Munib Hay

Munib Hay Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Munib Hay, Digital creator, Harar.

የሚኒስቴሮች ሹመት ዜናዎች ዉስጥ የብዙዎች ትኩረት  የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የብዙዎች ሀሳብ በትምህርት ሚኒስቴር በሚኒስትርነት ይቀጥላሉ
06/10/2026

የሚኒስቴሮች ሹመት ዜናዎች ዉስጥ የብዙዎች ትኩረት የትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የብዙዎች ሀሳብ በትምህርት ሚኒስቴር በሚኒስትርነት ይቀጥላሉ

06/10/2026

Exactly i appreciate because diversity is Teacher.

05/10/2026

ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አሠራርን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 8 አመታት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ዐቢይ አህመድን (ዶ/ር) ለቀጣይ የሥራ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መርጧል።

03/10/2026

Ethiopian Prime Minister of Ethiopia

ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ተሹመዋልየሀረሪ ክልል ምክር ቤት ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ መርጧል
03/10/2026

ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
በመሆን ተሹመዋል

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ መርጧል

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበውን የክልሉ መንግሥት ካቢኔ አባላትን ሹመት አፅድቋል ‎አቶ ጌቱ ነገዎ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ...
03/10/2026

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበውን የክልሉ መንግሥት ካቢኔ አባላትን ሹመት አፅድቋል
‎
አቶ ጌቱ ነገዎ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል
‎

🦅 intelligence
03/10/2026

🦅 intelligence

ትምህርት ሚኒስቴር UNICEF ለሀረሪ ክልል የትምህርት ቢሮው  የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ***************************** በሀረሪ ክልል ለሚገኙ ለገጠር ትምህርት ቤቶች...
30/09/2026

ትምህርት ሚኒስቴር UNICEF ለሀረሪ ክልል የትምህርት ቢሮው የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ
*****************************
በሀረሪ ክልል ለሚገኙ ለገጠር ትምህርት ቤቶች
የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (EMIS)
Educational Management Information System ዘመናዊ ለማድረግ የላፕቶፕ ድጋፍ አደረገ!
‎
ሀረር ፣ መስከረም 20/2019 ዓ.ም የሀረሪ ክልል የትምህርት ቢሮ የመረጃ አስተዳደርን (EMIS) ዘመናዊ ለማድረግ እና ትምህርት ቤቶች በቀጥታ የትምህርት መረጃ መጫን እንዲችሉ UNICEF የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ።

የተማሪዎች የምዝገባ ​መረጃዎች ከየመዋቅሩ (ከትምህርት ቤት እስከ ትምህርት ሚኒስቴር) ይሰበሰባሉ፣ ይተነተናሉ፣ ከዚያም ለሪፖርት ዝግጁ ይሆናሉ።
* ስለ EMIS (የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት) ሶፍትዌር installation ትምህርት ሚኒስቴር UNICEF የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ በክልሉ በሶፊ እና በኤረር ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 20 ትምህርት ቤቶች የተበረከተ ሲሆን፥ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት አንድ አንድ ላፕቶፕ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
‎
‎የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለጹት ይህ ድጋፍ በትምህርት ቤቶች ያለውን የመረጃ አያያዝ ሥርዓት በእጅጉ የሚያቀልጥፍ ነው።
‎
‎ትምህርት ቤቶቹ ተወካዮችም የተበረከቱትን ላፕቶፖች ከቢሮ ኃላፊው አቶ ጌቱ ነገዎ እጅ ተረክበዋል።

በዚህ ዓመት በሁሉም ት/ቤቶች እየተተገበረ የሚገኘው የትምህርት የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት (EMIS) ምንድን ነው?

EMIS (Education Management Information System) ማለት የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ማለት ነው። ​ይህ ሥርዓት ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድረው ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፦
* ከተማሪዎች፣ ከመምህራን እና ከትምህርት ቤቶች መረጃዎችን ይሰበስባል።
* የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለመገምገም ይረዳል።

የEMIS ዋና ዋና ስራዎች
* ​የተማሪዎች ት/ቤት የምዝገባ መረጃ፣ የተማሪዎች ውጤት እና የተማሪዎች ዝውውር።
* ​የመምህራን የትምህርት ደረጃ፣ የሥራ ልምድ
እና ስርጭት ወዘተ።
* የመሠረተ-ልማት መረጃ፡- የትሞህርት ቤቶች የክፍሎች ብዛት፣ ላብራቶሪዎች እና የትሞህርት ቤቶች የመጽሐፍት አቅርቦት ወዘተ ያካትታል ።
* የፋይናንስ መረጃ፡ ለትምህርት ቤቶች የሚመደብ በጀት እና ወጪ ወዘተ ያካትታል።

ሥርዓቱ እንዴት ይሠራል?
የተማሪዎች የምዝገባ ​መረጃዎች ከየመዋቅሩ (ከትምህርት ቤት እስከ ትምህርት ሚኒስቴር) ይሰበሰባሉ፣ ይተነተናሉ፣ ከዚያም ለሪፖርት ዝግጁ ይሆናሉ።
* ስለ EMIS (የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት) ሶፍትዌር አጠቃቀም እና የመረጃ አያያዝ ሂደት ዋና ዋና ነጥቦች:
​1. የተማሪዎች ት/ቤት ምዝገባ መረጃ ማስገባት (Data Entry)
* ተማሪዎች፦ በየዓመቱ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ እና ነባር ተማሪዎችን ማሸጋገር።
* መምህራን፦ አዳዲስ መምህራን ተቀጣሪዎችን መመዝገብ እና ስልጠና ወይም የደረጃ እድገት ሲያገኙ መረጃቸውን ማሻሻል።
* ትምህርት_ቤቶች፦ የግንባታ ሁኔታን እና የሚገኙ ቁሳቁሶችን (ጠረጴዛ፣ መጽሐፍ) መመዝገብ።

​2. የመረጃ ጥራት (Data Quality)
​መረጃው ትክክለኛ እንዲሆን የሚከተሉትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፦
* ​መረጃዎችን በወቅቱ የተማሪዎችን ት/ቤት
የምዝገባ መረጃ ማስገባት፣
* የተደገሙ የተማሪዎች ት/ቤት የምዝገባ መረጃዎች (Duplicates) አለመኖራቸውን ማረጋገጥ፣
* የተማሪዎች ስሞች ከትክክለኛው ሰነድ ጋር
መመሳሰላቸውን ማየት፣

​3. ሪፖርት ማውጣት (Reporting)
​ሥርዓቱ መረጃዎችን በሰንጠረዥ እና በግራፍ መልክ ያቀርባል። ​ይህም ትምህርት ቤቱ ምን እንደጎደለው እና ምን መሻሻል እንዳለበት ለማወቅ ይረዳል።

* መረጃን እንዴት መሙላት እና ሪፖርት ማዘጋጀት እንደሚቻል በዝርዝር እንመልከት
​3.1 መረጃ እንዴት ይሞላል? (Data Entry Process)
* የመረጃ ቅጾች (Forms): በመጀመሪያ መረጃው በወረቀት ቅጾች ላይ ይሰበሰባል። እነዚህ ቅጾች የተማሪ፣ የመምህር እና የትምህርት ቤት መረጃዎችን ያካተቱ ናቸው።
* የተሰበሰበው መረጃ በ EMIS ሶፍትዌር ውስጥ በየዘርፉ ይገባል
እያንዳንዱ ተማሪ ወይም መምህር መለያ ቁጥር (ID) ሊኖረው ይገባል
* የተማሪዎች መረጃዎች ከገባ በኋላ ስህተቶች ካሉ ይታረማሉ። ለምሳሌ፣ የተማሪ ዕድሜ ከክፍል ደረጃው ጋር መጣጣሙ ይረጋገጣል።

​3.2 የሪፖርት አዘገጃጀት (Reporting)
ማጠቃለያ (Aggregation): ሲስተሙ የግል መረጃዎችን በመሰብሰብ ወደ አሃዛዊ መረጃ ይቀይራቸዋል።
አመልካቾች (KPIs): እንደ የተማሪ-መምህር ጥምርታ፣ የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ እና የትምህርት ማቋረጥ መጠን ያሉ ሪፖርቶች ይዘጋጃሉ።
report : ሪፖርቶቹ ለትምህርት ባለድርሻ አካላት ይላካሉ። ይህም መጽሐፍት ወይም መምህራን በብዛት ወደ ሚያስፈልጋቸው ትምህርት ቤቶች ለማሰራጨትና ለመመደብ ይረዳል።

30/09/2026
የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በክልሉ በገጠርና በከተማ  የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ !‎‎ሀረር ፣ መስከረም ...
29/09/2026

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በክልሉ በገጠርና በከተማ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ !
‎
‎ሀረር ፣ መስከረም 19/2019/ዓ.ም የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አርሰላን አብዲ በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙ የትምህርት ቤቶች ግንባታዎች አፈጻጸምና በገጠር ትምህርት ቤቶች ያለው የትምህርት ተሳትፎ ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አደርገዋል።
‎
‎የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ
‎
‎በተለይም በገጠር ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ተሳትፎ ማሳደግና ለትውልድ የሚመጥን ምቹ የመማሪያ አካባቢ መፍጠር የቢሮው ዋነኛ ግብ መሆኑን ጠቁመዋል።
‎
‎አያይዘውም በክልሉ እየተካሄዱ ያሉ አዳዲስ የትምህርት ቤቶች ግንባታዎችና የማስፋፊያ ስራዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና ጥራት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው አረጋግጠዋል።
‎
‎በመስክ ጉብኝቱ ላይ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እና ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ አርሰላን አብዲ ተገኝተዋል።
‎
‎ሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ
‎19/1/2019

Address

Harar

Telephone

+251915736636

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Munib Hay posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Munib Hay:

Shortcuts

Share