
18/06/2025
የድህረ እዉነት ዘመንን የዋጀ ከመደመር እሳቤ የተቀዳ ሁሉንም አቅሞች ያሰባሰበ ኮሙኒኬሽን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ወሳኝ ነዉ :-አቶ ዲኒር ዩሱፍ
"በሀረሪ ክልል በአባዲር ወረዳ ለህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች በገዥ ትርክት ግንባታና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ።
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዲኒር ዩሱፍ በፓርቲያችን 2ተኛው መደበኛ ጉባኤ አፅንኦት የተሰጣቸው ገዥ ትርክት እና የኮሙኒኬሽን ስራችን ዙሪያ ውጤታማ ተግባራት ለማከናወን ይረዳ ዘንድ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መዘጋጀቱን በመክፈቻ መልእክት ያስተላለፏት
የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና አባላት ማኅበራዊ ሚዲያውን ለገዥ ትርክት ግንባታ፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ለዕውቀት ሽግግር እና የኢትዮጵያን እውነት ለመግለጥ ዘመነ መረብን የሚመጥን ጠንካራ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የሚድያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት የየዕለት ተግባር ነው ያሉት ሀላፊው የሚዲያ አጠቃቀማችንም የሀገር እና የህዝቦች አንድነት እና ወድማማችነትን ሊያጎለብቱ የሚገቡ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሴይፍ ጌታቸው በበኩላቸው ብዝሃነትን ማዕከል ያደረገ አሳባሳቢ ትርክት መገንባት ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል ።
የተዛባውን ትርክት በማከም፣ ልዩነትን በማጥበብና ስብራትን በመጠገን የብሔራዊነት ትርክት በመገንባት ሀገራዊ አንድነትን ማፅናት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዘርፍ ኃላፊን ፣ የወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ የወረዳ ፓርቲ ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።