
03/07/2025
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ !!
ሰኔ 1/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዋንጫ ክለባችን ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2-1 በማሸነፍ ያነሳዉን ዋንጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አላግባብ በሆነ መንገድ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ ይሰጥ በማለት የወሰኑትን ዉሳኔ በመቃወም የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በዛሬው እለት የቅሬታ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብቷል።
የቅሬታ ደብዳቤ ለማስገባት በተቀመጠዉ ቀነ ገደብ መሰረት ክለባችን በዛሬዉ እለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አላግባብ ዋንጫው ከእኛ እንዲነጠቅ በማለት የወሰነዉን ዉሳኔ በድጋሚ እንዲያጤን እና እንዲያስተካክል በማለት የተለያዩ የFIFA እና የሀገራችን የእግር ኳስ መተዳደሪያ ደንቦችን በመጥቀስ በዉሳኔዉ ላይ ቅሬታዉን በመግለፅ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በማለት ገልፆ ደብዳቤ አስገብቷል።
ክለባችን ሲዳማ ቡና የመጀመሪያ ምዕራፍ ህጋዊ ሂደቱን በተከተለ መልኩ ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ ያስገባ ሲሆን በቀጣይም ፍትህ እስኪያገኝ ድረስ ህጋዊ ሂደቶችን እየተከተለ ወደተለያዩ ምዕራፎች የሚያመራ ይሆናል።
✍️ Biruk Hanchacha