
18/05/2025
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ጅማ ከተማ ገቡ።
ወደ ከተማዋ ሲደርሱ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮችን ጨምሮ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከነገ ጀምሮ ለ2 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሌማት ትሩፋት ምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኢትዮጵያ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም መድረክ ላይ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል ያካሄድናቸው ጥረቶች እና የተገኙ ልምዶች በስፋት ይገመገማሉ ተብሎ ይጠበቃል።