19/09/2025
አንድ አሳ አስጋሪ ገና ሳይነጋ በጠዋት ተነስቶ ወደ ባህር ወረደ:: ባህሩ ዳርቻ ሲደርስ ጨለማ ስለነበር ከውሃው ዳር ቁጭ አለ፡፡ ዳሰስ ሲያደርግ እግሩ ሥር አንድ ጆንያ ሙሉ ድንጋይ አገኘ።
የአሳ ማጥመጃ መረቡን ከጎኑ በማስቀመጥ ፀሐይ ወጥታ በደንብ ብርሃን ሆኖ መረቡን እስኪጥል ድረስ የሚሠራው ስላልነበረው እግሩ ሥር ካገኘው ድንጋይ አንዱን አውጥቶ ወረወረው:: የተወረወረው ድንጋይ ራቅ ብሎ የባህሩ ውሃ ላይሲያርፍ ጨንቧ የሚል ድምጽ አሰምቶ በዚያው ሰጠመ:: አሳ አስጋሪው ደስ ስላለው ደግሞ ሌላ ድንጋይ አንስቶ ወረወረ። የተወረወረው ድንጋይ ውሃው ላይ ሲያርፍ ተመሳሳይ ድምጽ በማሰማት አሁንም ቁልቁል ሰጠመ።
በዚህ ሁኔታ አሳ አስጋሪው ሌላ ምንም የሚሠራው ስላልነበረው በጆንያው ዉስጥ የነበረውን ድንጋይ ተራ በተራ እየወረወረ ጨርሶ ፀሐይ ስትወጣ እና ብርሃን መታየት ሲጀምርከነበረው ጆንያ ሙሉ ድንጋይ ውስጥ ለመጨርሻ ጊዜ ሊወረዉር በእጁ የያዘው አንድ ትንሽ ድንጋይ ብቻ ነበር የቀረው:: አሁን ብርሃን ስላለ ድንጋዩን ከመወርወሩ በፊት ምን እንደሆነ ለማወቅ በደንብ አገላብጦ ተመለከተው:: በእጁ የያዘው ድንጋይ አልማዝ መሆነን ሲያውቅ በጣም ተናደደ፡፡ ለካስ ያ በጆንያ የሞላው እና እየወረወረ ባህር ውስጥ ሲጨምረው የነበረ ድንጋይ በሙሉ አልማዝ ኖሯል። በእጁ የያዘው ነገር ምን ያክል ዋጋ እንዳለው ሳያውቅ ጥልቁ ባህር ዉስጥ በመወርወር ያን ሁሉ ኃብት አባከነው፡፡
ሁላችንም በሕይወት ስንኖር ከአንድ ጆንያ አልማዝ የበለጠ ዋጋ ያለው 'ጊዜ' የሚባል ውድ ነገር እናገኛለን፡፡ ነገር ግን ብዙዎቻችን ይህን ያገኘነውን ውድ ነገር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ሳንገነዘብ ልክ እንደ አሳ አስጋሪው በጣም ብዙውን መልሰን ከማናገኝበት ጥልቅ ባህር ዉስጥ ወርውረን ልንጨርስ ትንሽ ሲቀረን ያ ያባከንነው ጊዜ የነበረውን ዋጋ እንረዳለን:: ነገር ግን የተወረወረውን መልሶ ማግኘት አይቻልም።
ያገኘነውን የጊዜ ዋጋ በሚገባ ተገንዝበን ጥቅም ላይ ማዋል ከቻልን ግን ለእራሳችንም ሆነ ለአገር የሚበጁ ብዙ ተግባሮችን መፈፅም እንችላለን፡፡ በመጨርሻው ሰዓትም የሚቆጨን ነገር አይኖርም።
👉👉ሳናውቅ የምናባክነው ኃብት
🙏በስኬት የተሞላ መልካም ሳምንት ይሁንል።
◉◉ በታሪኮቹ ከተማራችሁ ቴሌግራማችንን ፎሎ እንድታደርጉን በአክብሮት ጠይቅን።◉◉
▰◍ ተጨማሪ ፅሁፎችን ለማግኘት ቴሌግራምችንን ይጓብኙ ብዙ ይማራሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇??👇👇👇👇
Telegram https://mubesabr