11/03/2026
💡
ጎግል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና ሱማልኛን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ቋንቋዎች የሰው ሠራሽ አስተውሎት የፍለጋ ማጠቃለያ (AI Overviews) አገልግሎቱ ላይ ማካተቱን አስታወቀ::
አገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በSearch ማድረጊያው ላይ ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች በAI የተዘጋጀ አጭርና ግልጽ ማጠቃለያ ማግኘት የሚችሉበት ነው።
ጥያቄዎችን በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን በድምፅ እና በምስል (Google Lens) ላይ ጭምር ማቅረብ ይቻላል።
እንግሊዝኛ ለማይችሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ውስብስብ መረጃዎችን በራሳቸው ቋንቋ የሚያስችል በመሆኑ ጠቀሜታው የላቀ ነው።
#አጠቃቀም
ለምሳሌ አማርኛ አጠቃቀም:-
ብራውዘር (Browser) መክፈት፣ በመቀጠል ከስር ከተዘረዘሩት ቋንቋዎች "አማርኛ" የሚለውን መምረጥ፣ Search ማድረጊያ ላይ የምንፈልገው ጥያቄ በመጻፍ ፍለጋ ማስቀጠል በመጨረሻም "የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሁኔታ" የሚለውን መጫን ነው። መልሱን በአማርኛ ይሰጠናል።
ከስር ባለው መጠየቂያ የፈለግነው ጥያቄ ብናቀርብለትም በአማርኛ መልስ ይሰጠናል። መጀመሪያ የጠየቅነው በኦሮምኛ ወይም በሶማልኛ ቋንቋ ከሆነም ሂደቱ ተመሳሳይ ነው። ትግርኛ እና አፋርኛ ወይም ሌሎች ቋንቋዎች ከመረጥን ግን መፈለጊያው ላይ "የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሁኔታ" የሚለው አይኖርም።
የአጠቃቀም መግለጫ ከታች ተያይዟል።🙋😍