
12/05/2025
ለመላዉ የክልላችን ነዋሪዎች እንኳን ደስ አለን!!
ሀረር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ከፍተኛ ሊግ አደገ።
አዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ዉድድር ላይ ተሳታፊ የነበረዉ የከተማችን ብቸኛ ክለብ አስደናቂ ብቃት በማሳየት የምድቡ መሪ በመሆን ለጥሎ ማለፍ ዉድድር ማለፍ በማቻሉ ምክኒያት ወደ ከፍተኛ ሊግ ማለፉን አረጋግጧል።
ይህ አኩሪ ድል እንዲመዘገብ ላደረጋችሁ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች በሐረሪ ክልል መንግስት ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
የሀረር የማንሰራራት ዘመን አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል !!