Sabom mame 2

Sabom mame 2 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sabom mame 2, Digital creator, Dakar, Harer.

05/01/2026
05/01/2026

ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ለግለሰብም ሆነ ለሀገር ደሕንነት የጎላ ፋይዳ አለው-አቶ ሳዳም መሀመድ

‌‎ሀረር፤ ታህሳስ 27/2018 (ሀክመኮ) ፡‒ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ለግለሰብም ሆነ ለሀገር ደሕንነት የጎላ ፋይዳ እንዳለው የሀረሪ ክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሳዳም መሀመድ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል ብሔራዊ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መቶ ፐርሰንት ተደራሽ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የክልሉ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊና የክልሉ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አስተባባሪ አቶ ሳዳም መሀመድ ገለፁ።

እስካሁን ባለው ሂደት በክልሉ ከ 269 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ ተመዝግበው መውሰዳቸውንም ገልፀዋል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተግባራዊ መደረጉ ከዚህ በፊት ከመታወቂያ ካርድ ጋር ተያይዞ ይከናወኑ የነበሩ የማጭበርበር ችግሮችን ለመከላከል እያስቻለ እንደሚገኝም አክለዋል።

በተለይ ፋይዳ ከሲስተም ጋር የተሳሰረ በመሆኑ አንድ ሰው በአንድ ማንነትና በአንድ መታወቂያብቻ እንዲገለገል በማድረግ ቀድመው የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን ሙሉ በሙሉ እያስቀረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እንደ ሀገር ለተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን፣የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አስረድተዋል።

በተለይ በአገልግሎት ሰጪ እና ተቀባዩ መካከል መተማመን እንዲፈጠር በማስቻል ለግለሰብም ሆነ ለሀገር ደሕንነት የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል።

በሌላ በኩል ከከተማ ከተማ፥ከክልል ክልል ፥ ከአንድ ተቋም ሌላ ተቋም በማይቀያየር እና ወጥ በሆነ የግለሰብ ማረጋገጫ ስርዓት ዜጎች የተሻለ እና የታመነ አገልግሎት እንዲያገኙ ይረዳል።

ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸውን እንግልት በመቀነስ ባሉበት ቦታ ሆነው በፈለጉት የመንግስት ተቋም፣ወረዳ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሞባይላቸውን ብቻ በመጠቀም አገልግሎቶችን ፍፁም አስተማማኝ በሆነ መልኩ እንዲያገኙ ያስችላል።

በተለይ ወረቀትንና የተንዛዛ ቢሮክራሲን በማስቀረት የቴክኖሎጂ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ዘርፎችን በማቀናጀት ኢትዮጵያ በ2030 ካለመችበት እንድትደርስ የሚያስችላት ትልቅ የብልጽግና ግብ ነዉ፡፡

መታወቂየው ሁሉም ዜጋ ልክ እንደ ሰብዓዊ መብት የሚያገኘው ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ እያንዳንዱ ዜጋ በዚህ የታሪክ ጉዞ ውስጥ የፋይዳ መታወቂያ በመያዝ፣ለሀገሪቱ የዲጂታል ሽግግር ስኬትና ለዘመናዊ አሰራር መስፈን የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

05/01/2026
03/01/2026

Address

Dakar
Harer

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sabom mame 2 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share