Selihom Media, promotion and Event/ሰሊሆም ሚዲያ፣ ማስታወቂያና ኤቨንት

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • Selihom Media, promotion and Event/ሰሊሆም ሚዲያ፣ ማስታወቂያና ኤቨንት

Selihom Media, promotion and Event/ሰሊሆም ሚዲያ፣ ማስታወቂያና ኤቨንት "መልካም ነገር ልናጋራችሁ ዘወትር እንተጋለን"
አስደሳችና ወቅታዊ ነገሮችን ማግኘት ከፈለጉ ይቀላቀሉን!!!

የኢድ አል-ፈጥር በዓል  ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
10/04/2024

የኢድ አል-ፈጥር በዓል


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

  ወንጀለኛውን አሪፍ አልዪን በማፈላለግ እንተባበርሁላችንም  #ሼር በማድረግ ለተጨነቀች ነፍስ እንድረስዛሬ በሐረር ከተማ በ8 ዓመት የትዳር አጋሯ፣ በልጆቿ አባት አሲድ የተደፋባትን አያንቱ ...
21/03/2024


ወንጀለኛውን አሪፍ አልዪን በማፈላለግ እንተባበር
ሁላችንም #ሼር በማድረግ ለተጨነቀች ነፍስ እንድረስ

ዛሬ በሐረር ከተማ በ8 ዓመት የትዳር አጋሯ፣ በልጆቿ አባት አሲድ የተደፋባትን አያንቱ ሙስጠፋን በሕክምና ቦታ ሔጄበአካል አየዋት።😭😭

የቀደመ መልኳ ተራግፎ፣ ሰውነቷ ተቦዳድሶ በአካልም በሥነ-ልቦናም ተጎድታ ሳያት አንጀቴ ተላወሰ። ለካ በሰው ልጅ የዚህን ያክል ይጨከናል!? !?😭😭

ይህን አረመኔያዊ ተገባር የፈፀመው ሰው የውሐ ሽታ ከሆነ 2 ወር ሊሞላው ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

እባካችሁን ወገኖች ሐረር ከተማ ያላችሁ በሕይወት ፋና ሆስፒታል ድንገተኛ(ይማጅ) በመምጣት እህታችንን እናበረታታት።

መምጣት የማትችሉና በሩቅ ያላችሁ ወገኖች 👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
☎️+251912943262 አህመዲን አብዱረህማን(አጎት)
☎️ +251948749452 ሙስጠፋ ታዬ(አባት)

ቢያንስ ካሉበት ሁኔታ አንፃር ዘላቂ ነገሮች እስከሚመቻቹ ድረስ ለነገሮች ቅርብና አስታማሚም በሆነው አጎቷ የባንክ አካውንት #ከ100 ብር ጀምሮ የቻልነውን እናድርግ።

(CBE👉 1000076818952 አህመዲን አብዱረህማን ሙሳ)

ይህን አረመኔ በተለያየ አጋጣሚ ያየ ሰው በአቅራቢያው ባለ ፖሊስ ጣቢያ በመጠቆም ሰዋዊ ግዴታችንን እንወጣ።

የአብሮነት ከተማ 🇪🇹 ድሬ🕌 ሮመዳን  ❤  ዐቢይ ጾም⛪📷👉 Yordanos Brhane
21/03/2024

የአብሮነት ከተማ 🇪🇹 ድሬ

🕌 ሮመዳን ❤ ዐቢይ ጾም⛪

📷👉 Yordanos Brhane

  ~ ማክሰኞ የካቲት ⓳ #በነፃ               ማዕዶት የኪነ-ጥበብ ማህበር ከሰምና ወርቅ ጋር በመተባበር ❷❶ኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት በሐረር ከተማ የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 19 አዘጋ...
24/02/2024

~ ማክሰኞ የካቲት ⓳
#በነፃ



ማዕዶት የኪነ-ጥበብ ማህበር ከሰምና ወርቅ ጋር በመተባበር ❷❶ኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት በሐረር ከተማ የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 19 አዘጋጅቷል።

በዚህ ምሽት ላይ ስራዎቻቸውን ለማቅረብና ለመታደም በርካቶች አብረውን ያመሻሉ።


💠 ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ
💠 አርቲስት ሥዩም ተፈራ
💠 አዘጋጅና ፀሐፊ ጌትነት እንየው

📝ቀጠሮውን ከእኛ ጋር ያድርጉ። መገኛችን ወንደርላንድ ኢንተርናሽናል ሆቴል ነው።

📅


👉ግጥሞች 👉ወግ 👉መነባንብ 👉ዲስኩር 👉መዘክር 👉 የአንድ ሠው ቴአትር የፕሮግራማችን አካል ናቸው።

👉 በነፃ

ለበለጠ መረጃ 👉 #0983751084 ይደውሉ!!!

✅✅✅✅ ✅✅✅✅
🎭🎶 ማዕዶት የኪነ-ጥበብ ማህበር / Maedot Art Association - Harar
📞 +251983751084 / +251904049504
Like our youtube channel👇
👉 https://youtube.com/
Like our page👇
👉 https://www.facebook.com/MaedotArt
Like our Facebook group👇
👉 https://facebook.com/groups/2487478338193332/
Join our Telegram Channel 👇
👉https://t.me/bbbgytrxgvdscittyssaw
follow on Instagram
👉https://instagram.com/maedot_art_association?
"ጥበብን ለጥበበኞች"

 ኢትዮጵያዊው ጎግል፣ ጨዋታ የማያጣው፣ በቂ መረጃ ከማስረጃ ጋር የሚኖረው ጀግናው የስፖርት ሰው ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን።
23/01/2024



ኢትዮጵያዊው ጎግል፣ ጨዋታ የማያጣው፣ በቂ መረጃ ከማስረጃ ጋር የሚኖረው ጀግናው የስፖርት ሰው ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን።

  ተወዳጁ የEbs የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈተወዳጁ ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ...
14/01/2024



ተወዳጁ የEbs የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ

ተወዳጁ ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከወጣም በኃላ ኑሮ በአሜሪካ የተሰኜ አስተማሪ ፕሮግራም ለኢትዮጵያን ሲያቀርብ የነበረ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነበር

ከውጭ ሀገር ተመልሶም በEbs የእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ዝግጅቶችን በማቅረብ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ የጋዜጠነትን ስነ ምግባር በአግባቡ የተላበሰ በሳል ጋዜጠኛ ነበር::

 #ሐረርበሀረር ከተማ የፈረቃ ታክሲ መቅረቱን የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርተ ቢሮ አስታወቀ።በሀረር ከተማ የፈረቃ ታክሲ መሰረቱን የክልሉ መንገደ ልማትና ትራንስፖርተ ቢሮ አስታውቋል።የሐ...
11/01/2024

#ሐረር

በሀረር ከተማ የፈረቃ ታክሲ መቅረቱን የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርተ ቢሮ አስታወቀ።

በሀረር ከተማ የፈረቃ ታክሲ መሰረቱን የክልሉ መንገደ ልማትና ትራንስፖርተ ቢሮ አስታውቋል።

የሐረሪ ክልል ትራንስፖርት መንገድ ልማት ቢሮ በ7 ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ከቀን 03/05/2016 እለት ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆኑትን ተግባራት ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

ቢሮው ረዘም ላሉ ጊዜያት በተደጋጋሚ ሲቀርቡ የነበሩት ጥያቄዎች እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰትን ከማሳለጥና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት(ተደራሽነትን) ከማረጋገጥ እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉትን ክፍተቶች ከማስተካከል አንፃር ጉዳዮቹን በማጤን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በመሸም መሰረት ተከታዮቹን ሰባት ውሳኔ አሳልፏል።

1. የታክሲ ፈረቃ ከጥር 03/2016 ጀምሮ የቀረ መሆኑን

2. ታክሲዎች በተመደቡበት ቀጣናና የታፔላ ስምሪት ብቻ እንዲሰሩ ፣ የታፔላ ስምሪት ያልወሰዱ በፍጥነት እንዲወስዱ ፤ ያለ ታፔላ ታክሲ መስራት የማይችል መሆኑ፣

3. የሌላ ክልል ታርጋ ያላቸው ታክሲዎች በሀረር ከተማ ወሰን ውስጥ በትራንስፖርቱ ህጉ መሰረት መንቀሳቀስ የማይችሉ መሆኑን፤

4. ያለመደብ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ( በሁለት ቁጥር ታርጋ፣ የንግድ ስራ የሚሰሩ ሀይሉክስ መኪናዎች ፣ ከኃላ ክፍት ፔጆዎች ወዘተ.. በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ትክክለኛው መደብ እንደመለሱ፣ ስቲከር ለጥፈው በሁለት ቁጥር ታርጋ የሚሰሩ ታክሲ መስራት የማይችሉ መሆኑን፤

5. የሽንኮር ሰላም ጎዳና (ከደሴ ሆቴል እሰከ ሽንኮር ማዞሪያ) ዘወትር እሁድ እሁድ ከጠዋቱ12 ሰዓት እስከ ረፈዱ 3 ስዓት ድረስ ማንኛውም ከተፈቀደለት ተሸከርካሪ ውጪ መንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑን፣ የተፈቀደለት ማለት 1ኛ አንቡላንስ ፤የፀጥታ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በልዩ ሁኔታ እንዲያልፉ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተፈቀደላቸው ተሸከርካሪዎች በስተቀር

6. ከ 3ቶን በላይ የሆኑ ተሸከርካሪዎች በሀማሬሳ በኩል በቀጥታ ወደ ከተማ መግባት የሚችሉት ከሰዓት ከ12 ሰዓት እሰከ ጠዋት 12 ሰዓት መሆኑን፤

7. ከጥር 10/2016 ጀምሮ ክልላዊ የትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ መፍጠሪያና ቁጥጥር ዘመቻ በትራፊክ ፖሊስ፣የትራንስፖርት ተቋጣጣሪና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚደረግ መሆኑ ተወስኗል።

02 / 05 / 2016

ምንጭ👉 harar mass media agency

"ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያለ ምክንያት መሞትስ ?" ጌትነት ወንድሜ በቅርስነት የተመዘገበው ሎምባርደያ ምሽት ሲፈርስ በመጋዘን ተከራይተው ያስቀመጡትን መፀሀፍ በማውጣት ላይ ሳሉ አፍራሽ ግ...
11/01/2024

"ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያለ ምክንያት መሞትስ ?"

ጌትነት ወንድሜ በቅርስነት የተመዘገበው ሎምባርደያ ምሽት ሲፈርስ በመጋዘን ተከራይተው ያስቀመጡትን መፀሀፍ በማውጣት ላይ ሳሉ አፍራሽ ግብረ ሀይሉ በላያቸው ላይ ቤቱን ደረመሱት።

ወንድሜ ጌትነት ከነያዘው መፀሀፍ ጀርባው ላይ የቤቱ ክምር ዲንጋይ ወደቀበት 😭
ጌትነት አሮጌ መፀሀፍ እየሸጠ የሚተዳደር የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው። እስፓይናል ኮርዱ ሙሉ በሙሉ ነው የደቀቀው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገባ አልተሳካም ወንድሜ ገና ገና መኖር ሰይጀምር ተቀጠፋ።

ቅርሱም ሎምባርደያ ፈረሰ
ወንድሜም ተቀጠፈ 😭
ማነው ሐላፊነት የሚወስደው ማነው ?

የድሃ እንባ ይጮሃል ፈጣሪ ፍርዱን ብቻ ስጥ ስርአት ቀብሩ ሐሙስ ጥር 02/2016 በደብረዘይት (ቢሾፍቱ ) ይፈፀማል::

via Teddy Bacha

እያዩ ፈንገስ ... "ቧለቲካ" ቴአትር ታገደ። ደራሲ ... በረከት በላይነህተዋናይ ... ግሩም ዘነበ     የመንግስት የፀጥታ አካላት ለአለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ከነ...
10/01/2024

እያዩ ፈንገስ ... "ቧለቲካ" ቴአትር ታገደ።

ደራሲ ... በረከት በላይነህ
ተዋናይ ... ግሩም ዘነበ

የመንግስት የፀጥታ አካላት ለአለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ከነገ ሐሙስ ጥር 2/2016 አ.ም ጀምሮ እያዩ ፈንገስ "ቧለቲካ" ቴአትር ለህዝብ እንዳይታይ ተከልክሏል።
ቴአትር ቤቱም ይህንኑ የመንግስት የፀጥታ ሀላፊዎች ትእዛዝ ለቴአትሩ አዘጋጆቹ በማሳወቅ ውሉን ማቋረጡን ገልጿል።

ማስታወሻ፦

* በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የአንድ ሰው የሙሉ ጊዜ ቴአትር
* እያዩ ፈንገስ በመጋቢት /2006 ዓ.ም ነው መታየት የጀመረው
* እያዩ ፈንገስ ዘንድሮ ( 2016 ) 10 አመት ሞላው።
* በራስ ሆቴል ይዘጋጅ በነበረው ጦቢያ ፖየቲክ ጃዝና በተለያዩ መድረኮች ከ25 በላይ ( ከ20 - 30 ደቂቃ ) የሚፈጁ ክፍሎች የተሰራ
የሙሉ ጊዜ ቴአትር
1. እያዩ ፈንገስ ቁጥር 1 ..... "ፌስታሌን"
2. እያዩ ፈንገስ ቁጥር 2 ..... "አጀንዳዬን"
3. እያዩ ፈንገስ ቁጥር 3 ..... "ቧለቲካ" ተሰርተዋል።

* "ቧለቲካ" መታየት የጀመረው ጥቅምት 15/2016
* ዘወትር ሀሙስና እሁድ እየታየ ነበር
* "ቧለቲካ" ከጥቅምት 15/2016 ጀምሮ 20 መድረኮች ተሰርቷል።

via Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

አትሌት ታደሰ ለሚ ከግድያ ሙከራ ተርፏልአትሌት ታደሰ ለሚ እሁድ ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ለጉዳይ ከወጣበት ስፍራ  ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ ከቀኑ 11:30 በሱሉልታ ከተማ በተለምዶ  ...
02/01/2024

አትሌት ታደሰ ለሚ ከግድያ ሙከራ ተርፏል

አትሌት ታደሰ ለሚ እሁድ ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ለጉዳይ ከወጣበት ስፍራ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ ከቀኑ 11:30 በሱሉልታ ከተማ በተለምዶ አስር ኪሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት ተገለፀ።

አትሌቱ ሲያሽከርክር የነበረውን መኪና መንገድ ዘግተው፣ መኪናው ከመቱበት በኋላ የግድያ ሙከራ እንዳደረጉበት ተገልጿል።

የግድያ ሙከራው በሚደረግበት ወቅት እንደ አጋጣሚ በአካባቢው የትራፊክ ፖሊሶዎች ደርሰው ሊታርፉት እንደቻሉ ተጠቁማል።

የግድያ ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩት አካላት የያዙትን መኪና ተራፊኮቹ የተመለኩት ቢሆንም ሊደረስባቸው ባለመቻሉ ለግዜው ማምለጣቸው ተነግርዋል።

እንድ አትሌቱ አስታየት ከሆነ የግድያ ሙከራው ለአራተኛ ግዜ እንደተሞከረበት ጠቅሶ፣ በጫካ ልምምድ በሚያደርግበት ስፍራ በመምጣት የግድያ ሙከራውን ቢያደርጉም፣ አብረውት ልምምድ በሚሰሩ ጓደኞዎቹ አማካኝነት መትረፉን አስረድተዋል ።

አትሌቱ ኢትዮጵያን በተለያዩ ሻምፒዮናዎች በ800 እና 1500 ሜትር መወከሉ ይታወሳል።

Ethio Athletics Inside

"ትንኮሳ ከተፈፀመብን የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለመጠቀም እንገደዳለን" - የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንየሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ትንኮሳ ከተፈፀመባት የኒውክሌር ጦር...
21/12/2023

"ትንኮሳ ከተፈፀመብን የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለመጠቀም እንገደዳለን" - የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ትንኮሳ ከተፈፀመባት የኒውክሌር ጦር መሳሪያዋን ለመጠቀም እንደምትገደድ አስጠንቅቀዋል።

ኪም ጆንግ ኡን ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት በቅርቡ በሀገሪቱ አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ላይ የተሳተፉ ወታደሮችን ባመሰገኑበት ወቅት ነው።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በምስጋና ስነ-ስርዓቱ ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ጠላት ባሏቸው ላይ አስቀድመው ለመጠቀም ደጋግመው መዛታቸው ተገልጿል።

ሰሜን ኮርያ ያስወነጨፈችው አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል አቅማችንን ለጠላቶቻችን ያሳየንበትም ነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ባላንጣ ያሏቸውን ሀገራት ከፀብ አጫሪነት ተግባር እንዲታቀቡ ያሳሰቡት ፕሬዝዳንቱ፤ ሀገሪቱ ትንኮሳ የሚፈጸምባት ከሆነ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከመጠቀም ወደ ኋላ አንደማትል ነው የገለፁት።

ሰሜን ኮሪያ ሰኞ እለት በአምስት ወራት ውስጥ የመጀመሪያውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ያደረገች ሲሆን፤ የሞከረችው የባለስቲክ ሚሳኤል 15 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት የመጓዝ አቅም እንዳለው ተጠቁሟል።

እንደ ኤኤንሲ ዘገባ ሰሜን ኮርያ ሰሞኑን ያስወነጨፈችው አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ከጎረቤት ሀገራት ባለፈ አሜሪካ መድረስ መቻሉ ትልቅ ስጋት መደቀኑን ተገልጿል።

ጃፓን፣ ደቡብ ኮርያ እና አሜሪካ በሰሜን ኮርያ የሚሳኤል ስጋት ዙርያ የመረጃ መለዋወጫ ስርዓት ባሳለፍነው ሰኞ ተግባራዊ ማድረጋቸው ይታወሳል።

📢📢📢ዳግም ፋርማሲ ~ ⒹⒶⒼⒾⓂ ⓅⒽⒶⓇⓂⒶⒸⓎ  በከተማችን ሐረር ጥራት ያለቸውን መድሐኒቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የምናውቀው ሲንቦና ፋርማሲ ተደራሽነቱን በማስፋት   ሥያሜ ሁለተኛውን ቅር...
20/12/2023

📢📢📢ዳግም ፋርማሲ ~ ⒹⒶⒼⒾⓂ ⓅⒽⒶⓇⓂⒶⒸⓎ



በከተማችን ሐረር ጥራት ያለቸውን መድሐኒቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የምናውቀው ሲንቦና ፋርማሲ ተደራሽነቱን በማስፋት ሥያሜ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ በከተማው እንብርት(አጂፕ) ላይ ከፍቷል፡፡

በማንኝውም ሰዓት ሁሉንም መድሐኒቶችን ማግኘት የሚችሉበት በብቁ ባለሞያዎች የሚመራው ፋርማሲ ከነገ ጀምሮ አገልግሎቱን መስጠት ይጀምራል፡፡

አድራሻ~ ሐረር አጂፕ ነዳጅ ማደያ ጎን
☎️ 0910062563 / 0940680111

Address

Harar

Telephone

+251904049504

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Selihom Media, promotion and Event/ሰሊሆም ሚዲያ፣ ማስታወቂያና ኤቨንት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Selihom Media, promotion and Event/ሰሊሆም ሚዲያ፣ ማስታወቂያና ኤቨንት:

Share