Awee

Awee Egziyabiherin terahuugn ba hazene gizee

13/03/2026
በምልጃዋ ያመኑትን ሁሉ ሊምርላት ቃል ኪዳን ሰጣትነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤልም የዘለዓለም ድንግልናዋን በትንቢት መጽሐፉ ምዕራፍ 44÷1 ሲናገር “ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መ...
25/12/2025

በምልጃዋ ያመኑትን ሁሉ ሊምርላት ቃል ኪዳን ሰጣት

ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤልም የዘለዓለም ድንግልናዋን በትንቢት መጽሐፉ ምዕራፍ 44÷1 ሲናገር “ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፣ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፤” ብሎአል። የተዘጋ የመቅደስ በር የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። “ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤” የሚለው ኃይለ ቃል በድንግልና ጸንታ እስከ ዘለዓለሙ እንደምትኖር ይነግረናል። “ሰው አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል” ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ፣ በድንግልና የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ በመሆኑ፣ ከርሷ በተዋህዶ ሰው የሆነ የባህርይ አምላክ እንጂ ዕሩቅ ብእሲ አይወለድምና በድንግልና እንደጸናች ትኖራለች ማለቱ ነው።

“እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፤” ይላል። ዮሐንስ 3÷17፣ 1ኛ ዮሐንስ 4÷10። ይህን መውደድ ይህን ፍቅር የገለጸው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሕቱም ድንግልና በመወለድ ነው። የእመቤታችን ድንግልና በሦስት ወገን ነው፤ በሥጋዋ÷ በነፍሷና በልቡናዋ ነው። ይህ ድንግልና የዘለዓለም ድንግልና ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤” ብሎአል። ኢሳይያስ 7÷14።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመጽነሷ በፊት፣ በጸነሰችም ጊዜ፣ ከጸነሰችም በኋላ ድንግልናዋ የጸና ነው፤ ከመውለዷ በፊት፣ በወለደችም ጊዜ፣ ከወለደችም በኋላ ኅትምት በድንግልና ናት። የውዳሴ ማርያም አንድምታ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ያላትን አብራርቶ ይነግረናል፡፡ እመቤታችን መልአኩ ሲያበስራት “ወንድ ሳላውቅ ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል?” የሚል ጥያቄ አንስታ ነበር፡፡ ይህን ያለችው ክብር ይግባትና የወንድ ሀሳብ በአእምሮዋ ፈጽሞ ተመላልሶ ስለማያውቅ ነው፡፡ ሌሎች ሴቶች ስለወንድ ከመናገርና በሕጋዊ ሩካቤ ከመገናኘት ቢታቀቡ ከማሰብ ግን አይነጹም፡፡ እምቤታችን ግን ከመናገር ከማድረግ ከማሰብ ንጽህት ናት፡፡ ከዚህች ቅድስት ድንግል ጋርም በመቃብሩ ስፍራ በጎልጎታ ተደፍታ ስትለምነው በምልጃዋ ያመኑትን ሁሉ ሊምርላት ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡

በሥላሴ አኗኗር ወልድ ለአብ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ እንደሆነ ሁሉ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያምም ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጇ ነው። በጳጳስ ወንበር ቄስ፣ በንጉሥ ዙፋን ራስ ደፍሮ እንደማይቀመጥ ሁሉ በአምላክ ዙፋን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ማን ያድራል? ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለነቢዩ ለሕዝቅኤል አስቀድሞ የነገረው። ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃ 4÷12 “እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፣ የተዘጋ ምንጭ፣ የታተመ ፈሳሽ ናት፤” ብሎአል። እንደተቆለፈች አምላክ ብቻ አድሮባት የወጣባት ገነት፣ እንደተዘጋች የዘለዓለምን ሕይወት ክርስቶስን ያመነጨች፣ እንደታተመች የሕይወትን ውኃ ክርስቶስን በአራቱም ማዕዝን አፍስሳ የተጠሙ ነፍሳትን ያረካች፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት።

07/12/2025

This version of Facebook uses less data and works in all network conditions.

07/12/2025

ይህንን የማኅበረ ቅዱሳን መቱ ማዕከል ገጽ ካለበት ወደ 15000 ብናሳድግ ለቤተክርስቲያን ይጠቅማልና ምንም ገንዘብ ሳናወጣ በኦርቶዶክሳዊነት እሳቤ ብቻ እንተባበር ።

18/11/2025

በነገሮች ሁሉ የእውነት ባለቤት እና የድንግል ማርያም ልጅ የሆነውን መድኃኔዓለምን በማስቀደም የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ እና ስርዓቶቿን ለዓለም እናሰ.....

የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነዉ እርሱም ዝሙት ርኩሰት መዳራት ጣዖትን ማምለክ  ሟርት ጥል ክርክር ቅንአት ቁጣ ዐድመኛነት መለያየት መናፍቅነት ምቀኝነት መግደል ስካር ዘፋኝነት ይህንም የሚመስል ነ...
21/02/2025

የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነዉ እርሱም ዝሙት ርኩሰት መዳራት ጣዖትን ማምለክ ሟርት ጥል ክርክር ቅንአት ቁጣ ዐድመኛነት መለያየት መናፍቅነት ምቀኝነት መግደል ስካር ዘፋኝነት ይህንም የሚመስል ነዉ አሰቀድሜም እንዳልሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም የመንፈስ ፍቅር ደስታ ሰላም ትዕግሥት ቸርነት በጎነት እምነት የዉሀት ርስን መግዛት ነዉ፡፡

ወደ ገላትያ 5፤19-22

Address

Harer

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awee posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share