Hossana Press

Hossana Press Polotics is a game I am free from that kind of game

የሆሳዕና አስፓልት ስራ በጥራት ደረጃውን ጠብቆ 20 ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ለመቀበል እየተጠናቀቀ ይገኛል።
27/11/2025

የሆሳዕና አስፓልት ስራ በጥራት ደረጃውን ጠብቆ 20 ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ለመቀበል እየተጠናቀቀ ይገኛል።

ዞኑ ያለውን የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ከዘርፉ የተሻለ ገቢ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን አስተዳደር አስታወቀሆሳዕና ፦09/03/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከሚገ...
21/11/2025

ዞኑ ያለውን የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ከዘርፉ የተሻለ ገቢ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን አስተዳደር አስታወቀ

ሆሳዕና ፦09/03/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ዞኖች አንዷ የሆነችው ስልጤ ዞን በርካታ የቱሪስት መስህብ ሊሆኑ የሚችሉ ጸጋዎች ያላት ዞን ነች።

ከነዚህም መካከል በዞኑ ቅበት ከተማ አስተዳደር አጎዴ ቀበሌ የሚገኘው ሀር ሻይጣን የተፈጥሮ ሀይቅ አንዱና ዋነኛው ነው።

ሀይቁ 20 ኛውን ብሔር ብሔረሰቦች በዓል አስመልክተው በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ምልከታ እያደረገ በሚገኘው የጋዜጠኞች ቡድን ተጎብኝቷል።

የቅበት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መለሰ ዘይኔ በዚሁ ወቅት "ሀር ሻይጣን" የስልጥኛ ቃል ሲሆን ጥሬ የአማርኛ ትርጉሙ ዕጣን ጨምር ማለት እንደሆነ ገልጸዋል።

52 ሜትር ጥልቀት እንዳለው የሚነገርለት "ሀር ሻይጣን" ሀይቅ ክረምት ከበጋ የውሃ መጠን እንደማይቀንስ አቶ መለሰ ተናግረዋል።

ሐይቁን በማልማት ሙሉ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግም 72 ሄ/ር መሬት ከይገባኛል ነፃ የማድረግ ሥራ መሠራቱን ጠቁመዋል።

የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል በበከላቸው ዞኑ በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ሊሆኑ የሚችሉ ጸጋዎች ያላት ዞን እንደሆነ ተናግረዋል።

እነዚህን በቀጣይነት በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ ከክልልና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዞኑ ካለው እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ ሳይሆን መቆየቱን የሚናገሩት አቶ ሙበራ በተለያዩ ሚዲያዎች የፕሮሞሽን ሥራ እንደሚሰራ አብራርተዋል።

ሙሉዓለም ቀጭኔ (ከወራቤ)

የአርቶ ፍል ውሃ በሚፈለገው ልክ ለምቶ አዋጭነት እንድረጋገጥ በመንግሥት በኩል አስፈላጊው መሠረተ ልማቶች እንድሟሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ጠየቁፍል ውሃው በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ምልከታ ተ...
21/11/2025

የአርቶ ፍል ውሃ በሚፈለገው ልክ ለምቶ አዋጭነት እንድረጋገጥ በመንግሥት በኩል አስፈላጊው መሠረተ ልማቶች እንድሟሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ጠየቁ

ፍል ውሃው በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ምልከታ ተደርጓል

ሆሳዕና ፦11/03/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)

በሀላባ ዞን ከሚገኙ ተፈጥሯዊ የመስህብ ስፍራዎች መካከል የአርቶ የተፈጥሮ ፍል ውሃ አንዱ ነው።

የአርቶ የተፈጥሮ ፍል ውሃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ውስጥ በዌራ ወረዳ ታችኛው አርሾ ቀበሌ ይገኛል።

ይህ ፍል ውሃ የሀላባ ዞን ዋና ከተማ ከሆነው ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በ10 ኪ/ሜትር ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ዋና መቀመጫ ከሆነው ሆሳዕና ከተማ 55 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

አርቶ ፍል ውሃ ከቱሪስት መስህብነቱ ባለፈም በህመም ፈዋሽነቱ ይታወቃል።

በዚህም ምክንያት ከሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የተለያዩ አካላት ወደ ስፍራው በመምጣት በውሃው በመታጠብና በእንፋሎቱም በመታጠን ለሕመማቸው ፈውስ እንደሚያገኙ የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከዚህም በተጨማሪ ለምግብነት የሚውሉ ድንች፣የበቆሎ እሸት ቡናና ሸይ የመሳሰሉትን በፍል ውሃው በማፍላትና በማብሰል ይበሉታል ይጠጡታልም በዚህም ብርድ፣ሳል እና ከመሳሰሉ በሽታዎች ይፈወሳሉ።

ይህ ተፈጥሯዊ ፍል ውሃ በሚፈለገው ልክ ለምቶ የቱሪስት መዳረሻ መሆን እንድችል በመንግስት በኩል መንገድ፣ማረፊያና ሌሎችም መሠረተ ልማቶች እንድሟላለትም ጠይቀዋል።

የሀላባ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀሩና አህመድ በበኩላቸው በዞኑ በርካታ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህብ ሊሆኑ የሚችሉ ቦታዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ከዚህም በዌራ ወረዳ የሚገኘው የአርቶ ፍል ውሃ አንዱ መሆኑን ገልጸው ይህንንም ማህበረሰቡ ከተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስ እንደሚጠቀመው አብራርተዋል።

ፍል ውሃው ከዚህም በተጨማሪ ለመስኖ አገልግሎት እንደሚውል አቶ ሀሩና መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት መነሻነትም ፍል ውሃውን በዘላቂነት ለማልማት አርቶ ፋማ ፕሮጀክት በማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ሙሉዓለም ቀጭኔ

በሀላባ ዞን በዘንድሮ የምርት ዘመን 11 ሺህ ሄክታር ማሣ በበርበሬ መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀበዞኑ  በክላስተር የለማ የበርበሬ ማሣ  በጋዜጠኞች ቡድን ምልከታ ተደርጓል።ሆሳዕና...
21/11/2025

በሀላባ ዞን በዘንድሮ የምርት ዘመን 11 ሺህ ሄክታር ማሣ በበርበሬ መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ

በዞኑ በክላስተር የለማ የበርበሬ ማሣ በጋዜጠኞች ቡድን ምልከታ ተደርጓል።

ሆሳዕና 11/03/2018 (ሀድያ ቴሌቪዥን)

ወይዘሮ ዘይነባ ሸህ ነሲር እና አቶ ሱልጣን አደም ሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛው በደኔ ቀበሌ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ሲሆኑ በርበሬ በአከባቢው የኢኮኖሚ ጀርባ አጥንት እንደሆነ ገልጸዋል።

በአሁኑ ጊዜ ከ45 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ በርበሬ እያመረቱ እንደሆነ ገልጸው በክላስተር ማልማታቸው የተሻለ ምርት ለማግኘት፣የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከልና በህብረት ለምርቱ የሚፈልገውን እንክብካቤ ለማድረግ እንዳገዛቸው ተናግረዋል።

ከዚህም 12 ኩ/ል በሄክታር እንደሚያገኙና በዓመትም ከፍተኛ አንድ ሚሊዮን ዝቅተኛ እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር ገቢ እንደሚያገኙ አብራርተዋል።

በተለያዩ ጊዜያት በምርቱ የሚከሰቱ በሽታዎችን መንግስት በጥናት የተደገፈ መፍትሄ እንድፈለግ አሳስበዋል።

የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀጂ ኑሪዬ እንደ ዞን በበልግና በመኽር ከ 11 ሺህ ሄክታር መሣ በበርበሬ ምርት መሸፈኑን ገልጸዋል።

ከዚህም አራት ሺህ ሄክታር በክላስተር የሚለማ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የበርበሬ ምርታማነትን የሚቀንሱ በሽታዎችን ለመከላከል ወቅቶችን የመቀየር ፣ የተሻለ ዘር የማዘጋጀትና በማሣው የተለያዩ በፈረቃ የተለያዩ ምርቶችን የማምረት ሥራ መሰራቱን አቶ ሀጂ ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከዩንቨርስቲዎች ጋር ጥናት ላይ የተመሰረተ መፍትሄ እየተፈለገ ነው ብለው እንደ ሀገር የተጀመረውን ድህነትን በማሸነፍ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

በዘነድሮ ዓመት አንድ ሺህ 100 ሄ/ር ማሣ በመስኖ ለመሸፈን ግብ ተጥሎ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ሀጂ በዞኑ በርካታ የጎርፍ አደጋ ሲደርስባቸው የነበሩ አከባቢዎች አሁን ላይ ሁኔታው በመቀየር ትርፍ አምራች መሆን እንደቻሉ ኃላፊው አንስተዋል።

ሙሉዓለም ቀጭኔ

07/10/2025

Amile Farm Galaxinoomo

የዚህን ሀይቅ ስሙንና የት አከባቢ እንደሚገኝ በኮሜንት በማስቀመጥ ለሁሉም እናስተዋውቅ
28/09/2025

የዚህን ሀይቅ ስሙንና የት አከባቢ እንደሚገኝ በኮሜንት በማስቀመጥ ለሁሉም እናስተዋውቅ

28/09/2025

Yahoode በእንግሊዝኛ ምን ይባላል?

25/09/2025

ኮሪደር በሀዲይሳ ምን ተብሎ ይጠራል?

በሀድያ ዞን ከሚገኙ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ በከፊል፦ሌላም በዞናችን ያሉ ለቱሪስት መስህብነት የሚሆን ፎቶ እና አከባቢውን በውስጥ መስመር ላኩልኝ። #ሀድያ ቴሌቪዥን
05/06/2025

በሀድያ ዞን ከሚገኙ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ በከፊል፦
ሌላም በዞናችን ያሉ ለቱሪስት መስህብነት የሚሆን ፎቶ እና አከባቢውን በውስጥ መስመር ላኩልኝ።
#ሀድያ ቴሌቪዥን

Hossana Wachemo Ethiopia🇪🇹
24/05/2025

Hossana Wachemo Ethiopia🇪🇹

Address

Hosa'ina

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hossana Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category