27/04/2026
የለውጥና የብልጽግና መሃንዲስ፦ የክቡር ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ስኬታማ የሥራ ጉዞ!
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከተመሠረተ ማግስት ጀምሮ ያጋጠሙትን ዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች በብቃት በመወጣት፣ በአሁኑ ወቅት በአስተማማኝ የዕድገት ጎዳና ላይ ይገኛል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ የህዝብ የልማት አቅሞችን በማቀናጀት የተከተሉት ቁርጠኛ አመራር ለተመዘገቡት ድሎች ባለቤት ነው።
ክልሉ ገና ሲመሰረት የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና እና አሳሳቢ ሁኔታዎችን በመቀየር ረገድ ርዕሰ መስተዳድሩ የወሰዱት የፖሊሲ ውሳኔ (ወጪ ቅነሳ) ውጤት አምጥቷል።
በዚህም መሠረት የክልሉ ዕዳ ወደ ዜሮ እንዲወርድ የተደረገ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከነበረው 2 ቢሊዮን ብር የገቢ አሰባሰብ በአሁኑ ወቅት ወደ 18 ቢሊዮን ብር በላይ በማደግ በክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል።
ሌላው በዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ አመራር የተመዘገበው ደማቅ ስኬት፣ ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተዘረጋው የክላስተር አደረጃጀት ነው።
ይህ አደረጃጀት ሕገ-መንግስታዊ መሠረት እንዲኖረው በማድረግ፣ በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በጋራና በእኩልነት እንዲለሙ መንገድ የከፈተ ከመሆኑም በላይ ለደቡብና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችም እንደ ተሞክሮ የተወሰደ የላቀ አሠራር ሆኖ ተመዝግቧል።
በመሠረተ ልማት ዘርፍም ለበርካታ ዓመታት ተጀምረው ተጓትተው የነበሩ በርካታ ፕሮጀክቶች ፍጻሜ እንዲያገኙ ተደርጓል።
ርዕሰ መስተዳድሩና ካቢኔያቸው ከሥራ ማስኬጃ በጀት በመቀነስ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠታቸው በስድስቱም ዞኖች የሚገኙ የውሃ፣ የመስኖ፣ የመንገድ፣ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ተጠናቅቀው ለሕዝብ አገልግሎት በቅተዋል።
በክልሉ የተመዘገበው ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ መነቃቃትና ማህበራዊ ልማት በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትና ተቀባይነትን አስገኝቷል።
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ከፍተኛ ተቀባይነት የመነጨው ከቃላት ይልቅ በተግባር ከሚያሳዩት ውጤት ነው። በክልሉ በተመዘገበው ሁለንተናዊ የልማት ድል የክልሉ ሕዝብ ደስተኛ መሆኑን በተለያዩ መድረኮች ሲገልጽ ቆይቷል።
በእሳቸው ብርቱ አመራር፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ ላይ የሰላም፣ የልማትና የአንድነት ተምሳሌት ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት ክልሉ እያስመዘገበ ያለውን ሁለንተናዊ ስኬትና የርዕሰ መስተዳድሩን ውጤታማ አመራር ለማጠልሸት በማህበራዊ ሚዲያ የሚነዙ አሉታዊ ትርክቶች ፍጹም ከእውነት የራቁ ናቸው።