Dawro tube

Dawro tube welcome to green Light Media

13/07/2026
04/07/2026

Today, devastating footage is emerging from Mekelle 🇪🇹, the capital of the Tigray region. The sheer desperation of a community pushed to its absolute limits is on full display.

The TPLF leadership is forcibly rounding up young children and youth, packing them onto buses to be sent to the frontlines of war. In a raw, powerful act of defiance, the local community took to the streets, blocking roads, pelting the vehicles with stones, and begging through tears for the return of their stolen children.

Despite the desperate pleas of weeping mothers and raging communities, the forced conscription of child soldiers continues unabated. This is not just a political issue; it is a profound violation of human rights and a devastating assault on innocence.

The international community, global citizens, and human rights organizations cannot look away. Silence is complicity. We must stand with the parents of Tigray and demand an immediate end to this inhumanity.
Green Light Media Human Rights Watch Abiy Ahmed Ali BBC News Africa

እንኳን ደስ አለህ 🎉🎓ዶክተር አስናቀ ቦያና በትናንትናው ዕለት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በDisaster Risk Management (DRM) የ3ኛ ድግሪ (PhD) ትምህርታቸውን  በከፍተኛ ማዕ...
29/06/2026

እንኳን ደስ አለህ 🎉🎓

ዶክተር አስናቀ ቦያና በትናንትናው ዕለት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በDisaster Risk Management (DRM) የ3ኛ ድግሪ (PhD) ትምህርታቸውን በከፍተኛ ማዕረግ በማጠናቀቅ የዶክትሬት ማዕረጋቸውን በክብር ተቀብለዋል።

ዶ/ር አስናቀ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአንጋፋው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት በከፍተኛ ማዕረግ በመመረቅ፣ በታርጫ ከተማ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት እንዲሁም በማረቃ ወረዳ ምክር ቤት በታማኝነት፣ በትጋትና በቁርጠኝነት በማገልገል ከማህበረሰቡና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ዘንድ ትልቅ ክብርና አንቱታን አትርፈዋል።

የዕውቀት አድማሳቸውን ይበልጥ ለማስፋትም ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በማቅናት በ(GIS & RS) የሁለተኛ ድግሪያቸውን ተቀብለዋል።

በአሁኑ ሰዓትም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሌክቸረርነት፣ በተመራማሪነትና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲው በተመቻቸላቸው የትምህርት ዕድል የ3ኛ ድግሪያቸውን በላቀ ውጤት አጠናቀዋል።

ዶ/ር አስናቀ በትምህርት ጉዟቸውና በሥራ ዘመናቸው በትጋት፣ በቁርጠኝነትና በማይበገር ጥረት የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ፣ ለብዙዎችም የጥንካሬና የስኬት እውነተኛ አርአያ የሆኑ ምሁር ናቸው።

በድጋሜ እንኳን ደስ አለህ ዶ/ር አስናቀ ቦያና! ይህ የላቀ ስኬትህ የዓመታት የልፋት ውጤት ነውና፣ እንኳን ደስ አለህ።👏💐
Dawro tube

እንኳን ደስ አለህ!🎓 ዶ/ር ለገሰ በጋሻው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከርሰ-ምድር ውሃ ምህንድስና (Groundwater Engineering) የዶክትሬት (Ph.D.) ዲግሪያቸውን በስኬት በማጠና...
26/06/2026

እንኳን ደስ አለህ!🎓
ዶ/ር ለገሰ በጋሻው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በከርሰ-ምድር ውሃ ምህንድስና (Groundwater Engineering) የዶክትሬት (Ph.D.) ዲግሪያቸውን በስኬት በማጠናቀቅ ተመርቀዋል።

ቀደም ሲል የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጂኦሎጂ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በሃይድሮጂኦሎጂ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ያገኙት ዶ/ር ለገሰ፣ ለዓመታት ባሳዩት ጠንካራ ጥረትና ትጋት አሁን ላይ በዘርፉ ከፍተኛውን የአካዳሚክ ማዕረግ ጨብጠዋል።

በሙያዊ መስክም በከርሰ-ምድር ውሃ፣ በማዕድን ፍለጋ፣ በቦርሆል ቁፋሮ ቁጥጥር እና በውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ ከፍተኛ አማካሪ በመሆን ለሀገራችን ዘላቂ የውሃና የአካባቢ ጥበቃ መፍትሄዎች ትልቅ አስተዋፅዖ እያበረከቱ ይገኛሉ።

Congratulations 🎉

17/06/2026
በክልሉ የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ባልደረባው በትናንትናው ምሽት አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ🥺በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ...
17/06/2026

በክልሉ የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ባልደረባው በትናንትናው ምሽት አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ🥺

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ባለደረባ የነበሩት አቶ ገለሶ ጌትሶ ትናንት ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከወላይታ ሶዶ ወደ ዳውሮ ገሳ ሲጓዝ በነበረው መኪና ላይ በደረሰው አደጋ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

በዚህም የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ አቶ ገለሶ በጤናው ዘርፍ ከጤና ጣቢያ ባለሙያነትና ኃላፊነት እሰከ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊነት በህዝብ አገልጋይነት የሚታወቅ ቅንና ሰው አክባሪ፣ በጤናው ዘርፍ ለሚመዘገበው አመርቂ ውጤት ለተቀን የሚተጋ ብርቱ ባለሙያና አመራር ነበር ብሏል።

ለሥራ ታታሪና ሰው ወዳድ እንዲሁም በተሰማራበት ቦታ ሁሉ ብቁና ጠንካራ የሥራ ባለደረባ ነበር ያለው መምሪያው ለመላው ቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን ሲል ባወጣው መግለጫ ሃዘኑን ገልጿል።

ነፍስ ይማር 😭የዋካ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰንበት ትምህርት አገልጋይ እንደ ወጣች የጠለቀች የቀትር ፀሐይ፣ ነፈሰ ይማር!ለአገልጋይ ዘማሪት ቤቴልሔም አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነፍሷን በ...
17/06/2026

ነፍስ ይማር 😭
የዋካ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰንበት ትምህርት አገልጋይ እንደ ወጣች የጠለቀች የቀትር ፀሐይ፣ ነፈሰ ይማር!

ለአገልጋይ ዘማሪት ቤቴልሔም አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነፍሷን በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን።
በህገ ቤተክርስቲያን ትዳር ፈጽመው ገና የሙሽርነት ጊዜውን ላልጨረሰው ለባለቤቷ፣ ለአገልግሎት ጓደኞቿና ለመላው ቤተሰቦቿ እግዚአብሔር ፍጹም መጽናናትን ይስጥልን። ነፍስ ይማር።

17/06/2026
የትናንት ማታ ወላይታ ሶዶ- ዳውሮ ገሳ አደጋ በትናንትናው እለት​ከወላይታ ሶዶ ተነስቶ ወደ ገሳ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ (ባስ) «በዛሮ ቀበሌ ዉስጥ አዋሾ...
17/06/2026

የትናንት ማታ ወላይታ ሶዶ- ዳውሮ ገሳ አደጋ

በትናንትናው እለት​ከወላይታ ሶዶ ተነስቶ ወደ ገሳ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ (ባስ) «በዛሮ ቀበሌ ዉስጥ አዋሾ Church ተብሎ በሚጠራው ሴፈር በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ብዙሃን ሲጎዱ ብዙዎች ለሞት ተዳርገዋል። በዚህም በድንገት ለህልፈት ከተዳረጉ ወገኖች እነዚህ ይገኙባቸዋል።

ለሞቱት ነብስ ይማር፤ ለተጎዱት ማገገምን እንመኛለን

16/06/2026

😭
በሀገራችን ኢትዮጵያ በየቀኑ የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች የንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ፣ ቤተሰቦችን እየበተኑ እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየፈጠሩ የሚገኙ አገራዊ ጠባሳዎች ሆነዋል።

ይህ እልቂት ዛሬም በሰዎች ህይወት ላይ ቁማር መጫወቱን ቀጥሎ፣ በአሰቃቂነቱ ወደር የሌለው ሌላ መርዶ ለመስማት ተገደናል።

ዛሬ አመሻሽ ላይ መነሻውን ከወላይታ ሶዶ አድርጎ ወደ ዳውሮ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ፣ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ልዩ ስሙ «ዛሮ» ተብሎ በሚጠራው አደገኛ ስፍራ ላይ በመገልበጡ እጅግ አስከፊ የትራፊክ አደጋ ደርሷል።

ከአካባቢው እየወጡ ያሉ የመጀመሪያ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአደጋው ሳቢያ የበርካታ ወገኖቻችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አልፏል፤ ቁጥራቸው የበዛ ተጓዦችም በጽኑ ተጎድተዋል።

በአሁኑ ሰዓት በአደጋው ስፍራ ላይ በህይወት የተረፉትን ሰዎችን ከተደራረበው ፍርስራሽ ውስጥ አውጥቶ ለመታደግ የሚደረገው የነፍስ አድን ስራ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

ሰዓታት በረዘሙ ቁጥር የሚጠፋው ህይወት ሊጨምር ስለሚችል፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የህክምና ባለሙያዎች እና ማንኛውም አይነት ተሽከርካሪ ያለው አካል ሁሉ በአንድነት በመረባረብ አስቸኳይና ያልተቆጠበ ድጋፍ ሊያደርጉላቸው ይገባል።

በዚህ ድንገተኛና ልብ ሰባሪ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በሰላም ያኑርልን፤ ለተጎጂዎች በሙሉ ፈጣንና ሙሉ ፈውስን ይስጥልን።

ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህ መሪር ሀዘን ለተመቱት ለተጎጂ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና ለመላው የዞኑ ህዝብ ፈጣሪ መጽናናትንና ብርታቱን እንዲሰጥ ከልብ እንመኛለን። 🥺🙏 Green Light Media

Address

Hirna
06

Telephone

0473450210

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawro tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share