HU FM 91.5 RADIO

HU FM 91.5 RADIO Haramaya University Community Radio Station

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኩርፋ ጨሌ ፣ በግራዋ ፣ በመዩ ሙሉቄና በቁንቢ ወረዳዎች በኤልኒኖ ምክንያት የዝናብ እጥረት በመከሰቱ በግብርና ስራቸው ላይ ችግር መፍጠሩን ነዋሪዎች ገለጹበምስራቅ ሀረ...
06/09/2026

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኩርፋ ጨሌ ፣ በግራዋ ፣ በመዩ ሙሉቄና በቁንቢ ወረዳዎች በኤልኒኖ ምክንያት የዝናብ እጥረት በመከሰቱ በግብርና ስራቸው ላይ ችግር መፍጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ

በምስራቅ ሀረርጌ ቆላማ አካባቢዎች የኤልኒኖ ተጽዕኖ በተለይ ዝናብን ጠብቀው የግብርና ስራዎችን የሚያከናውኑ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን የአካባቢዎቹ ነዋሪዎችና አመራሮች ተናግረዋል፡፡

የቁንቢ ወረዳ ሞጆ ለገ ሆሜ ቀበሌ ነዋሪ ወ/ሮ ጀነቲ ሀራድ እንደተናገሩት የቀበሌያቸው ነዋሪ አርሶና አርብቶ አደሮች የዘሩት በቆሎና ማሽላ ዝናብ ባለመዝነቡ ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ነዋሪው ለችግር መዳረጉን ተናግረዋል፡፡

አርሶና አደር ጀነቲ በሞጆ ወንዝ አካባቢ የሚኖሩና ውሀውን የሚስቡበት ሞተር የሌላችው አርሶ አደሮች ከድርቁ አደጋ ማምለጥ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደር ኡርጌ መሃመድ ፣ ጃፈር መሃመድ ፣ መሃመድ ጀማል መሃመድ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ሐ.ዩ. ኤፍ ኤም 91.5 እንደተናገሩት በአካባቢያቸው የዝናብ ዕጥረት የበቆሎና ማሽላ ሰብሎችን ሲያወድም ድንች እና ሌሎች አትክልቶች አፈር ውሰጥ በተከሰቱ ነፍሳት በመውደማቸው ለምግብ እጥረት እንደገጠማቸውና ይህንን ችግር ለማሳለፍ የቀን ስራ ፍለጋ ወደ ግራዋ ከተማ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመዩ ሙሉቄ የሞጆ ወልደያ ነዋሪ አርሶ አደር ሃስን ኡመር በበኩሉ ከዚህ ቀደም የስንዴ ምርት ይመረትባቸው የነበሩ ሰፋፊ የእርሻ ማሳዎች በዝናብ እጥረት የተነሳ ጾም ማደራቸውን ገልጸዋል፡፡

በቁንቢ ወረዳ የከራ ባልጪ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊዪ ዱሪ አካባቢው በተደጋጋሚ በድርቅ ከመመታቱ ጋር ተያይዞ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በየጊዜው ድጋፍና ክትትል በማድረግ አርብቶ አደሮችን በሞጆ ወንዝ ዳርቻ በመውሰድ ወደ ግብርና ስራ እንዲገቡ ከስልጠና እሰከ ግብርና ግብአቶች በመስጠት አካባቢውን ምርታማ ለማድረግ ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው ኤልኒኖ ባስከተለው የዝናብ እጥረት በዚህ መኅር ወቅት የተላከላቸውን ምርጥ የማሽላ ዘር በ20 ሄክታር ላይ በክላስተር ቢዘሩም ድርቁ ማሳ ላይ ሙሉ ለሙሉ አውድሞታል ብለዋል፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር ዶክተር አብዱለጢፍ አህመድ በበኩላችው በሞጆ ስምጥ ሸለቆ የተሰራውን ውጤታማ የግብርና ስራ በደጋማው የወረዳው አካባቢዎች ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ እንደነበር ጠቁመው በከራ ባልጪ 20 ሔክታር ላይ የተዘራው ማሽላ የኤልኒኖ ተጽዕኖ ሙሉ ለሙሉ ወድሞ በማየታቸው ማዘናቸውን ገልጸው የአካባቢውን ነዋሪዎች ችግር ለማቃለል በቀጣይ የሚዘንበውን ዝናብ በመጠቀም ደራሽ የሆኑ ለሰውና እንስሳት የሚሆኑ እንደ ስኳር ድንች ፣ ካውፒናና ሌሎች የአደንጓሬ ሰብሎችን ከባለድርሻ አባላት ጋር በመሆን ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የቁንቢ ወረዳ ምክትል አስተዳዳርና የወረዳው የአርብቶና አርሶ አደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልበሃሪ ሲራጅ የኤልኒኖ ቀውስ በአካባቢያቸው ወንዞችና የውሀ ጉድጓዶችን መጠን በመቀነሱ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ንጹህ የመጠጥ ውሀ ማግኘት ስለማይቻል በሰውና በከብቶች ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያሰከትል ስለሚችል ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የኤልኒኖ ተጽእኖ ጠንካራ ሊሆን እንደሚችል ትንበያ ስላለ ችግሩን ለማቃለል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ አቶ አብዱልበሃሪ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ሲሳይ ዋቄ

 በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህር የሆነው ሀብታሙ ለገሰ ያለውን እውቀት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በተከታታይነት በማቅረብ ከ2ኛ ደረጃ እስከ ድህረ ምረቃ ድረስ ላሉ ተ...
06/09/2026



በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህር የሆነው ሀብታሙ ለገሰ ያለውን እውቀት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በተከታታይነት በማቅረብ ከ2ኛ ደረጃ እስከ ድህረ ምረቃ ድረስ ላሉ ተማሪዎች የኢኮኖሚክስ ትምህርት ሌክቸሮችንና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ማብራሪያ በቪዲዮ እየሰራ በዚህ ሊንክ (https://youtube.com/?si=Zc3j93sEaChfRlgv
) እና በመደበኛ ነባር የሚዲያ ዘርፎች በማቅረብ እገዛ እየደረገ ነው።

ይህም ተማሪዎችን ለማገዝ የሚያደርገውን አስተዋኦ እና ያለውን ዕውቀት ለብዙዎች ለማካፈል የሚያደርገውን ጥረት በመመልከት በ"የቅን ልቦች" የሽልማት ውድድር በኢኮኖሚክስና ፋይናንስ ዘርፍ ዕጩ ሆኖ ቀርቧልና በተግባር የሚያደርገውን መልካምነት በመደገፍ ድምፅ እንስጠው።

መልካምነት እናበረታታ!
በቀጣዩ ሊንክ ተጠቅመን ለወንድማችን ድምፅ እንስጠው!
https://yekinlibochaward.org/nominees/habtamu-legese

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሰጥ የነበረው የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በስኬት ተጠናቀቀበታዝማ የውስጥ ደዌና የቀዶ ህክምና ልዩ ማእከል የልብ ቀዶ...
05/09/2026

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲሰጥ የነበረው የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት በስኬት ተጠናቀቀ

በታዝማ የውስጥ ደዌና የቀዶ ህክምና ልዩ ማእከል የልብ ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሀኑ ኃይለማሪያም እንደተናገሩት ለመጀመሪያ ጊዜ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ11 ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎቱን በስኬት መስጠት ችለናል ብለዋል።

ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሉ ለህክምናው ያደረገው አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት የአገልግሎቱ ውጤታማነት ላይ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።

ዶክተር ብርሀኑ አክለውም ታዝማ የውስጥ ደዌና የቀዶ ህክምና ልዩ ማእከል ይህን አገልግሎት በኢትዮጵያ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ግብ እውን እንዲሆን ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል በዚህም በስድስት ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ውስጥ አገልግሎት መስጠቱንና ወደፊትም አገልግሎቱን እንደሚያስፋፉ ገልፀዋል።

ህክምናውን ያገኙት በህይወት ፋና ሆስፒታል ውስጥ ቀጣይ የክትትል ሂደታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ሁሉም በተሻለ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ብለዋል ።

የህክምናው ተጠቃሚ ህፃናት ወላጆች በሰጡት አስተያየት ይህን አጋጣሚ እንድናገኝ እና ልጆቻችን ህክምናው ተደርጎላቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ ሆነው በማየታችን ደስታ ሆነናል ብለዋል።

ዘጋቢ :- ታደለ ጥላሁን
ፎቶ ግራፈር ፡- በሐይሉ ግርማ
ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲብ የህዝብና ዕለም አቀፍ ግንኙነት

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰ አገልግሎት ለአካባቢው ማህበረሰብ በመስጠት ከዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ ሆኖ መመረጡ ተገለፀሸገር ኤፍ ኤም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ  የተሰራ ጥናትን መሰረት አድር...
05/09/2026

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰ አገልግሎት ለአካባቢው ማህበረሰብ በመስጠት ከዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ ሆኖ መመረጡ ተገለፀ

ሸገር ኤፍ ኤም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተሰራ ጥናትን መሰረት አድርጎ እንደዘገበው ሐረማያ ፣ አዲግራት እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ እርካታ ከተመዘገበባቸው መካከል ቀዳሚዎቹ መሆናቸው ተገልጿል።

ጥናቱ የቀረበው የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ ምርምር ፣ የአመራር ልማት መርሃ ግብር እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2018 አፈጻጸም ዙሪያ በተዘጋጀው ውይይት ላይ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ጥናቱ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ አጥኚዎች መሰራቱንና በ2017 እና በ2018 በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚሰጠው አገልግሎት መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ማህበረሰቡ ምን ያህል ደስተኛ ናቸው የሚለውን ለማወቅ የተሰራ ነው፡፡

በጥናቱ 47ቱም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተካተቱ ሲሆን ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፣ ከ16 ሺህ በላይ መምህራን፣ ከ4 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሰራተኞች እና 4 ሺህ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች (በአጠቃላይ 61 ሺህ 431 ሰዎች) በጥናቱ ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን በራሳቸው ውሳኔና ፍላጎት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአልጎርይዝም ተመርጦ በሚቀርብላቸው ይዘት እየተመሩ መ...
01/09/2026

የወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን በራሳቸው ውሳኔና ፍላጎት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአልጎርይዝም ተመርጦ በሚቀርብላቸው ይዘት እየተመሩ መሆናቸው ውስብስብ ማህበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ተጽዕኖዎችን እያስከተለ መሆኑ ተገለጸ።

«ከስክሪን ቀንሰን መጽሐፍ እንግለጥ» በሚል መሪ ቃል ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ አዘጋጅነት የንባብ ፌስቲቫል ተካሂዷል።

የንባብ ፌስቲቫሉ በከተማዋ በሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞች በተዘረጉ 72 የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት ለአምስት ተከታታይ ቀናት መካሄዱ ይታወሳል።

መርሃ-ግብሩ ወጣቶች በስክሪንና በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ በማመጣጠን፣ ትኩረታቸውን ወደ ጥልቅ ንባብ፣ ፈጠራና ሂሳዊ አስተሳሰብ እንዲመልሱ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ደህናሰው ሽመልስ እንዳሉት፣ ከአካላዊው ማህበረሰብ ባልተናነሰ የበይነ-መረብ ማህበረሰብ በስፋት በተመሰረተበት በዚህ ዘመን፣ የወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ስማርት ፎን ያለው ሁሉ የመረጃ አሰራጭ በሆነበት የዲጂታል ዘመን፣ ሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች በቀላሉ ለህዝብ እንዲደርሱ መደረጉ ለሚያስከትላቸው ጉዳቶች የመረጃ አሰራጮችን ተጠያቂ የሚያደርግ በቂ አሰራር አለመኖሩ ችግሩን እያባባሰው መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኃላፊነት የሚሰማውን ዲጂታል ዜጋ ለመፍጠር፣ የወጣቶችን የሚዲያ ንቃተ-ህሊና በትምህርትና በስልጠና ማሳደግ፣ እንዲሁም በፖሊሲ የተደገፈ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ መዘርጋት እንደሚገባ መምህሩ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በአንዳንድ ባደጉ ሀገራት በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ይተገበር የነበረው የመማርና የማስተማር ሥርዓት ወደ ቀድሞው የመማር ሥርዓት እየተመለሰ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህም ተማሪዎች በአልጎርይዝም ተመርጦ በሚቀርብላቸው ይዘት በመጠመዳቸው የማሰብ፣ የመማርና ትኩረትን የማስቀጠል አቅማቸው እየተዳከመ መምጣቱ ከሚያበረክቱት ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ህጻናትና ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ረጅም ሰዓታትን ማሳለፋቸው፣ በትምህርታቸው ላይ ያላቸውን ትኩረት ከማሳነሱ ባለፈ የእንቅልፍ ሥርዓታቸውን ሊያውክና የማሰብና የመማር አቅማቸውን ሊያሳንስ እንደሚችል አመልክተዋል።

በመሆኑም ህጻናት በማህበራዊ ሚዲያ የሚያሳልፉበትን ጊዜ በአካል በሚከናወኑ ጨዋታዎች፣ በንባብና በሌሎች ጠቃሚ ተግባራት ላይ እንዲያሳልፉ ወላጆችና ማህበረሰቡ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

አሁን ላይ ዋነኛው ችግር ቴክኖሎጂው ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂው በሚጠቀሙት ሰዎች እጅ የሚወሰደው አጠቃቀምና አቅጣጫ መሆኑን ያመለከቱት መምህር ደህናሰው፣ ወጣቶች በአልጎርይዝም ከመመራት ይልቅ ማህበራዊ ሚዲያን በራሳቸው ውሳኔ፣ ፍላጎትና እውቀት መጠቀም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን፣ የሥራና የፈጠራ እድሎችን ለማስፋት እንዲሁም ለሀገራዊ ጥቅም በኃላፊነትና በእውቀት እንዲጠቀሙበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፤ አሸናፊ ከበደ
ነሀሴ 26/12/2018 ዓ.ም

31/08/2026
31/08/2026
ለተማሪዎች የሚሰጠው የሣይንስ ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ኢንጅነሪንግና ሒሳብ ‘STEM’ ትምህርት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ​የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎ...
31/08/2026

ለተማሪዎች የሚሰጠው የሣይንስ ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ኢንጅነሪንግና ሒሳብ ‘STEM’ ትምህርት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ

​የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ (STEM) ደረጃ-II የክረምት ሥልጠና ፕሮግራም ተጠናቀቀ።

​የዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ ተሳትፎ እና የኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ከተፈጥሮ እና ኮምፒዩቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ሥልጠና ላይ ከሰባት ትምህርት ቤቶች የመጡ 59 ተማሪዎች ሥልጠናቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል፡፡

​በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር አቶ ከማል ቃሲም በሥልጠናው ማጠቃለያ ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም የ STEM ሥልጠና ካለው ከፍተኛ ጠቀሜታ አኳያ በቀጣይም በትኩረት የሚሠራበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

​የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ዋቅጅራ በበኩላቸው ሀገር ሊቀየር የሚችለው በእውቀት በመሆኑ ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋጽዖ ላላቸው የትምህርት ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲም በሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎችን ለማብቃት እየሠራ ያለው ሥራ የሚበረታታና የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

​የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የ STEM ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ሔኖክ ደሳለኝ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታልና ዕውቀት ተኮር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር በምትጥርበት በዚህ ወቅት እንደ 'Digital Ethiopia 2025' ያሉ የሀገሪቱ የዲጂታል ልማት አጀንዳዎች የዲጂታል ክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እውቀት፣ ፈጠራ እና የሰው ኃይል ልማትን አጥብቀው የሚሹ ናቸው፡፡

ስለሆነም ከልጅነት ጀምሮ ጠንካራ የ STEM ትምህርት መስጠት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

​ከክረምት ሥልጠና ተሳታፊዎች መካከል ተማሪ ሀዊ ዳቢ እና ተማሪ ኢብራሂም አብዱጀባር ከሐረማያና ከአዴሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጡ ሲሆን በቆይታቸው በተግባር የተደገፈ እውቀት መቅሰማቸው የሳይንስ ትምህርትን በአግባቡ እንዲረዱ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

​በመጨረሻም ለሥልጠናው ተሳታፊዎች ከዕለቱ የክብር እንግዶች የሥልጠና ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ይበልጣል ግዛው
ፎቶግራፈር፦ ቴዎድሮስ ሊሻን

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HU FM 91.5 RADIO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to HU FM 91.5 RADIO:

Shortcuts

Share

Category