11/08/2026
ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ (ዶ/ር) በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድና ትራፊክ ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
በቅርቡ እየሱስ ይመጣል በማለት በአደባበይ ሲሰብኩ ታይተው በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነው የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ (ዶ/ር) በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድና ትራፊክ ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
ከወራት በፊት እየሱስ ይመጣል በሚል በአደባበይ ሲሰብኩ በሚያሳዩ ምስሎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች አማካኝነት በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ትኩረትስበው የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ (ዶ/ር) አዲስ የሥራ ሀላፊነት ተሰጣቸው።
በዚሁ መሠረት ዋና ኢንስፔክተር (ዶ/ር) ተስፋዬ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድና ትራፊክ ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የከተማዋን የመንገድ ላይ የትራፊክ እንቅስቃሴና ደህንነት በበላይነት እንደሚመሩ ታውቋል።
ኃላፊው በቀጣይ በከተማዋ የሚታዩ የትራፊክ መጭናነቅ እና አደጋዎችን ለመቀነስ፣ እንዲሁም የትራፊክ ህግ ማስከበር ሥራዎችን ለማጠናከር ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ ከተሰጠው ኃላፊነት ጋር ተያይዞ ተገልጿል።