HMH Hadiyya Media House HMH is a media company with a YouTube channel and a page. Follow us now Kabeera����
(9)

Hadiyya Media House is currently serving Hadiyya and others, who are voiceless being their voice. It is a Social Media on Facebook, YouTube & some other platforms.

ሀቀኛ የታሪክ ተመራማሪው አረፉ!! ነፍሳቸው በገነት ትረፍ! HMH
10/11/2025

ሀቀኛ የታሪክ ተመራማሪው አረፉ!! ነፍሳቸው በገነት ትረፍ!
HMH

 #እናመሰግናለን!የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከዚህ ቀደም የሀዲያ ሽማግሌዎች ባላቸው ከፍተኛ መተማመን ወደ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ በመመላለስ የመለሰ አብረሃምን ጉዳይ በምክክር ለመፍታ...
26/08/2025

#እናመሰግናለን!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ከዚህ ቀደም የሀዲያ ሽማግሌዎች ባላቸው ከፍተኛ መተማመን ወደ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ በመመላለስ የመለሰ አብረሃምን ጉዳይ በምክክር ለመፍታት ጥረት ቢያደርጉም ባለመደመጣቸው በሚዲያችን ፖለትካዊ ትችት በመስጠት የፌዴራል መንግስት ሀገራዊ ምክክርና መግባባትን በማለም ለዚህ ውጥን መሳካት ደግሞ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ወደር የለሽ መሆኑን በመጠቆም የክልላችን መንግስት ከዚህ አቅጣጫ ተቃራኒ መጓዝ እንደሌለበትም በተደጋጋሚ አስተያየት ስንሰጥ ቆይተናል።

ዛሬ ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ፎረም በሆሳዕና ከተማ መመስረቱን በመስማታችን ያጣነው ተስፋና እምነት አቆጥቁጧል።

ከክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ገጽ ያገኘነው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀገር የሽማግሌዎች ፎረም ሰብሳቢ ዳኛ ሞላ ጫኬቦ እንደገለጹት ፎረሙ እንዲመሰረት ለክልሉ መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።

የፎረሙ መመስረት አብይ ዓላማ የክልሉን ህዝቦች የእርስ በርስ መስተጋብር ከማጠናከሩም በላይ ከመንግስት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል መሆኑን ሰብሳቢው ጠቁመዋል።

ፎረሙ የክልሉን ህዝቦች አንድነት ለማስጠበቅ፣ቱባ ባህሎችና እሴቶች ለማጎልበትና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሰብሳቢው አመላክተዋል።

አባላት በክልሉ የሚነሱ ጉዳዮችን በውይይትና በምክክር ለማስፈጸም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አስታውቀዋል።

HMH መልካም ተግባራትን፣ ውሳኔዎችንና አካሄዶችን ስትመለከት በክልሉ መንግስት ጥንካሬ ስር ወትፋ ለክቡራን ተከታዮቿ ታቀርባለች! እንድሁም የክልሉን መንግስት ውስንነቶች፣ የግለሰቦችና የቡድን የመብት ጥሰትንና የፍትህ መጓደልንም እንድሁ ለህዝብ በማቅረብ ለተበዳዮች ፍትህ በመጠየቅ ትታወቃለች።

በዚህም፣ ከዚህ በፊት በሀዲያ ሽማግሌዎች ታስቦና በተደጋጋሚ ተሞክሮ የነበረው የመምህር መለሰ አብረሃም ጉዳይ በዚህ የክልሉ ሽማግሌዎች ፎረም አማካኝነት እንድታይ ቀድሞ ጥረት ሲያደርጉ በነበሩ ሽማግሌዎች በመወሰኑ ከዛሬ ጀምሮ ውጤቱን እስክንናሳውቃችሁ ድረስ በዚህ ገጽ ከመለሰ አብረሃም ፍትህ ማጣት ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ አስተያየቶችና ትችቶች የሚቆሙ ስሆን የሽማግሌዎቹ ፎረም የደረሰበትን ውጤት ይዘን የሚንመለስ ይሆናል። እስከዚያው መልካም ቆይታ ለውድ ተከታዮቻችን!!
!



 #ተመልሰናል በምክር ቤት ያለ መከሰስ መብቱ ተነስቶ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣በሽብር እና ሰው በመግደል ወንጀል የተጠረጠረት አቶ ታረቀኝ ደግፌን ጨምሮ  35 የጉራጌ ልጆች ክሳቸውን ሲከታተ...
03/03/2025

#ተመልሰናል
በምክር ቤት ያለ መከሰስ መብቱ ተነስቶ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣በሽብር እና ሰው በመግደል ወንጀል የተጠረጠረት አቶ ታረቀኝ ደግፌን ጨምሮ 35 የጉራጌ ልጆች ክሳቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ቢሆንም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ክሳቸው አቋርጦ ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀዲያው ልጅ መለሰ አብርሃም ያለምንም ወንጀል ህጋዊ ፍቃድ እያለው ሚዲያ ያለንግድ ፍቃድ ተጠቅመሃል በሚል የሀሰት ክስ ዛሬም በእስር ላይ ይገኛል።
እንደዚህ ጫፍ የወጣ ብሄርተኝነት እና ውግንና በክልሉ ላይ የጉራጌ አመራር የበላይነት በግልፅ የጉራጌ ልጆችን እየጠቀመ የሀዲያ ልጆችን እየጎዳ እንደሆነ ማሳያ ነው።
#ፍትህ ለመለሰ አብርሃም

     #ይነበብ!ለህዝብ ልማት ሟች የሆነው እጩ ዶክተር መለሰ አብረሃም ወለቦ ከታህሳስ 13/2016 ጀምሮ ያለምንም ክስ 6 ወራትን ቆይቶ ግንቦት 27/2016 ከእስር ከወጣ ከአንድ ወር እረ...
25/01/2025

#ይነበብ!
ለህዝብ ልማት ሟች የሆነው እጩ ዶክተር መለሰ አብረሃም ወለቦ ከታህሳስ 13/2016 ጀምሮ ያለምንም ክስ 6 ወራትን ቆይቶ ግንቦት 27/2016 ከእስር ከወጣ ከአንድ ወር እረፍት በኋላ የተቀረውን የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ጨርሶ ወደ ህንድ ለመመለስ ሃምሌ ወር ላይ ተነሳ። ኤርፖርት ሲደርስ ግን "ከሀገር መውጣት አትችልም፣ጰነገ ሄደህ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ቢሮ አናግራቸው" ተብሎ ተመለሰ። በነጋታው ወደዚያ ስሄድ "መሄድ አትችልም!" ተብሎ ታሰረ።

የተጠረጠረው በማህበራዊ ሚዲያ በሚያቀርባቸው የፖለቲካ ትችትና አስተያየቶቹ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 6(1)ለ እንድሁም አንቀጽ 6(2) በግልጽ፣

አንድ ንግግር እንደ ሃሰተኛ መረጃ ወይም እንደ ጥላቻ ንግግር ተወስዶ ማሰራጨት የማይከለከለው ወደ ፖለቲካ ትችትነት ወይም አስተያየትነት ያጋደለ እንደሆነ ነው!

ብሎ በግልጽ ከማስቀመጡም በላይ መለሰ አብረሃም የፈፀመው ወንጀል በግልጽ ማስረጃዎች ተረጋግጦ ባልቀረቡበትና ፍርድቤቱ ይህንኑ ተገንዝቦ የዋስ መብት ከመስጠቱም በላይ ክሶቹን ውድቅ ባደረገበት ሁኔታ በክልሉ ከፍተኛ አመራር ትዕዛዝ በዐቃቤ ህግ ይግባኝ ተጠይቆ ለተጨማሪ ግዜያት መምህሩ በእስር እንድንከራተት እየተደረገ ይገኛል።

የይግባኝ ቅሬታ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድቤትም ታህሳስ 07/2017 ለቀረበለት አቤቱታ በሁለት ዙር ቀጠሮ ብቻ እስከ ጥር 06/2017 ለአንድ ወር እንድቆይ ምክነያት ከሆነ በኋላ ጥር 06/2017 ላይ በነበረው ቀጠሮም ለየካቲት 04/2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህም ለአንዲት የይግባኝ ቅሬታ 3 ወራትን አቆይቷል። ከዚያ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተመልሶ ተደጋጋሚ ቀጠሮዎች እየተሰጠ የሚቆይ ይሆናል። በዚህ ሁሉ ባጠቃላይ ለሁለት አመታት በእስር የሚቆይበት ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ ግልጽ ነው። አሁን ባጠቃላይ አንድ አመት ከአንድ ወር ታስሯል።

ታዲያ ይህ አንድን ምስኪን ኢትዮጵያዊ መምህር በግልጽ ባልተመሰከረበትና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቱን ባላረጋገጠበት ሁኔታ በስኮላርሽፕ ከሚማርበት የዶክትሬት ድግሪ ትምህርት ማስቀረት ታሪክ ይቅር የማይለውና የማይሽረው ጠባሳ አስቀምጦ ከማለፍ በስተቀር ለአሳሪዎች ምን ትርፍ ያስገኛል?

ማሰር መፍትሄ ካልሆነ አስሮ ማቆየት ብሄር ተኮር ጥላቻ በወለደው የቅም በቀል ፖለተካ አንድን የሀዲያ ተወላጅ ከትምህርቱና ከቤተሰቡ ነጥለው አስሮ ማቆየት እንጂ ፖለቲካዊ ትርፉ ምንድነው?

ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ድምፅ በማሰማት ላይ ይገኛል። መለሰ ራሱ የሀዲያ ሽማግሌዎችንና የሀይማኖት አባቶችን በመላክ በተሳሳተ መንገድ ላይ እንደሆነ የሚሰማቸው ከሆነ እንድነግሩትና ወደፊት በምክክር ለመሄድ በደብዳቤ ጠይቋል። ግን የክልሉ መንግስት በህግም በባህልም በሀይማኖትም በምንም መለሰን ከእስር ለመፍታት አልፈለገም! ይባስ ብሎ አሁን ለምን በማህበራዊ ሚዲያ ፍትህ ይጠየቃል በሚል ቁጣ ወጣቱን ለማሰቃየት ማቀዳቸውን አፈትልኮ የወጣ መረጃ ያስረዳናል። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ብቻ ነው።

ለወንድማችን ፍትህ ከተሰጠው በማህበራዊ ሚዲያ የክልሉን መንግስት የመተቸት ተልዕኮ የለንምና ወደ መደበኛው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥቆማዎች እንመለሳለን። ይህ የክልላችንን መንግስት ያላስደሰተው እንደሆነም ማወቅ እንሻለን።



25/01/2025

የአሳሪ ክፉ አስሮ ለታሳሪው ፍትህ ስጠየቅ ይበሳጫል። መለሰ አብረሃምን ፍቱት። አለመግባባትን በንግግርና ወንድማዊ ግሳፄ ጨርሱ። ይህ ከሆነ የክልሉን መንግስት ማንደግፍበት ሰበብ የለንም።

ፍርድቤቶች ተቋማዊ ገለልተኝነትን፣ ዳኞችም ሙያዊ ነፃነትንና የስነምግባር መርሆዎችን መጠቀም ይጠበቅባቸዋል።"(ሆሳዕና ጥር 16/2017)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የ20...
24/01/2025

ፍርድቤቶች ተቋማዊ ገለልተኝነትን፣ ዳኞችም ሙያዊ ነፃነትንና የስነምግባር መርሆዎችን መጠቀም ይጠበቅባቸዋል።

"(ሆሳዕና ጥር 16/2017)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል" ስል የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

#በመጀመሪያ ቢሮው በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጹ (በፌስቡክ) የክልሉን ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት ዶክተር ኤርስኖ አቡሬ ከታች በቀይ ምልክት እንዳስመለከትነው "አቶ ኤርስኖ" በማለት መግለጹ መታረም ያለበት መሆኑን ለማሳሰብ እንፈልጋለን።

በመቀጠል፣ በክልሉ ያለውን የፍትህ ስርዓት ለማሻሻልና በግልጽ የሚታይ ፖለትካዊ ጣልቃ-ገብነት ለማስቀረት ፍርድቤቶች ህግንና ህጉ የተራቀቀበትን ህገመንግስት መሰረት አድርገው የከበረውን የዳኝነት ሙያ በተቋማዊና የዳኝነት ገለልተኝነትና ነፃነት መርህ መስራት ያስፈልጋል። ዳኞች ግራና ቀኝን በማድመጥ ገለልተኛና ህጋዊ ውሳኔ ከማስተላለፍ ይልቅ አንዳንዴ ከፈራጅነት ይልቅ የከሳሽኘትን ሚና ለመጫወት ስሞክሩ ይታያሉ። ይህ ማህበረሰቡ የፍርድ ቤቶችን ገፅታ በተበላሸ መንገድ እንድረዱና በፍርድ ቤቶች ያለውን ዕምነትና በጎ አመላካከት እንዲያጣ ያደርጋልና በትኩረት መታዬት አለበት።





 #እናመሰግናለን።ስለምስክርነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መዋቅራዊ በሆነ መንገድ የማህበራዊ ሚዲያ ፍርፋሪ የሚሰጣቸውን ሰራዊት በማቋቋም ራሱ ጽፎ በሚሰጣቸ...
23/01/2025

#እናመሰግናለን።
ስለምስክርነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መዋቅራዊ በሆነ መንገድ የማህበራዊ ሚዲያ ፍርፋሪ የሚሰጣቸውን ሰራዊት በማቋቋም ራሱ ጽፎ በሚሰጣቸው comment ራሱ የሚረካ ቱልቱላ መዋቅር መሆንን መምረጡ አግራሞትን የሚፈጥር ሆኗል። ይህንኑ እንደሚያደርግ ከዚህ በፊት የተከፋይ የሚዲያ ሰራዊቱን comments screenahot በማድረግ በገጻችን እየለጠፍን ለናንተ ለውድ ተከታዮቻችን መረጃ ስንሰጥ የነበረ ስሆን ዛሬ የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ገጽ አረጋግጦልናል። ከታች በቀይ የከበብነውን ተመልከቱት!

እኛ እንደ HMH መስራቾችና አንቀሳቃሾች አንድ ነገር ላይ እናምናለን። ለዚህም ኖረናል። ይህም፣ ጥሪ ነገር ስንመለከት በጥሩነቱ፣ መጥፎውን በመጥፎነቱ ለህዝብ በማቅረብና የራሳችንን ትንታኔዎች በማከል ነው። እኛ በክልላችን የመልካም አስተዳደርና ተጨባጭ የልማት ተግባራት እንድሁ ፍትህ ሰፍኖ ለትክክለኛ ብልጽግና የሚሰሩ ስራዎችን ስንመለከት በሚዲያችንም ሆነ በሌሎች አጋር ሚዲያዎች መረጃዎችን በማጋራት ህዝብና መንግሰትን በማቀራረብ ተገቢውን የመረጃ ፍሰት እንፈጥራለን።

ነገር ግን አሁን ላይ በክልላችን "ብሉ ጠጡ!" ይባላል፣ የሚበላውም ሆነ የሚጠጣው የለም። ይህ በሆነበት የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በሁሉም የስር መዋቅሮች ያደራጃቸውን ፍሪፋሪ ፈላጊ የሚዲያ ሰራዊት በማደራጀት በትክክለኛ መረጃዎችና ሀሳቦች ስንፍናቸውንና እኩይ ተግባሮቻቸውን የሚያጋልጥ ጽሁፍ ሲመለከቱ copy link በማድረግ በtelegram group paste በማድረግ "እንዳሻው ጣሷችን፣ ልማታችን፣ ብሉ ጠጧችን ወዘተ" እያሉ በክልላችን የማንመለከተውን ልማትና ብልፅግና ሲዘምሩ እንመለከታለን።

በተጨማሪም፣
የክልሉ መንግስት በተለያዩ ደላሎች ወጣቶችንና በሚዲያ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሸቦችን በየካፍቴሪያ ሻይ እንዲጋብዙ እያደረገ አቋማቸውን በማስለወጥ ቀደም ስል ይነስም ይብዛም ኢፍትሃዊነትን ለመታገል የሚሞክሩትን ጥረት እንዲተውና እነርሱም ምንም የሚታይ ነገር በሌለበት "ብሉ ጠጡ!" እንዲሉ በማስደረግ ለትዝብት እየጣሏቸው፣ technical support ከማግኘቱም በላይ ወጣቶቹን technically ከህዝቡ ልብ የማውጣት ስራ በተጠና መንገድ እያከናወነ ይገኛል።

በመጨረሻም፣
የክልሉ መንግስት በደላሎቹ ከሚያሳስታቸው በተጨማሪ፣ ራሳቸውን በራሳቸው ለክልሉ መንግስት subjugate በማድረግ ምናልባትም በሹመትና ጥቅማጥቅም ፍለጋ ውስጣቸው ያለውን እውነት በመደበቅ ግፈኛውን የክልላችንን መንግስት አልሚ ወተት አድርገው ለህዝብ ለማቅረብ ሲታትሩ ተመልክተን አዝነናል። በርግጥ አንዳንዴ የክልላችንን መንግስት የግፍ ጽዋ ለማምለጥ የሚደረግ እጅ መንሻም ይሆናል "ብሉ ጠጡ ከእንዳሻው ጣሰው ማዕድ" ማለት።

ግን ግን ግን
1. በየቀኑ የሚለዋወጥ አቋም አይኑረን!
2. እውነትን መሰረት እናድርግ!
3. ከምንም በላይ የሰፊው ህዝባችን ዕጣፈንታ ትልቁ ትኩረታችን ይሁን!

4. ማሽቃበጥ ከዘራችሁ የተመታ ይሁን!

እመኑን ከዚህ ውጭ አልጫ ተብላችሁ ወደ ውጭ ትተፋላችሁ እንጂ የገዛ ህሊናችሁ ጭምር ከጎናችሁ አይሆንም።

በማጠቃለያው👇




Share

 #ተነቅቶባቸዋል                ጤና ለጤናችን ⚪️⚫️🔴በእርግጠኝነት የሀዲያ ተወላጆች አይደሉም። " የሀዲያ ህዝብ የዋህ በመሆኑ በሀሰት መረጃዎች ይደናገራል፣ ምንም ማስረጃ ሳናቀርብ...
23/01/2025

#ተነቅቶባቸዋል ጤና ለጤናችን ⚪️⚫️🔴
በእርግጠኝነት የሀዲያ ተወላጆች አይደሉም። " የሀዲያ ህዝብ የዋህ በመሆኑ በሀሰት መረጃዎች ይደናገራል፣ ምንም ማስረጃ ሳናቀርብ በቅንዓትና ጥላቻ ተነሳስተን ስለ ግለሰቦችና ድርጅቶች የሀሰት መረጃዎችን ብናሰራጭ አምኖ ይቀበለናል" የሚል እምነት ያላቸው የሀዲያን ካባ የለበሱ የሀዲያ ጠላቶች በዝተዋል። ይህን አይነቱን ሁኔታ በደርግ በመነ መንግስት ያስተዋሉት አንድ ስመጥር ታጋይ እንድህ በማለት ነበር ሁኔታውን በቅኔ ለህዝቡ ይፋ ያደረጉት። "Ka inqallanme bamcci hamaaramadae moo'lehe inqqe iiqoo'ne" በማለት!! ዛሬም በከተሞቻችን ከጉራጌ፣ ከኦሮሞና ከሌሎችም ሩቅ አከባቢዎች ጭምር የታሸጉ ውሃዎችን እየገዛን ስንጠጣ ትንፍሽ ያላሉት እነዚህ ባልጩቶች ከሀዲያ ምድር የመነጨውን ገፀ-በረከት፤ ጤና ውሃን እንዳንጠቀም በማድረግ ከሌሎች አከባቢዎች የሚመጡ ውሆችን ብቻ እንድንገዛ ለማድረግ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት መጠመዳቸውን በተደጋጋሚ አስተውለናል።

በነገራችን ላይ እነዚህ የሀዲያ ህዝብ ጠላቶች በግለሰቦችና ድርጅቶች ብቻ ሀሰተኛና ጥላቻ ወለድ መረጃዎችን በማሰራጨት አያበቁም። ከዚያ አልፈው የተለያዩ የሀዲያ ጎሳዎችን በሀሰተኛ አካውንቶቻቸው በመቅረብ እርስ በርስ እንድጠራጠርና ውስጣዊ ክፍፍል እንድኖር በማድረግ አዳክመው እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሌተከቀን እየለፉ ይገኛሉ።

በመሆኑም
የተከበርከው የሀዲያ ህዝብ ሆይ ከጥንት ጀምሮ በአባቶቻችን አጥንትና ደም የፀናውን ሀዲዮማ በማስጠበቅ፣ እርስበርስ በመከባበርና በመዋደድ፣ ጠላት ከሚወረውራቸው ከፋፋይ አጀንዳዎች ራስህን በመጠበበቅ፣ በመንቃትና አሪቆ በማሰብ ለልማት፣ ለፍትህና ለነገህ ዕጣፈንታ ዛሬ የሚጠበቅብህን አድርግ!

ወንድምህን ሲያደክሚልህ አንተን የሚያበረቱህ እንዳይመስልህ! የወንድምህ ውድቀት ያንተም መሆኑን እስክትረዳ ስንቴ ትወድቃለህ? ስንቴ ታጣለህ? እስከመቼ አላስፈላጊ ዋጋ እየከፈልክ ማንም እየተጫወተብህ ትኖራለህ?

ይህ በጤና ውሃና በድርጅቱ ብቻ የተቃጣ ቀስት ከመሰለህ ስተሃል። አንተንና ምንህንም ነው የማይቀበሉት! የበረታ ግለሰብ ካለ ይመታል። የጠነከረ ድርጅት ካለህ እንድፈረስ ይደረጋል። የጠነከረ አንድነት ስኖርህ ለመከፋፈል ይሰራሉ። ጠርጥር ሀዲያ!!

!
ስትገፉን እንደ አለት እንጠነክራለን! ምክንያቱም እኛ እኮ ሀዲያ ነን!⚪️⚫️🔴
Share!



23/01/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንዳይመሰረት ከመንግሥት አቅጣጫ በተቃራኒው ቆመው "ጉራጌን ክልል ካላደረግን" በማለት ህዝብ እያሳመጹ የነበሩት የጉራጌ ባለስልጣናት ክልሉ ከተመሰረተ በኋላ ለማፍረስ ባለቸው ዓላማ የክልሉን ህዝብ እርስበርስ እንዲገፋፋ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ። የዚህ ክፉ ስራቸው አካል የሆነው ለክልሉ ህዝቦች የጋራ ልማትና ፍትህ ድምፅ የሚሆነውን የዶክትሬት ድግሪ ተማሪ አስረው ፍትል በማሳጣት ህዝብን ለማሳመጽና ክልሉን ለመበተን ቆርጠው ተነስተዋል። መለሰ አብረሃም ከመታሰሩ በፊት ስለ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች የተናገረውን ስሙ!

"Ani ixxe maqireme losoommoki. Meles ka Hind uulla maqireme losukkuyya, hanniinsette waatittoki yakkamaare, Hadiyya yakk...
22/01/2025

"Ani ixxe maqireme losoommoki. Meles ka Hind uulla maqireme losukkuyya, hanniinsette waatittoki yakkamaare, Hadiyya yakkam uulliinsete" yaate dabarokoki. Ka uulla ixxo Hadiyya yakkate weeshakkamoki. Hadiyyoomina lobakat bito miqaakko ni beshichcho. Hanqa woce yitakolas anim ixxesa ihe yakkota'n losano maysoommo yaa baddoommo. ixxi ka minadabina hanqa wocimine losanii laso gatukisa sawoommaa xisookko😭! Danaamisa sagari inkona! Hind uullinsete! Ka photo kiisumoki anete ee balla!
⚪️⚫️🔴

 🤨የሀዲያ ሀገር ሽማግሌዎች በሀገር ደረጃ በተመሰከረላቸውና ብዙዎች ተሞክሮውን ለማጋራት የተለያዩ ትምህርታዊና ሳይንሳዊ የጥናትና የምርምር ስራዎችን በሰሩበት፣ የተለያዩ ሚዲያዎች ሰፋፊ ዘገባ...
22/01/2025

🤨
የሀዲያ ሀገር ሽማግሌዎች በሀገር ደረጃ በተመሰከረላቸውና ብዙዎች ተሞክሮውን ለማጋራት የተለያዩ ትምህርታዊና ሳይንሳዊ የጥናትና የምርምር ስራዎችን በሰሩበት፣ የተለያዩ ሚዲያዎች ሰፋፊ ዘገባዎችን በሰሩበት" ጢግ ጉላ" በተሰኘው የእርቅ ስነ ስርዓት ሞት ያስከተለውን ከባድ ግጭት ወይም ክስተት ሀላፍነት በመቀበል ከጥንት ስወርድና ሲዋረድ በመጣው ጥበብ ተጠቅመው እርቀ-ሰላም ያወርዳሉ። በሚገርም ሁኔታም ገዳይ የሟች ቤተሰብ የሚሆንበትንና ቅም-በቀል እንዳይኖር የማድረግ ፀጋ የተቸራቸው የሀዲያ ሽማግሌዎች የሀዲያ ህዝብ እርስበርስ እንድሁም ከአጎራባች ህዝቦች ጋር በዘላቂ ሰላምና ጥሩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና አብሮነት እንዲኖረው አስችለው ቆይተዋል።

እነዚህ የተከበሩ የሀዲያ ሽማግሌዎች ልጃችን እጩ ዶክተር መለሰ አብረሃም በግፍ ከታሰረ በኋላ የህዝብን ጩኸት ለማርገብና ለተበዳይ ወንድማችን ፍትህ ለማስገኘት እንድሁም የክልሉ መንግስት ቅሬታ ካለው ጠይቆ ቀጣይነት ያለውን መደማመጥና አብሮ መስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በማሰብ የሀይማኖት አባቶችን አካተው ደብዳቤ በማዘጋጀት ከመምህር መለሰ አብርሃምም ችግሮችን በንግግር ለመፍታትና ለምክክር ፈቃደኛ ስለመሆኑ በጽሁፍ ማረጋገጫ ይዘው ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ስድስት ግዜ ተመላልሰዋል።

ነገር ግን በስድስቱም ግዜ እዚህ በጽሁፍ ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ወደ ርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ እንዳይደርሱ የተደረጉ ስሆን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና አማካሪውና ሌሎች የተለያዩ ዘርፎች አማካሪዎች እንድሁም የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አናግረዋቸዋል። ሁሉም በአንድነት የመለሰ አብረሃም መታሰርም ሆነ መፈታት በርዕሰ መስተዳድሩ ይሁንታ መሆኑን በመጥቀስ ርዕሰ መስተዳድሩን ማግኘት እንደማይችሉ በማሳወቅ በተደጋጋሚ መልሰዋቸዋል። ነገር ግን ለሀዲያ ሽማግሌዎች ጀርባ የሰጡት ርዕሰ መስተዳድሩ የሌሎች አጎራባች ህዝቦች ሽማግሌዎችን ሆሳዕና ወዳለው ቢሯቸው በመጋበዝ በተደጋጋሚ ሲያወያዩ ተመልክተናል።

በመጨረሻም የሀዲያ ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በብዙ ሀዘንና የልብ ስብራት ወደ ቤታቸው ተመልሰው ነገሮች በህግ አግባብ እንድታዩ ተው በማለት ያዘዙን ስሆን፣ ህግ ነገሮችን አይቶ በመጀመሪያ በዋስ የመፈታት መብት ፈቀደ። ነገር ግን ርዕሰ መስተዳድሩ በብዙ ቁጣ ይህ ተፈፃሚ እንዳይሆን ከለከሉ። በመቀጠል ፍርድቤቱ ክሶችን ውድቅ አደረገ። አሁንም ርዕሰ መስተዳድሩ ይግባኝ ጠይቁና ልጁ ከእስር እንዳይፈታ አድርጉ በማለት ለክልሉ ፍትህ ቢሮ ሀላፊና በስሩ ላለው ዐቃቤ ህግ አስጠነቀቁ። ይህንኑ ከራሳቸው ሰምተን አዘንን።

እንግድህ እየሞቱ ማቃሰት ሰዋዊ ነውና የወንድማችንን ህመም አብረን ለመታመም ተነሳን። ነገር ግን ሰላማዊ የፍትህ ጥሪያችንን የናቀው የክልላችን መንግስት ወንድማችንን ከአንድ ቀጠሮ ወደ ሌላ ቀጠሮ በየዙሩ አንድ አንድ ወር እየተቀጠረ ያለ ጥፋቱ በእስር እንዲማቅቅ እያደረገ መቆየትን መርጧል። ዝሆኖች ሲጣሉ ሳሩ ይጎዳል ነውና እኛም ምንም እንኳን መለሰ ለልማት፣ ለፍትህና እኩልነት ድምጽ እያሰማ ባደገበት ማህበረሰብ ጓዳ በጠላቶች ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት ብሆንም ለህዝባችን ሰላም ቅድሚያ በመስጠት እስካሁን የሰላም መንገድ ብቻ መርጠናል። Share አድርጉ!







Address

Bezabih Petros' Memorial Street
Hosa'ina

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HMH posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to HMH:

Shortcuts

Share