04/05/2026
#ኢመደአ ለኢትዮጵያ ባህር ኃይል ከፍተኛ መኮንኖች የሳይበር ደህንነት ስልጠና ሰጠ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ለኢትዮጵያ ባህር ኃይል ከፍተኛ መኮንኖች የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል። ይህ ስልጠና በዋነኝነት ትኩረቱን ያደረገው በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዙ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከልና የተቋሙን የመረጃ ደህንነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ነው። ስልጠናው በዘመናዊው የቴክኖሎጂ ዘመን ለሀገር መከላከያ ዘርፍ አስፈላጊ የሆነውን የዲጂታል እውቀት ለማስጨበጥ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ እንደገለጹት፣ ስልጠናው ሁለቱ ተቋማት ከዚህ ቀደም በነበራቸው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት የተከናወነ ሲሆን በተለይም በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በመረጃ ልውውጥና በሰው ኃይል ልማት ዙሪያ ተቋማቱ በጋራ ለመሥራት የገቡትን ቃል የሚያሳይ እንደሆነ ተመላክቷል። ስልጠናው የሁለቱን ተቋማት ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረውም ኮሞደሩ ገልጸዋል።
ኮሞደሩ አክለውም የባህር ኃይሉ የሚጠቀማቸው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመጠቆም፣ ስልጠናው እነዚህን መሣሪያዎች በጥንቃቄ ለመያዝ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ውጤታማና ስኬታማ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ለመፈጸም የቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማቶችን ከጠላት ጥቃት መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ስልጠናው የአባላቱን የመከላከል አቅም እንደሚያሳድግ እምነታቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ኮሞደሩ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የዲጂታል ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፣ መሰል የንቃተ-ህሊና ማጎልበቻ መድረኮች በቀጣይነት በተለያዩ የኃይል ክፍሎች ውስጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። የባህር ኃይሉ ወደፊትም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በቅርበትና በአጋርነት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/.../information-network.../
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933
The Information Network Security Administration (INSA) was first established in 2007 by the Council of Ministers Regulation No. 130/2007 with the aim of protecting our country's information and information infrastructures from attacks and safeguarding national interests. Our ...