Awda Hasab አውደ ሓሳብ

Awda Hasab አውደ ሓሳብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Awda Hasab አውደ ሓሳብ, Digital creator, Harar.

አውደ ሓሳብ፣ 'የሓሳብ መድረክ' ማለት ነው። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትንተና፣ ሓሳብ እና እይታ ይጋራበታል።

Awda Hasab, meaning "Idea Forum," is a space where analysis, thoughts and perspectives are shared on a wide range of topics.

የHachalu Hundessa Foundation የአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሽልማት መሰረዙን በመግለጽ ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ ጠይቋል::ፋውንዴሽንፌኑ ሁል ጊዜ ከተጎጂዎች ጎን በመቆም...
05/07/2025

የHachalu Hundessa Foundation
የአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሽልማት መሰረዙን በመግለጽ ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ ጠይቋል::

ፋውንዴሽንፌኑ ሁል ጊዜ ከተጎጂዎች ጎን በመቆም ሰብአዊ መብት የሚጥሱ እና ኢፍትሃዊ ድርጊት የሚፈጽሙትን ለመታገል ከህዝቡ ጎን እንደሚቆምም አረጋግጧል::

  . . .በዓለም ላይ በሴቶች የተፈፀሙ ጥቃቶች ከባድ መዘዝ አስከትለዋል፤ ታዋቂ የሙዚቃ ሰዎችን እንኳን ድርጊቱን ፈጽመው ሲከሰሱ፣ ዝናቸው፣ ሀብታቸው፣ ክብራቸው እና ታሪካቸው አፈር ድሜ ሲ...
04/07/2025

. . .
በዓለም ላይ በሴቶች የተፈፀሙ ጥቃቶች ከባድ መዘዝ አስከትለዋል፤ ታዋቂ የሙዚቃ ሰዎችን እንኳን ድርጊቱን ፈጽመው ሲከሰሱ፣ ዝናቸው፣ ሀብታቸው፣ ክብራቸው እና ታሪካቸው አፈር ድሜ ሲበላ ደጋግሞ ታይቷል።

በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ከአጥናፍ አጥናፍ ዓለም ቆሞ ያጨበጨበላቸው ስመገናና አርቲስቶች በሴቶች ላይ ጥቃት በመፈፀማቸው ወደኋላ የማይመለስ ውድቀት ደርሶባቸዋል። ጥቂቱ . . . :-

1. ክሪስ ብራውን
የአር ኤንድ ቢ እና ፖፕ ዘፋኝ ክሪስ ብራውን እኤአ በ2009 የወቅቱ የፍቅር ጓደኛው የነበረችው ሪሃና ላይ ከባድ የአካል ጥቃት ፈጽሞ የታሪኩ ጠባሳ ሆኖ አልፏል። ክስተት ሰፊ የመገናኛ ብዙሃን እና የማህበራዊ ሚዲያዎ ሽፋን አግኝቶ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር፤ በተለይ የሪሃና ፎቶዎች ከጥቃቱ በኋላ ይፋ መውጣታቸው በአሜሪካ የፍትህ አካላት ሳይቀር ትልቅ ውዝግብ አስክትሎ ነበር።

ይህ ጥቃት ባስከተለው መዘዝ ክሪስ ብራውን የህዝብ ተቀባይነቱ አፈር ልሷል፤ ጣራ የነካው ዝናው ተከስክሷል። በርካታ የሙዚቃ እና የስፖንሰርሺፕ ውሎች ተሰርዘውበታል። በህግ ፊት ተጠያቂ ሆኖ የማህበረሰብ አገልግሎት ተፈርዶበታል። ምንም እንኳ በሙዚቃ ህይወቱ ቢቀጥልም የፈጸመው ጥቃት ታሪክ እና ዝናው ላይ ዘላቂ ጠባሳ ፈጥሯል።

2. አር ኬሊ
የአር ኤንድ ቢ አፈ ታሪክ እስከመባል ደርሶ የነበረው አርቲስት አር ኬሊ በተለያዩ ጊዜያት በሴቶች የፈጸማቸው ጥቃቶች ይፋ መደረጋቸውን ተከትሎ ምነው እጄንም ምኔንም በቆረጠው እስከማለት አድርሶታል። በተለይ በታዳጊ ሴቶች ላይ የፈጸማቸው የወሲብ ጥቃት፣ የማስፈራራት እና የጋብቻ ወንጀሎች አስደንጋጭ ነበሩ። እኤአ በ2019 "Surviving R. Kelly" ያሚል ርዕስ ዘጋቢ ፊልም ከተለቀቀ በኋላ በርካታ ሴቶች አደባባይ ወጥተው የወሲብ ጥቃት እንደፈጸመባቸው ተናግረዋል። ክሶቹ በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በመገናኛ ብዙሃን ተሰራጭተው የህዝብ ቁጣ አስከትለዋል።

አር ኬሊ እኤአ በ2022 በአሜሪካ ፌዴራል ፍርድ ቤት ተጠያቂ ሆኖ የ30 ዓመታት እስራት ተፈረዶበታል። በዚህም የሙዚቃ ህይወቱ ፈራርሷል፤ የቀድሞ አልበሞቹ ከብዙ የሽያጭ መድረኮች ተወግደዋል፤ ሀብቱ እና ዝናው ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

ይህ ክስተት በሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚፈጸሙ የጾታ ጥቃቶች እና የጥቃት ሰለባዎች ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሯል።

3. ዶ/ር ሉክ
ታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር ዶ/ር ሉክ (ሉካስ ጎትዋልድ) እኤአ በ2014 በፖፕ ንግስቷ ኬሻ የወሲብ እና ስሜታዊ ጥቃት በመፈጸም ተጋልጧል:: ይሁንና ኬሻ ከእሱ ጋር የነበራትን የሙዚቃ ውል ለመቅድ የረጅም ጊዜ የህግ ትግል ጠይቋታል::

ይሁንና የህዝብ ቁጣ በፈጠረው ተፅእኖ ሌሎች ሴቶችም ተመሳሳይ ጥቃት እንደፈጸመባቸው አጋልጠዋል። ይህም የሚል ዝነኛ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ አስከትሏል፤ የዶ/ር ሉክ ዝና በእጅጉ ተጎድቷል፤ በርካታ አርቲስቶች ከእሱ ጋር መስራት አቁመዋል። ምንም እንኳ በሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ መስራቱን ቢቀጥልም ክብሩ፣ ዝናውና ሀብቱ ተሽመድምዷል። በኢንዱስትሪው የሰቀለው ታሪክ አፈር ለብሷል።

የሮክ አርቲስት ማሪሊን ማንሰን (ብሪያን ዋርነር)፣ የሂፕ ሆፕ አርቲስት ###ተንታሲዮን (ጃህሴ ኦኒፍሮይ) እና ሌሎችም በርካታ የሙዚቃ ኢንዱስትሪው ገናኖችና ዝነኞች በሴቶች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ለውድቀት ተዳርገዋል።
በአገራችን የተባለ አርቲስት (ታዋቂ ዘፋኝ) ፍቅረኛው (ሚስቱ) በመግደል ተጠርጥሮ በእስር መቆየቱ ይታወቃል:: "ገድሏል ወይስ አልገደለም?" የሚል አከራካሪ ጉዳይ በህግ ምላሽ ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም አቃቤ ህግ በቀጠሮ ቀኑ ክስ ባለመመስረቱ በህጉ መሰረት በዋስ ተለቋል:: ምንም እንኳን በዋስ የተለቀቀበት አግባብ የህግ ክፍተት እንደሌለው የሚገልጹ ህግ አዋቂዎች ቢኖሩም አቃቤ አንዱአለም በዋስ እንዲወጣ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ ግን ምርመራ የሚያስፈልገው ነው::

ይሁንና #ቀነኒ ራሷን አጠፋች ቢባል እንኳን መንስኤው ሲፈጽምባት የነበረው አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት ለመሆኑ የቅርብ ጓደኞቻቸው ሳይቀሩ ደጋግመው ገልጸዋል:: በፈጸመባት አካላዊ ጥቃቶች ሰውነቷ ላይ የተፈጠሩ ቁስሎችና ብልዞችም አሁንም ድረስ በፎቶ እና በቪድዮ እየተጋሩ ነው:: አንዱአለምም ቢሆን እስከ አሁን ድረስ አካላዊ ጥቃት "አልፈጸምኩባትም" የሚል ማስተባበያ አልሰጠም::

ስለሆነም ቢያንስ በፈጸመባት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሊወገዝ፣ ሊከሰስ፣ ክብሩና ታሪኩ ሊገፈፍ ይገባ ነበር። ይሁንና ጭራሽ በግድያ በመጠርጠሩ 'የጎደፈ' ስሙን ለማደስ በሚል ስሌት በባሌም በቦሌም 'ሎቢ' ተደርጎለት ለሽልማት በቅቷል:: ሽልማቱ ለፍትህ፣ ለርትእና ለእኩልነት ሲታገል ዛሬም ድረስ ምላሽ ባላገኘ መንገድ በተገደለው ስም የተዘጋጀ መሆኑ ደግሞ ብዙዎችን አሳዝኗል፤ አስቆጥቷልም። በመሆኑም ሽልማቱን የሰጠው Hachalu Hundessa Foundation ከተቋቄመለት ዓላማ በተቃራኒ ዘላቂ አሉታዊ ውጤቶች እንዳያስከትልበት ጭምር ቆም ብሎ ሊያስብበትና ስህተቱን ማረም ይጠበቅበታል።


 #ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም!". . . አንዳንድ ሰው የገዛ ቤቱን መቃሚያ ሊያደርግ ይችላል። ሌላ ሰው ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ የቤቱን ንፅህና ሊጠብቅ ይችላል። አንዳንድ 'ኮሜንት መስጫው...
09/06/2025

#ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም!

". . . አንዳንድ ሰው የገዛ ቤቱን መቃሚያ ሊያደርግ ይችላል። ሌላ ሰው ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ የቤቱን ንፅህና ሊጠብቅ ይችላል። አንዳንድ 'ኮሜንት መስጫውን ክፈት' የሚሉ ሰዎች የእኔ የፌስቡክ ገጽ ላይ ስለ ብሔርተኝነት፣ የጥላቻ ንግግር ማውራት የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው፤ እኔም አልፈልግም" ያሉት የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ናቸው። ፕሬዝዳንቱ ሙስጠፌ ኡመር ከቢቢሲ ሶማልኛና አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋዊ የፌስቡክ አካውንታቸው ለህዝብ አስተያየት ዝግ የሆነበት ምክንያት ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት መልስ የተቀነጨበ ነው። (በአብዛኛው እርስ በእርሱ የተጣረሰው ሙሉ ቃለ ምልልሳቸው https://www.facebook.com/share/p/1Hp8V2SP3b/ ላይ ማንበብ ትችላላችሁ)

ፕረዝዳንቱ አቶ ሙስጠፌ ይግረማችሁ ብለው " . . . እኔ የምፈልገው በዕይታ ከእኔ የሚለይ ነገር ያለው ሰው ፌስቡክ አለው፤ በራሱ ፌስቡክ ይጻፍ። ማንም አይከለክለውም። ስለዚህ ከሚዲያ ነጻነት ጋር የሚቃረን ነገር የለውም። ግን እኔ የገጹን ሥነ ምግባር እየጠበቅኩ ነው" በማለት ያክላሉ።

ይሁንና አቶ ሙስጠፌ ያልተረዱት እውነት አለ። የፌስቡክ ገጻቸው እንደ የማንም ግለሰብ አድርገው መውሰዳቸው ስህተት ነው። የህዝብ ተመራጭ እንደመሆናቸው መጠን ህዝብም በሚደርሳቸው መንገድ ሀሳቡን የመስጠት መብት እንዳለው መረዳት ይጠበቅባቸዋል።

ፌስቡክም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ለመንግስት መሪዎች ከሚመሩት ህዝብ ጋር በቀጥታ ለመገናኘት እና ሀሳብ ለመለዋወጥ ጠቃሚ መድረክ ናቸው። ለአብነት ህዝብ በፌስቡክ የሚሰጣቸው አስተያየቶች ጠቀሜታቸው ዘርፈ ብዙ ነው። ለአብነትም:-

👉 👉 የህዝብ አስተያየት መረዳት/መለካት፡-
የፌስቡክ አስተያየቶች መሪዎች የህዝብ ስሜትን፣ ፍላጎቶችን፣ እና ቅሬታዎችን ለመረዳት ቀጥተኛ መንገድ ናቸው። ይህም ፕሬዝዳንቱ ህዝቡን የሚያሳስቡ ጉዳዮችን አውቀው ትኩረት ለመስጠት ያስችላቸዋል።

👉 የፖሊሲ ግብአት ማግኘት: -
የክልሉ ነዋሪዎች በሚሰጠት አስተያየት አማካኝነት በተለያዩ ፖሊሲዎች ላይ ያላቸውን አመለካከት፣ ሃሳቦች እና ገንቢ ትችቶች ሊያቀርቡበት ይችላሉ። ይህ ለመሪው የፖሊሲ ውሳኔዎችን ከማድረግ በፊት የህዝብን ድምጽ እንዲያካትት ያስችለዋል።

👉 ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማሳደግ:- የህዝብ አስተያየቶች በመንግስት እና በህዝብ እና በክልሉ መካከል ያለውን ግልጽነት ያጠናክራል። ለህዝብ ጥያቄዎች ተጠያቂ መሆናቸውንም ያሳያል።

👉 ቀጥተኛ ግንኙነት እና እምነት መፍጠር:- ፌስቡክ መሪው ከህዝቡ ጋር በቀጥታ እንዲነጋገር ያስችለዋል። ይህ ደግሞ በመሪው እና በዜጎች መካከል መተማመን እና ወዳጅነት ይገነባል።

👉 የፖለቲካዊ ድጋፍ ማሰባሰብ: -
በምርጫ ወቅት የህዝብ አስተያየቶች ለፖለቲካዊ ዘመቻዎች እና ለወደፊት ምርጫዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ ያግዛሉ።

በአጠቃላይ የፌስቡክ አስተያየቶች ለክልል ፕሬዝዳንት ወይም ለመንግስት ባለስልጣን ከህዝቡ ጋር የተሻለ ግንኙነት እንዲፈጥር፣ የህዝብን ድምጽ እንዲሰማ፣ የህዝብ አስተያየት ለመገምገም፣ የፖለቲካ ስትራቴጂን ለማዳበር እና በተሻለ ቁመና ክልሉን/ተቋሙን ለመምራት መሳሪያ ይሆነዋል።

ይህ ሲባል ግን ሁል ጊዜ ሁሉም ሰው ጠቃሚ አስተያየቶችን ይሰጣል ማለት አይደለም። ለመቆጣጠር ፈተና የሚሆኑ አሉታዊ አስተያየቶችም ሊሰጡ ይችላሉ። እሳቸው እንዳሉት የጥላቻና የጽንፈኛ አስተያየቶችም ሊሰጡ ይችላሉ። ይሁንና ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም:: ከጉዳቱ ይልቅ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ የፌስቡክ አካውንታቸውን ለህዝብ አስተያየት ዝግ ማድረጋቸው ሊታረም የሚገባ ትልቅ ጉድለት ነው።

ኤሎን ማስክ $424 ቢልዮን አካባቢ ሀብት እንዳለው መረጃዎች ያመለክታሉ:: አገር ካልሆነ በስተቀር በግለሰብ ደረጃ የሚፎካከረው የለም:: ይሁንና ትዊተርን (የአሁኑ Xን) በ $44 ቢሊዮን ዶ...
08/06/2025

ኤሎን ማስክ $424 ቢልዮን አካባቢ ሀብት እንዳለው መረጃዎች ያመለክታሉ:: አገር ካልሆነ በስተቀር በግለሰብ ደረጃ የሚፎካከረው የለም::

ይሁንና ትዊተርን (የአሁኑ Xን) በ $44 ቢሊዮን ዶላር ሲገዛ ይሄን ያህል ገንዘብ በካሽ አልነበረውም፤ ይሄን ያህል ገንዘብ በካሽ (ተቀማጭ) የሚኖራቸው ጥቂት አገራት ብቻ ናቸው።

በመሆኑም ኩባንያውን (ቴስላ) እንደ ዋስትና በማስያዝ በባንክ ብድር ነበር የግዥ ገንዘቡን የከፈለው። በአሁኑ ወቅት ከሞገደኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር በፈጠረው ሰጣ ገባ የቴስላ አክሲዮን ዋጋ እየቀነሰ ይገኛል። ይህም ከባንክ በወሰደው 44 ቢሊዮን ብድር ቀጥተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ጀምሯል። የቴስላ ዋጋ በቀነሰ ቁጥር ላይ የሚገጥመው ጫና ይጨምራል።

ለዚህም ነው ሰሞኑን በፎክስ ኒውስ ላይ ቀርቦ ለማልቀስ ተቃርቦ ከእንባው ጋር ሲታገል የነበረው።

እናም “የዓለም ቁጥር 1 ሀብታም” መሆን ገንዘብ ላይ እንደመዋኘት ማለት አይደለም። ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች እንደ ዋስትና መጠቀም ትችላለህ ማለት ነው። ችግሩ የሚጀምረው እነዚያ ንብረቶች ዋጋቸውን ሲቀንስ/ሲያጡ ነው። ለዚህም ነው የምድራችን ሀብታሙ ሰው በጣም ከባድ ጊዜ እያሳለፈ ያለው።

እናም አንዳአንዴ በጣም ሀብታሞች ከድሆች የከፉ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል:: ለዚህም ነው "ሀብታም ሰዎች ሀብታም ችግሮች አሏቸው" የሚባለው። Rich People Have Rich Problems❗😥

 #አይበገሬውባለፉት 15 ዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአቶ ታዬ ደንደኣን ያህል ጭቆናና ግፍን የተቃወመ የለም፤ አቶ ታዬ የሰላማዊ ትግል አርማ ነው፤ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምልክትና መታወቂ...
02/06/2025

#አይበገሬው

ባለፉት 15 ዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአቶ ታዬ ደንደኣን ያህል ጭቆናና ግፍን የተቃወመ የለም፤ አቶ ታዬ የሰላማዊ ትግል አርማ ነው፤ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምልክትና መታወቂያ ነው። የፍትህና የእውነት መገለጫ ነው።


ሀሳቡን በድፍረት ይገልጻል፤ ለተጨቆኑ ድምጽ ይሆናል። የህብረተሰቡን ችግሮች፣ የመንግሥት በደሎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በግልጽ ያስተጋባል። በህዝብ ልብ ውስጥ ተስፋና ተቃውሞ ያነቃቃል።

አቶ ታዬ የዴሞክራሲ መርሆዎችን በተግባር ያሳየ ነው። የእኩልነትና የሰብአዊ ክብር ታጋይ ነው። እሱ በተጋፈጠባቸው ፈታኝ ሁኔታዎች ተደጋጋሚ እስራትና ማስፈራራት አስተናግዷል። በምንም ለማንም ሳይበገር ተስፋ ባለመቁረጥ በጽናት ቆሟል። የእሱ ጽናትና ቁርጠኝነት ለብዙዎች መነሳሳት ፈጥሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለጤና ባለሙያዎች ድምጽ በመሆንና የመንግስትን ህጸጾች በማጋለጥ የፈጠረው ተጽእኖም የሚጠቀ ነው። ይሁንና አንደበቱን ለመዝጋት ሲባል ከዚህ ቀደም ነጻ በተባለባቸው ክሶች ድጋሚ ዛሬ ለእስር ተዳርጓል።

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awda Hasab አውደ ሓሳብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share