14/11/2025
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአጭር ጊዜ በዓሉን ለማስተናገድ ያከናወነው ቅድመ ዝግጅት የሚደነቅ ነው :- ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድ
****
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን ለማስተናገድ በአጭር ግዜ ያከናወነው ቅድመ ዝግጅት የሚደነቅ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድ ገልፀዋል።
ምክትል አፈ ጉባኤዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአጭር ጊዜ በዓሉን ለማስተናገድ ያከናወነው ቅድመ ዝግጅት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ቀሪ ስራዎች በቀሩት ጊዜያት እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ መቀመጡንና አብዛኛዎቹ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ተናግረው በዓሉን የክልሉን ሁለንተናዊ ገጽታ ለማስተዋወቅ መጠቀም ይገባል ሲሉም ምክትል አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ትግሉ መለሰ በበኩላቸው ክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጀመሩ መሰረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ ያደረገው ዝግጅት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በዓሉን በሚመጥን መልኩ የተገነቡ የመንገድ፣ የስቴዲየም፣ የሆቴሎችና የሁነት ማሳያ ፕሮጀክቶችና መሰረተ ልማቶችን በአጭር ጊዜ በጥራት ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በአሉ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በሚያንፀባርቅ መልኩ እንደሚከበር የገለፁት ደግሞ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ ናቸው ።
በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውን ገልፀው በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በሰላምና ፀጥታ፣ በሎጂስቲክ እና መስተንግዶ ስራዎች መከናወናቸውንም አብራርተዋል።
ዘጋቢ :- ይድነቃቸው ጌታቸው
05/03/18
ተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።
ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/
ዩቲዩብ :
https://www.youtube.com/
ቴሌግራም:
https://t.me/hararimassmediaagency