሲወጣ በጣም አዝኛለሁ።ለካስ መሪዎቻችን ወጣ ብለው አገር አያዩም ነበር ማለት ነው። መሳሪያና ሙሉ የውጊያ ትጥቅ ታጥቀህ ከተማ ላይ ፓትሮል ማድረግ ያሳፍራል።ውጩ አለምኮ በጣም አድጓል።እነ ዱባይ ላይ ፖሊስ ያየሁት ከወር ኋላ ነው።መሳሪያማ በጭራሽ አይቸ አላውቅም።ከመጣሁ ብዙ ቦታዎችን አይቻለሁ ወታደር አይቸ አላውቀም።ትራፊክ የሚባል ነገር ምንም የለም።ሁሉም ነገር በቴክኖሎጅ ነው።ወንጀል ሰርተህ 15 ደቂቃ አትቆይም ስትያዝ።በእርግጥ ዶክተር አብይ እድል ከሰጠነው የኢማራትን ቴክኖሎጅ አገራችን ላይ ያሳየን ይሆናል።የተጀመሩ ስራዎች ኮሊደር ልማቶች ሁሉ የሚያመላክቱት የውጩን አለማት የስልጣኔ ደረጃ ወደ አገራችንም እየገባ መሆኑን ነው። በቅርቡ በአላህ ፈቃድ መሳሪያና ዱላ የያዘ ፖሊስ የማናይባት ኢትዮጵያን እናያለን። ሰው እየጠበቅንኮ ልማት ማልማት አይቻልም። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአፈሙዝና ዱላ መውጣት አለበት።