30/08/2023
የጋቦን መሪ የነበሩት አሊ ቦንጎ ባሰራጩት አጭር ቪድዮ "ወዳጆቼ... ታስሬያለሁ፣ ድምፅ አሰሙልኝ (make some noise)" ብለዋል።
ዌል... ምናልባት የአባታቸውን የ41 አመት ስልጣን የወረሱት አሊ ቦንጎ በቁም እስር ላይ ስላሉ ያላወቁት ነገር ቢኖር በርካታ ጋቦናውያን ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ በጎዳናዎች ላይ ወጥተው "የደስታ ድምፅ እያሰሙ" መሆኑን ነው።
በነገራችን ላይ የዛሬ አምስት አመት ገደማ ጋቦንን የመጎብኘት እድል አግኝቼ ነበር።
ከነዳጅ ምርት በሚገኝ ገንዘብ በአለም እጅግ ሀብታም ከሚባሉት ሀገራት ውስጥ የምትመደበው ጋቦን ህዝቧ ግን በከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል። በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ምስል በወቅቱ ያነሳሁት የፕሬዝደንቱ ቅንጡ ፅ/ቤት ሲሆን የቦንጎ ቤተሰብ በፈረንሳይ የበርካታ ቪላዎች እና ውድ ተሽከርካሪዎች ባለቤት ነው።