Ethiopian Today

Ethiopian Today ይህ ፔጅ ውስጥ አስተማሪ ፡ አዝናኝ እና ወቅታዊ ጉዳዮች የሚዳ?

17/02/2022

በሀረሪ ክልል ድህነትን ለመቀነስና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት
እየተሰራ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ድህነትን ለመቀነስና እና
የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ
መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
በክልሉ ሁለተኛው ዙር የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በይፋ የተጀመረ ሲሆን÷
በመድረኩ ላይ ተገኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፥ ስር
የሰደደ ድህነትን ለመቀነስ እና የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት
እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በፕሮግራሙ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በጥራት ማከናወን ይገባል ያሉት
ርዕሰ መስተዳድሩ የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዋና አላማም በተለይ
የህብረተሰቡን ህይወት መቀየር መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት
ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ቆጥበው ወደ ጥቃቅንና አነስተኛ ለሚሸጋገሩ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች የክልሉ
መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሁለተኛው
የከተማ ሴፍቲኔት መርሃግብር ቀደም ሲል የታዩ ክፍተቶቸን በማረምና
ጥንካሬዎችን በማጎልበት በትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሁለተኛው ዙር የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም 1 ሺህ 562 ዜጎች ተጠቃሚ
ያደርገ የልማት ስራ ለማከናወን አስፈላጊውን የልየታና ሌሎች ስራዎች
መጠናቀቃቸው የተመላከተ ሲሆን ÷በመርሃግብሩም በአረንጓዴ ልማት፣ በደረቅ
ቆሻሻ እና ሌሎች ተግባራት እንደሚከናወኑ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት ፔጁን like shere &follow ያድርገለ

06/02/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአፍሪካዊያን እርስ በእርስ ቱሪዝምን በማስፋፋት
ኢንዱስትሪውን መደገፍ ይችላሉ አሉ
ጥር 28/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የአፍሪካዊያን እርስ በእርስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢንዱስትሪውን መደገፍ
ይችላሉ አሉ።
35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክቶ ለሀገራት መሪዎች እና
ከፍተኛ ኃላፊዎች በወዳጅነት አደባባይ በተከናወነው መርኃ ግብር ላይ ንግግር
ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አፍሪካ ዐቀፍ ቱሪዝምን ማስፋፋት እንደሚገባ
አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
የአፍሪካ ቱሪዝም መስክ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ አማካኝነት ክፉኛ መጎዳቱን
ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢንዲስትሪውን የሀገር ውስጥ እና የአፍሪካዊያን
እርስ በእርስ ቱሪዝም በማስፋፋት መደገፍ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
በአፍሪካ ዐቀፍ ቱሪዝም ውስጥ ለባህል ልውውጥ፣ ተግባቦት፣ ምጣኔ ሃብታዊ
ትስስር እና የአፍሪካ የቱሪስት መስህቦች የጋራ እድገትን ለማምጣት እድል
መኖሩንም ተናግረዋል፡፡
ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት አካል ሆኖ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ
የተገነባው የወዳጅነት አደባባይም ሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ለሚገባቸው
የወደፊት ብልፅግናቸው ምልክት ነውም ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ
ስሟን ወደሚመስል ከተማነት የሚለውጣት ታላላቅ ሥራዎችን እያከናወነች
መሆኗን በመግለፅም አደባባዩ የከተማ ቱሪዝምን የማጎልበት እንቅስቃሴ
ጠቋሚነቱን ገልፀዋል፡፡
እንደኢቢሲ መረጃ ኮቪድ-19 በመካከላችን የፈጠረው ርቀት የምንሻገርበት
መንገድ እንዲመጣ እንመኛለን ሲሉም መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

11/01/2022

የአማራ ክልል የፍትህ፣ የጸጥታ እና የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የአማራ ክልል የፍትህ፣ የጸጥታ እና የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው።
በውይይት መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን
ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የፍትህ እና
የጸጥታ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ
ያመላክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

05/01/2022

ቅዱስ_ላሊበላ_አብያተክርስቲያናት
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳
የንጉስ ላሊበላ ገድል ስለትውልዱ እንዲህ ይላል፣ “አባቱ በላስታ
አውራጃ የቡግናው ገዢ የነበረው ዣን ስዩም ሲሆን፣ እናቱ ደግሞ አገልጋይ
ነበረች…፡፡” አገልጋይቱ ከዣን ስዩም ማርገዟን የሰማችው የዣን ስዩም ሚስት
በንዴት ጦፈች፡፡ እመቤቲቱን ፍራቻ ነፍሰጡሯ አገልጋይ ወደ ሮሃ – የዛሬዋ
ላሊበላ – ሸሽታ ህፃኑ እዚያ ተወለደ፡፡ እናቲቱ ህፃኑን እዚያው ትታ ወደ ዣን ስዩም
ቤት ተመለሰች፡፡
ህፃኑን ፍለጋ፣ ዣን ስዩም ሰዎች ወደ ሮሃ ሲልክ፣ ህፃኑ በንቦች ተከብቦ አገኙት፡፡
ይሄኔ ሰዎቹ፣…ላህሊ..በላ አሉ፤ ንቦች ታላቅነቱን ተረዱለት እንደማለት ነው ይላል
ገድለ ላሊበላ፡፡ የቅዱስ ላሊበላ የትውልድ ቀን ታህሳስ 29፣ 1101 ዓ.ም ሲሆን
በየዓመቱ ታህሳስ 29፣ የገና ዕለት፣ በስሙ በተሰየመችው በቀድሞዋ ሮሐ፣
ባሁኗ ላሊበላ፣ ታላቅ ክብረ በዓል ይሆናል፡፡
የላሊበላ ወንድም ሀርቤ ለአባቱ ዙፋን ከላሊበላ ይልቅ የተገባ በመሆኑ
– ከህጋዊ ሚስት የተወለደ እንደመሆኑ መጠን እና ከላሊበላ ጋር ተያይዞ
በሚነሳው ትንቢት ሳቢያ ወንድሙን በበጎ አላየውም፡፡ በዚህም የተነሳ፣ ላሊበላ
ሀገሩን ለቅቆ ወደ እየሩሳሌም አቀና፡፡ በዚያም ለብዙ ዓመታት ቆየ፡፡
ከስደት እንደተመለሰ፣ መስቀል ክብራን አገባ፡፡ ቢሆንም ግን፣ ወንድሙ ሀርቤን
ፍራቻ ወደ በረሃ ለመሰደድ ተገደደ፡፡ ስለ ላሊበላ ወደ ዙፋን አወጣጥ
የሚጠቀሱት ዘገባዎች የተለያዩ ናቸው፡፡ አንድ ምንጭ፣ “ሀርቤ የላሊበላን
መንገስ አይቀሬነት ስለተገነዘበ፣ ዙፋኑን ለላሊበላ ለቅቆ፣ ገብረመስቀል ብሎ
አነገሰው…” ሲል፤ ሌላኛው ደግሞ፣ “በጦርነት ላሊበላ ወንድሙን አሸንፎ ዙፋኑን
እንደወረሰ…” ይገልጻል፡፡
የሆነው ሆኖ፣ ላሊበላ፣ በ1156 ዓ.ም፣ ገብረመስቀል ተብሎ ነገሰ፡፡ ለ40
ዓመታትም ገዛ፡፡ ኢትዮጵያዊ ምንጮች እንደሚሉት ላሊበላ አንድ ልጅ ብቻ
ነበረው – ይትባረክ፡፡ ምዕራባውያን ምንጮች ደግሞ ሌላ የይትባረክ ታናሽም
ነበር ባይ ናቸው – አትያብ የተባለ፡፡
ላሊበላ ያስተዳድረው የነበረው ግዛት እጅግ ሰፊ እንደነበር ይነገራል፡፡
ይኸውም፣ ከአባይ እስከ ምፅዋ፣ ከወንጪት እስከ መተማ፣ ከሐረር እስከ ዘይላ፣
ከጅማ እስከ ጫጫ፣ ከሲዳሞ እስከ ነጭ አባይ ይዘረጋል፡፡
ንጉስ ላሊበላ ይህን ሰፊ ግዛቱን በአራት ከፍሎ በአራት አስተዳዳሪዎች
ያስተዳድር የነበረ ሲሆን፤ አቡ ሳሊህ የተባለ የወቅቱ ፀሃፊ የላሊበላን ግዛት
በተመለከተ፣ “በዓለም ካሉ አራት ታላላቅ ነገስታት አንዱ … የትኛውም ንጉስ
ክንዱን አይቋቋመውም” ብሎለታል፡፡ ላሊበላ፣ በንግስና ዘመኑ ከሌሎች ሀገራት
ጋር መልካም ወዳጅነትን ፈጥሮ ነበር፡፡ በወቅቱ ከግብጽ ጋር ተቋርጦ የነበረው
የንግድ ግንኙነት ተጀምሯል፡፡ በግብጽ በነበሩት ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው
መከራም ጋብ ብሏል፡፡
መንፈሳዊው ንጉስ ላሊበላ፣ ከሚታወቅባቸው ነገሮች አንዱና ዋንኛው፣
በዘመኑ ከአንድ ወጥ ድንጋይ ያስፈለፈላቸው አስራአንድ ውቅር አብያተ
ክርስቲያናት ናቸው፡፡ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ በሶስት መደብ የተከፋፈሉ
ሲሆኑ፤ ሁሉም የመሬት ውስጥ ለውስጥ መተላለፊያ ያላቸው ናቸው፡፡
በመጀመሪያው መደብ ውስጥ፣ ቤተ መድኃኒዓለም፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ-
መስቀል፣ ቤተ-ደናግል፣ ቤተ-ጎለጎታ እና ቤተ-ሚካኤል ሲገኙ፤ በሁለተኛው
መደብ ውስጥ ደግሞ፣ ቤተ-አማኑኤል፣ ቤተ-መርቆሪዮስ፣ ቤተ-ሊባኖስ እና ቤተ-
ገብርኤል ይገኛሉ፡፡
በሶስተኛው መደብ ውስጥ የሚገኘው ቤተ-ጊዮርጊስ ነው፡፡ ቤተ-ጊዮርጊስ
ከሁሉም አብያተ ክርስቲያናት በስተመጨረሻ የተሰራና እጅግ ያማረ፣ በኪነ ህንፃ
ውበቱም ከሁሉም የላቀ ነው፡፡
ይህም፣ የአብያተ ክርስቲያናቱ ሰሪዎች በስራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተራቀቁ የመምጣታቸው ምስክር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም የላሊበላ አብያተ
ክርስቲያናት ሲወሱ የሚታየው ምስል የዚሁ የቤተ-ጊዮርጊስ ምስል ነው፡፡ ገድለ
ላሊበላ እንደሚያስረዳው፣ የፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ስራ የተጀመረው፣
በላሊበላ አስረኛ ንግስ ዘመኑ ነው፡፡
ስራውን ለማጠናቀቅም 23 ዓመት ፈጅቷል ይላል – ገድለ ላሊበላ፡፡
ንጉስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ለማነፅ ምን አነሳሳው?
ገድለ ላሊበላ፣ ንጉስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ለማነፅ ስላነሳሳው
ምክንያት ሲያትት፣ “ወደ መንግስተ ሰማያት አርጎ እጅግ የሚያማምሩ ህንጻዎችን
በመመልከቱና እግዚአብሔርም እነዚህን ህንጻዎች የመሰሉ አብያተ ክርስቲያናት
እንዲያንፅ ስላዘዘው፣ ቦታውንም ስለጠቆመው ነው…” ይላል፡፡ሌሎች ምንጮች
ደግሞ፣ “ላሊበላ ለረጅም ዓመታት እየሩሳሌም እንደነበረ፣ እየሩሳሌምንና ሌሎች
ሃይማኖታዊ ፋይዳ ያላቸውን ቦታዎችን በመጎብኘቱና ባየው ነገር እጅጉን
በመመሰጡ፣ ሌላኛዋን እየሩሳሌም ለመገንባት በማሰቡ ነው…” ባይ ናቸው፡፡
እኒህ ወገኖች እንደሚሉት፣ “በወቅቱ፣ በርካታ ኢትዮጵያዊያን
እየሩሳሌምን ለመጎብኘት በሚያደርጉት ጉዞ የሚደርስባቸውን እንግልት
ለማስቀረት እየሩሳሌምን፣ አካባቢውንና መንግስተ ሰማያትን ሁሉ በተምሳሌትነት
የሚያሳይ ታላቅ ግንባታ ለመስራት ስላሰበ ነው” ይላሉ፡፡
ለዚህም አብነት የሚሆነው በሶስት የተከፈሉት አብያተ ክርስቲያናት ተምሳሌትነት
ነው፡፡የመጀመሪያው ምድብ አብያተ ክርስቲያናት የምድራዊ እየሩሳሌም
ተምሳሌት ናቸው፡፡ ይህም፣ ቤተ-ማሪያም ጌተሰማኒን፣ ቤተ-ጎለጎታ የክርስቶስ
መቃብርን፣ ቤተ-ደናግል ክርስቲያናዊ ፍቅርና እምነትን ይገልጻሉ፡፡
የሁለተኛው ምድብ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ መንግስተ ሰማያትን
እንዲወክሉ ታስበው የተሰሩ ናቸው፡፡ ቤተ-ገብርኤል የመንግስተ ሰማያትን
መንገድ፣ ቤተ-ሊባኖስ የእግዚአብሄርን ዙፋን የሚሸከመውን መልአክ ኪሩቤልን፣
ቤተ-መርቆርዮስ ገሃነምን፤ የገነት ተምሳሌት ሰማያዊ እየሩሳሌም ሆኖ የታነጸው
ደግሞ ቤተ-አማኑኤል ነው፡፡
ከነዚህም በተጨማሪ ቀራኒዮ፣ የአዳም መቃብር፣ ክርስቶስ የተያዘበት፣
የተፈረደበት፣ ቢታኒያ ሁሉ በተምሳሌትነት የተወከሉበት ቦታ በላሊበላ አለ፡፡ መች
ይህ ብቻ፣ በላሊበላ የሚገኘው ዮርዳኖስ ተብሎ የተሰየመው ወንዝም ክርስቶስ
የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ ተምሳሌት ነው፡፡
ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱን ማን ሰራቸው?
በዚህ ጥያቄ ዙሪያ የተለያዩ ምንጮች የተለያዩ ገለጻዎችን ይዘው
ቀርበዋል፡፡ ገድለ ላሊበላ፣ ራሱ ንጉስ ላሊበላ እንደገነባቸውና መላዕክት
የህንጻውን ሰራተኞች ይረዷቸው እንደነበር፣ ሰራተኞቹ በቀን የሰሩትን መላዕክት
በማታ እጥፍ ጨምረው እንደሚሰሩ ይገልጻል፡፡
በ16ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ፖርቹጋላዊው ተጓዥ
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ በበኩሉ ደግሞ አንድ ካህን የህንጻዎቹ ስራ የተከናወነው
በግብጻውያን መሆኑን እንደነገሩት ጠቅሶ ጽፏል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ፣ ከ4
እስከ 5ሺ የሚሆኑ በግብጽ ያሉ ክርስቲያኖች በወቅቱ በሀገራቸው
በሚደርስባቸው መከራ እና እንግልት ሳቢያ በስፋት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው
እንደነበር የሚገልጹ መረጃዎችም አሉ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት የጻፉት ስርግው ሀብለማሪያም በበኩላቸው፣
ከላሊበላ በፊት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በርካታ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት
የመኖራቸው ጉዳይ፣ ንጉስ ላሊበላ በውጭ ሀገር ሰዎች አሰራው የሚለውን ገለጻ
አጠራጣሪ ያደርገዋል ይላሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ፣ ትሪሚንግሃም የተባሉ ፀሃፊ፣ በላሊበላ አካባቢ ሁለት መቶ
ያህል ሌሎች ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መኖራቸውን ገልፀው፣ አብያተ
ክርስቲያናቱ በውጭ ሀገር ሰዎች ታነፁ የሚለውን አስተሳሰብ አጠራጣሪ
ያደርገዋል ባይ ናቸው፡፡ እኚሁ ፀሃፊ፣ ጉዳዩን ሲያጠቃልሉ፣ በውቅር አብያተ
ክርስቲያናቱ ላይ የሚታየው የአክሱማዊ ህንጻዎች ተፅዕኖና የግዕዝ ፊደላት
አብያተ ክርስቲያናቱ በኢትዮጵያውያን ለመታነፃቸውና የአክሱማዊ የግንባታ
ጥበብ ቀጣይ አካል እንደሆኑ ጠቋሚ ቢሆንም፣ አብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ
የሚታዩት ቅርጾች ግን በግንባታው ላይ አንዳች የባዕዳን ተፅዕኖ ሳይኖር
እንደማይቀር ጠቋሚ ነው ይላሉ፡፡
፩ # ቤተ_ማርያም
==========
ከሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጡ በበርካታ ስዕሎች ያሸበረቀው
ቤተ ማርያም ነው፡፡ በዚሁ ቤተ ክርስቲያን መሃል ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ከታች
እስከ ላይ በጨርቅ የተሸፈነ ምሰሶ ይገኛል፡፡
ምሰሶው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በግልጽ ይታይ እንደነበርና በላዩ
ላይም የእየሱስ ክርስቶስ ስም በተለያዩ ቋንቋዎች – ግዕዝ፣ አረብኛ፣ ሂብሩና
ሌሎችም የተቀረፁበት እንደሆነ የሚገልጹት አስጎብኚ ካህናት፣ በ16ኛው ክፍለ
ዘመን የነበሩት የቤተ-ክርስቲያኑ አስተዳደሪ ባዘዙት መሰረት እስካሁን ድረስ
እንደተሸፈነ ይገልጻሉ፡፡መሸፈኛው ጨርቅ ቢያረጅ እንኳን ጨርቁን ለመለወጥ
ማንሳት ሳያስፈልግ፣ በላዩ ላይ እንዲደርቡበት ያስተላለፉት ጥብቅ ትዕዛዝ
እስከዛሬ ድረስ እንደተጠበቀ አለ፡፡ ይሁን እንጂ፣ በ1966 ለጥቂት ጊዜያት
ምሰሶው ተገልጦ አራቱም ጎኖቹ ፎቶግራፍ መነሳቱ ይነገራል፡፡ ባሁኑ ወቅት
እንደተለመደው ከታች እስከ ላይ ተሸፍኗል፡፡
፪_ # ቤተ_መድኃኔዓለም
===============
ቤተ መድኃኔዓለም ከሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ትልቁ ነው፡፡ በዚሁ
ቤተ ክርስቲያን በስተሰሜን በኩል የቤተ ክርስቲያናቱ ዋና አርክቴክት እንደሆነ
የሚነገርለት የሲዲ መስቀልና የሁለት ጓዶቹ መቃብር ይገኛል፡፡
፫_ # ቤተ_ጊዮርጊስና_ቤተ_ገብርኤል
= = = ============= ====
በቤተ ጊዮርጊስ ውስጥ ንጉስ ላሊበላ የራሱን ዕቃዎች ለማስቀመጥ
ይጠቀምበት ነበር የሚባል የዕንጨት ሳጥን አለ፡፡ በሚገርም መልኩ የእንጨት
ሳጥኑ በባለ እንጨት ብሎን የሚዘጋ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፣ የቤተ ገብርኤል
በሩ በእንጨት መዘውር (Wheel and Axel)
የሚከፈትና የሚዘጋ ነው፡፡ ይኸው ቤተ ገብርኤል ሌላም እንግዳ የሆነ ነገር
አለው፡፡ ይህም፣ መግቢያው በየት በኩል እንደሆነ አለመታወቁና ባሁኑ ወቅት
ያለው መግቢያ በላሊበላ ዘመን የተሰራ አለመሆኑ ነው፡፡
ትክክለኛው ሳይሆን አይቀርም ተብሎ በሚገመተው በታችኛው መግቢያ ክፍል
በኩል ዋሻ ሆኖ በውሃ የተሞላ ነው፡፡
በስተመጨረሻ
አስደናቂዎቹን የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት
መዝግቧቸዋል፡፡ አንዳንዶችም፣ 8ኛው የአለም አስደናቂ ነገር ሲሉ
ያሞካሿቸዋል፡፡
እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ከአህመድ ግራኝ ወረራ ጥፋት እንዴት እንዳመለጡ
አይታወቅም፡፡ ንጉስ ላሊበላ በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ተብሏል፡፡
ገድሎች የታሪካዊ ሰዎችን በጎ ጎን እጅጉን አግዝፈው ስለሚያቀርቡ
ተዐማኒነታቸውና ሚዛናዊነታቸው የሚጠራጠሩ ቢኖሩም፣ ገድለ ላሊበላ ጻድቁ
ንጉስ የመንግስትን ንብረት ለግሉ ተጠቅሞ እንደማያውቅና ፍጹም መንፈሳዊ
የሆነ ህይወት እንደመራ ያትታል፡፡ የሆነው ሆኖ፣ ገድለ ላሊበላ እንደሚያስረዳው
ላሊበላ፣ ሰኔ 12፣ 1172 ዓ.ም ዓረፈ፡፡ቅዱስ ሥጋውም በቤተ ጎለጎታ ውስጥ
ይገኛል፡፡
# ቅዱስ_ላሊበላን_ተሳልመን_በረከት_ለመቀበል ያብቃን
# share_share_share ያድርጉ

01/12/2021

መላ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት አገርን እየታደጉ የሚገኙበት ወቅት ላይ
የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ልዩ ትርጉም አለው ተባለ
ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) ለ15 ዓመታት በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች
ሲከበር የቆየው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ዘንድሮ “ወንድማማችነት ለኅብረ
ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በተለየ መልኩ እንደሚከበር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድ አስታውቀዋል።
የዘንድሮው 16ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በፌዴሬሽን ምክር ቤት
አስተባባሪነትና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት በድምቀት
እንደሚከበር ምክትል አፈ ጉባኤዋ ገልጸዋል።
የዘንድሮን በዓል የተለየ የሚያደርገውም ኢትዮጵያ በውስጥ አሸባሪ ኃይሎችና
በውጭ ኃይሎች የተባበረ ጥቃት የኅልውና አደጋ በተጋረጠባት በዚህ ሰዓት
ሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድነት በመቆም አገርን እየታደጉ
የሚገኙበት ወቅት ላይ የሚከበር መሆኑ ነው ተብሏል፡፡
አሸባሪው የትሕነግ ቡድን ከውጭ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ኢትዮጵያን
ለማፍረስ ቅድሚያ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መደምሰስና መበተን በሚል
እቅድ በሰሜን ዕዝ ላይ መቼም ታይቶ በማይታወቅ ክህደት ጀምላ ጭፍጨፋ
ማካሄዱን ያስታወሱት ምክትል አፈ ጉባኤዋ በዚህም ሳይወሰን የችግሩ ገፈት
ቀማሽ በሆነው በወንድሞቹ የአፋርና የአማራ ሕዝቦች ላይ ታሪክ መቼም ይቅር
የማይለውን የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መፈፀሙን ገልጸዋል፡፡
ምንም እንኳ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን እልህ አስጨራሽ የሕልውና ዘመቻ ላይ
ብትሆንም አሃዳዊያን ናችሁ በማለት ኅብረብሔራዊ የዴሞክራሲ ሥርዓታችንን
ለማጠልሸት የሚሯሯጡ ጠላቶቻችንን አንገት ለማስደፋትና የብሔር፣
የብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ቃል ኪዳን እንደገና ለማደስ በዓሉ በድምቀት
ይከበራል ነው የተባለው፡፡
በዚህም መሰረት በዓሉ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በፓናል ውይይት
እንደሚከበርና ክልሎችም በማዕከል በተዘጋጀላቸው ወቅታዊ የመወያያ ሰነዶች
አማካይኝነት እስከ ቀበሌ ድረስ በማውረድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
በመስጠት በዓሉን እንደሚያከብሩ ተገልጿል፡፡
የፌዴራልና የክልል የሲቪል ሰርቪስ ሁሉም ሰራተኞች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና
የየዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች በሚቀርቡላቸው
ሰነዶች ላይ ውይይት በማድረግ በዓሉን እንደሚያከብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት
አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለሰራዊቱ ደም በመለገስ እንዲሁም ለተፈናቀሉ ወገኖች፣
በግንባር እየተፋለም ላለው የአገር መከላከያ ሰራዊትና የዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ
ማድረግ የብዓሉ መርኃግብር አካል መሆኑ ተመላክቷል።

01/12/2021

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም መስክ ተባብሮ ሲነሣ
ውጤቱ ድል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በግንባር፣ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በኮሙዩኒኬሽን፣
በስንቅ ዝግጅት፣ ዘማች በመንከባከብ፣ ጸጥታ በማስከበር፣ ተፈናቃዮችን
በመደገፍ. በሁሉም ግንባሮች ለዘመታችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ” በማለት
በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

01/12/2021

ሰበር ዜና
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እየተመራ በሁሉም ግንባሮች ወደ ከፍተኛ
የማጥቃት እንቅስቃሴ የገባው የ"ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" አስደናቂ
ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ሲሉ የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት
ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት በጋሸና ግንባር ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ
ልዩ ሀይል ሚሊሻና ፋኖ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ የአርቢትን፣ የአቀትን፣
የዳቦና የጋሸና ከተሞችን ነጻ አውጥተዋል።
በዚህ ግምባር ጠላት ለበርካታ ወራት የዘረፈውን ሀብት በመጠቀም በወረራ
የያዘውን አካባቢ ህዝብ በማስገደድ ያሰራውን ባለብዙ እርከን ኮንክሪት ምሽግ
በተቀናጀ እቅድ፣ አመራርና ቴክኖሎጂ በመታገዝ በአነስተኛ መስዋዕትነት ምሽጉ
ተሰብሯል።
በዚህ ግንባር በርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን ከባድ መሳሪያዎች በወገን ጦር
ተማርከዋል።
ይህ ድል ለዝርፊያ የገባውን የጠላት ሀይል ወገቡን የቆረጠ ነው።
የወገን ጦር ጋሸናን መቆጣጠሩ ጠላት በላሊበላ፣ ወልዲያና ደሴ
የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጽዳት መንገዱን ምቹ
ያደርጋል።
የወገን ጦር የጋሸናን እና አካባቢውን ከመቆጣጠር አልፎ በላሊባለ፣ ወልዲያና
ወገል ጤና አቅጣጫ በአሁኑ ሰአት ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።
በወረኢሉ ግንባር የጃማደጎሎ ወረኢሉ ገነቴ፣ ፊንጮፍቱ፣ አቀስታ ከተሞች
በጀግኖቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይ ሚሊሻና ፋኖ ጥምረት
ከአሸባሪው ነጻ ወጥተዋል።
በሸዋ ግንባር የመዘዞ፣ ሞላሌ፣ ሸዋሮቢትና አካባቢው እንዲሁም ራሳና
አካባቢው ጀግኖቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል ሚሊሻና ፋኖ
በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ወጥተዋል። ጅግኖቹ
ወደፊት እየገሰገሱም ይገኛሉ።
በምስራቅ ግንባር በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአፋር ልዩ ሀይልና
ሚሊሻ ባደረጉት ተጋድሎ ነጻ የወጡት የካሳጊታ፣ ቡርቃ ዋኢማ ጪፍቱ ድሬሩቃ፣
ጭፍራ አለሌ ሱሉላ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ከጠላት ጸድተዋል፤ የአካባቢው
አስተዳደር ወደ ቦታው ተመልሷል።
አካባቢህን ጠብቅ
ወደ ግንባር ዝመት
ሠራዊቱን ደግፍ

01/12/2021

ደስ የሚል መልክት አለው አንብቡት!
ይጠቅማችኃል
ባልና ሚስት በትዳርና በፍቅር አብረው ይኖሩ ነበር ። እኚህ ባልና
ሚስት ሁለት ልጆች ነበራቸውና ለልጆቹ ማሳደጊያ ባልየው ተጨማሪ ስራ ሊሰራ
ተሰማምተው ራቅ ወዳለ አገር ሄዶ መስራት ጀመረ ። ለብዙ ዓመታት ከቆየ በኋላ
ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ሲነሳ ያልገመተው ነገር ከቀጣሪዎቹ ሰማ ። ደሞዙ
በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው 30 ብር
ተሰጠው ።
የተሰጠውን ተቀብሎ እግረ መንገዱ ስራ ካገኘ እየሰራ ጠርቀም
ያለ ብር ይዞ ቤተሰቦቹ ጋር ለመሄድ ተነሳ ። በመንገዱ አንድ ሸምገል ያሉ አባት
አገኘ "ወዴት ትሄዳለህ ልጄ ከየት ነውስ ምትመጣው ?" አሉት ። እሱም
ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው ። እሳቸውም እንዲህ አሉት
"እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ቀላል ነው ፤ እሱም እንዴት
አባቴ ?" ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም "በል አንድ አስር ብሩን አምጣና
እነግርሃለሁ" አሉት የቸገረው ነውና አንስቶ ይሰጣቸዋል ።
እኒህ አባትም "አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ
አትሂድ" ይህ ምክር አንድ ነው ይሉታል ። ሁለተኛውን አምጣና ሁለተኛውን
መንገድ ልንገርህ ይሉታል ። እሱም በየዋህነት ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ ፤
ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ምክሬ ነው" ይሉታል ። "በቃ ይሄ ነው ?" ቢላቸው "አዎን
ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም አሰፈላጊውና የመጨረሻውን ስጦታዬን
ልስጥህ" አሉት ሰጠ ። እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" ብለውት በባዶ
ኪሱ ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት ። እሱም ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ።
በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ መሸ ። ነጋዴዎቹም
ለምን ባቋራጭ አንሄድም በማለት ጉዞ ጀመሩ ። እሱም አብሯቸው ጉዞ
እንደጀመረ የሽማግሌው አባት ምክር አንድ ትዝ አለው ። "አቋራጭ ነው ብለህ
በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው ። ስለዚህ ተመልሶ በሚያውቀው
መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ በኋላ ከተማ ገባ ። "የመሸበት እንግዳ ነኝ
አሳድሩኝ" በማለት ሰው ጠየቀ ። አንድ የዛ ከተማ ሰውም "ይኸውልህ ወንድሜ
እዛ ቤት ሂድ ያሳድርሃል ፤ ነግር ግን እዛ ሰው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም
እድልህን ሞክር ።" እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት የእንግዳ ነው ተብሎ
ገባ ።
ታድያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረው
ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴት ሆነክ ተረፍክ ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴች
ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው ከተማው ለቅሶ ብቻ እኮ ነው የሆነው" አለው ።
ያቺ አስር ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛ ህይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው
። ስለመሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብ ከጓዳ ብቅ አለች"
እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም ። የተወሰነ አካሏ ብቻ ነው ሰው
የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ እስክትገባ ናፈቀ ።
"ከዚህች ጋር እንዴት ትኖራለህ?" ብሎ ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር
ትዝ አለው "በማያገባህ አትግባ" የሚለው ። ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን
ተቋቁሞ አደረ ። ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ
ነገር አለኝ ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም የሞላበት ሜዳ አሳየው
እንግዳውም "ይሄ ምንድ ነው ?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ
ብሎ ራሱን እየነቀነቀ ዝም አለ ። የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ "በእውነት አንተ
የምትገርም ሰው ነህ ፤ ይህ የምታየው ሰው ሁሉ ስለሚስቴ የማያገባቸውን
አስተያየት ስለሰጡ የተገደሉ ናቸው ፤ እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድንት የመጡ
ነበሩ ።
አንተ ግን ታላቅ ሰው ስለሆንክ የሀብቴን 1/4 ኛ ሰጥቼሃለሁና
ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ ። እዛች ደሳሳ ጎጆ
የደረሰው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር ። ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን
አላጣውም ። በትልቅ እንጨት የምትዘጋ በሩን ገፋ ሲያደርጋት ተከፈተች ። አይኑ
ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ። ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች ።
በንዴት ጦፎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል 3ተኛው ምክር ትዝ
አለው ። "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው ። ከቤቱ ውጭ በተጋደመው ዛፍ
ላይ ቁጭ ብሎ አደረ ። ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን
ስታየው እልልታዋን አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት ።
ከእንቅልፉ የነቃው ባል በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት
ገብታ ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀችው "ይህ የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ
ሁለተኛው" ብላ እንግዲህ የመጨረሻው ምክር የልጆቹን ነፍስ ከማጥፋት
እረዳው ማለት ነው ። ሰውዬው ሶስቱ የሽማግሌው አባት ምክሮች በደስታ
ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል አደረጉት ።
# ስለዚህ_ወዳጄ_ሆይ_አንተም_በህይወት_ስትኖር ፦
1. አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ
2. በማያገባህ አትግባ
3. ክፉ ለማድረግ አትቸኩል
እኔኔ ተመስጨ ነው ያነበብኩት ደስ እሚል ትምህርት አለው አንብቡት!
ይጠቅማችዋል
መልካም ጊዜ

01/12/2021

ሩሲያ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚሞከር ጣልቃ ገብነትን አስጠነቀቀች
ኅዳር 22/2014 (ዋልታ) ሩሲያ ከመጀመሪያውም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ
የምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር አስጠንቅቄያለሁ አለች።
በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ፌደሬሽን ተልዕኮ ተቀዳሚ ምክትል ተጠሪ
ዲሚትሪይ ፖለንስኪይ "ከጅምሩ ምዕራባዊን ወዳጆቻችን በኢትዮጵያ የውስጥ
ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡና ግልፅነት በጎደለው አካሄድ ምንም ዓይነት ድርጊትን
እንዳይፈፅሙ አስጠንቅቀናል" ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በጦርነቱ ውስጥ የውጭ ኃያል አገራት ቀጥተኛ ተሳትፎ
አለ ማለቱን በማስታወስ ይሄ ጉዳይ ለኢትዮጵያዊያን እጅግ ስስብለት (ትብ
ጉዳይ) መሆኑን ሩሲያ አስምራበታለች።
የትኛውም አሰላለፍ ግልፅ መሆን አለበት ሲሉም በእጅ አዙርና በድብቅ ዓላማን
ለማስፈፀም መሞከርን ኮንነዋል።

27/09/2021

ጥልቅ ልዩነቶች ቢኖራቸውም ፣ የህዳሴው ግድብ አጥፊ ግድብ ነው በሚሉት
ነገር ላይ ተስማሙ! በዚህ መሠረት በአንድ ነገር ላይ እንኳን ቢሆን
የመስማማታቸው ምክንያት የሆነውን የህዳሴ ግድብ መገንባት ምክንያት
ለሆነችው ለሀገራችን በሥነ -ምግባር ህግ መሰረት ምስጋናቸውን ማቅረብ
አለባቸው! እና ዛሬ በግብፃዊው አል-ሸርቅ ቻናል ላይ ባደረግሁት ቃለ ምልልስ
በህዳሴው ግድብ ውስጥ ስለ እስራኤል እጆች መኖር አስገራሚ በሆነ መልኩ
ይጠይቁኛል! እኔም መለስኩላቸው:-በቅርቡ በእስራኤል-ፍልስጤም ጦርነት
ውስጥ ሸምጋዮች ነበራችሁ! እናም ጦርነቱን ያቆመበት ምክንያት እኛ ነን
ብላችኋል! እንደምትሉት ከሆነ እስራኤል ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ያላትን ጦርነት
ከማቆም ይልቅ ህልውናችሁን አደጋ ላይ የሚጥል ጥማትን ለማቆም የበለጠ
ችሎታ ሊኖራችሁ ይገባ ነበር ? እንዲሁም አሁንም እንደምትሉት ከሆነ እስራኤል
በጦርነት ላይ የእናንተን ሽምግልና ከተቀበለች የእሷ አጋሮች በሚያደርጉባችሁ
የውሃ ጦርነት ላይ ሽምግልናችሁ መስራት ነበረበት?
እኔም ከንደገና ጠየኳቸው - ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ላይ የደገፏትን ማንነት
ያልገለፀችው ካይሮን ፈርታ ነው ለማለት ነው?
ወይስ እስራኤል በሕዳሴው ግድብ ውስጥ ያላትን ሚና ያልገለፀችው ግብፅን
ፈርታ ነበር?
አብሮኝ የቀረበው እንግዳ ኢትዮጵያ ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነው የህዳሴውን
ግድብ የገነባችው ብሎ ተናገረ! እኔም እንዲህ ብየ መለስኩለት: ያቀረብከው
ክስ የሚያሳየው ሀገርህ በ2015 የተፈራረመችው ምንም በማታውቀው ነገር
ላይ ነው እያልክ ነው ታድያ ሀገራችን እዚህ ላይ ምን አጠፋች? ክሶቹ ብዙ
ቢሆኑም ነገር ግን ሁሉም ውድቅ ነበሩ!
ብዙዎቻቸው በእነሱ እና በመንግስቶቻቸው መካከል ያለውን የፖለቲካ ጠቦች
በኢትዮጵያ ላይ ተመርኩዘው መቀጠል ዓላማ እንዳላቸው ነገርኩት እኛም
በፍፁም የማንቀበለው መሆኑን አጥብቄ አሳሰብኩት።
ﺇﺗﻔﻘﻮﺍ ﺭﻏﻢ ﺧﻼﻓﺎﺗﻬﻢ ﺍﻟﻌﻤﻴﻘﺔ ﻋﻠﻰ ﺃﻥ # ﺳﺪ _ ﺍﻟﻨﻬﻀﺔ ﻫﻮ ﺳﺪ ﺍﻟﺨﺮﺍﺏ ﻛﻤﺎ
ﻳﺰﻋﻤﻮﻥ ! ﻭﻋﻠﻴﻪ ﻓﺈﻧﻪ ﻳﺘﻮﺟﺐ ﻋﻠﻴﻬﻢ ﺃﺩﺑﻴﺎ ﺃﻥ ﻳﻘﺪﻣﻮﺍ ﺷﻜﺮﻫﻢ ﻟﺒﻼﺩﻧﺎ ﺍﻟﺘﻲ ﺷﻴﺪﺕ
ﻟﻬﻢ ﺳﺪﺍ ﻛﺎﻥ ﻭﻻ ﻳﺰﺍﻝ ﺳﺒﺒﺎ ﻓﻲ ﺍﺗﻔﺎﻗﻬﻢ ﻭﻟﻮ ﻋﻠﻰ ﺃﻣﺮ ﻭﺍﺣﺪ !
ﻭﻓﻲ ﻟﻘﺎﺋﻲ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﻴﻮﻡ ﻋﻠﻰ ﻗﻨﺎﺓ ﺍﻟﺸﺮﻕ ﺍﻟﻤﺼﺮﻳﺔ
ﻳﺴﺄﻟﻮﻧﻨﻲ ﻋﻦ ﻣﺰﺍﻋﻤﻬﻢ ﺍﻟﻤﺜﻴﺮﺓ ﺣﻮﻝ ﺍﻷﻳﺪﻱ ﺍﻹﺳﺮﺍﺋﻴﻠﻴﺔ ﻓﻲ ﺳﺪ ﺍﻟﻨﻬﻀﺔ !
ﺃﺟﺒﺘﻬﻢ ﻗﺎﺋﻼ ﺃﻧﺘﻢ ﻭﺳﻄﺎﺀ ﻓﻲ ﺍﻟﺤﺮﺏ ﺍﻹﺳﺮﺍﺋﻴﻠﻴﺔ ﺍﻟﻔﻠﺴﻄﻴﻨﻴﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﺣﺪﺛﺖ
ﻣﺆﺧﺮﺍ ! ﻭﻛﻨﺘﻢ ﺳﺒﺒﺎ ﻟﻮﻗﻒ ﺍﻟﺤﺮﺏ ﻛﻤﺎ ﺗﺰﻋﻤﻮﻥ ! ﻓﻬﻞ ﻛﻨﺘﻢ ﺃﻗﺪﺭ ﻋﻠﻰ ﺇﻳﻘﺎﻑ ﺣﺮﺏ
ﺑﻴﻦ ﺷﻌﻮﺏ ﺃﺧﺮﻯ ﻣﻊ #ﺇﺳﺮﺍﺋﻴﻞ ﻣﻦ ﺇﻳﻘﺎﻑ ﻋﻄﺶ ﻳﻬﺪﺩ ﻭﺟﻮﺩﻛﻢ ﻭﻭﺟﻮﺩ
# ﺍﻟﺴﻮﺩﺍﻥ ﻛﻤﺎ ﺗﺰﻋﻤﻮﻥ ؟
ﻭﻫﻞ ﻛﺎﻧﺖ # ﺇﺳﺮﺍﺋﻴﻞ ﺃﻗﺒﻞَ ﻟﺸﻔﺎﻋﺘﻜﻢ ﻓﻲ ﺣﺮﺏ ﺗﺸﻨﻬﺎ ﺑﺬﺍﺗﻬﺎ ﻣﻦ ﺷﻔﺎﻋﺘﻜﻢ ﻓﻲ
ﺣﺮﺏ ﻣﻴﺎﻩ ﻳﺸﻨﻬﺎ ﻋﻠﻴﻜﻢ ﺣﻠﻔﺎﺅﻫﺎ ؟
ﻭﺳﺄﻟﺘﻬﻢ ﻣﺠﺪﺩﺍ : ﻭﻫﻞ ﺧﺸﻴﺖ # ﺇﺛﻴﻮﺑﻴﺎ ﻣﻦ # ﺍﻟﻘﺎﻫﺮﺓ ﻣﻦ ﺍﻹﻓﺼﺎﺡ ﻋﻦ ﺩﺍﻋﻤﻴﻬﺎ
ﻓﻲ #ﺳﺪ _ ﺍﻟﻨﻬﻀﺔ ؟
ﺃﻡ ﺧﺸﻴﺖ ﺇﺳﺮﺍﺋﻴﻞ ﻣﻦ # ﻣﺼﺮ ﺃﻳﻀﺎ ﺑﺸﺄﻥ ﺍﻹﻓﺼﺎﺡ ﻋﻦ ﺩﻭﺭﻫﺎ ﺍﻟﻤﺰﻋﻮﻡ ﻓﻲ ﺳﺪ
ﺍﻟﻨﻬﻀﺔ ؟
ﻭﺯﻋﻢ ﺍﻟﻀﻴﻒ ﺑﺄﻥ #ﺇﺛﻴﻮﺑﻴﺎ ﻗﺎﻣﺖ ﺑﺘﺸﻴﻴﺪ ﺳﺪ ﺍﻟﻨﻬﻀﺔ ﺩﻭﻥ ﺇﺧﻄﺎﺭ ﻣﺴﺒﻖ !
ﻓﺄﺟﺒﺘﻪ ﺑﺄﻥ ﺍﺗﻬﺎﻣﻪ ﻫﺬﺍ ﻳﻌﻨﻲ ﺗﻮﻗﻴﻊ ﺑﻼﺩﻩ ﻋﻠﻰ ﺃﻣﺮ ﻻ ﺗﻌﺮﻑ ﻋﻨﻪ ﺷﻴﺌﺎ ﻭﻟﻢ ﺗﺘﻠﻘﻰ
ﺑﺸﺄﻧﻪ ﺇﺧﻄﺎﺭﺍ ﻋﻠﻰ ﺣﺪ ﻭﺻﻔﻪ ! ﻓﻤﺎ ﺫﻧﺐ ﺑﻼﺩﻧﺎ ؟
ﻛﺎﻧﺖ ﺍﻹﺗﻬﺎﻣﺎﺕ ﻛﺜﻴﺮﺓ ﻭﻟﻜﻨﻬﺎ ﺩﺣﻀﺖ ﺟﻤﻴﻌﻬﺎ !
ﺫﻛﺮﺕ ﻟﻪ ﺑﺄﻥ ﺍﻟﻜﺜﻴﺮﻭﻥ ﻣﻨﻬﻢ ﻫﺪﻓﻬﻢ ﺗﺼﻔﻴﺔ ﺍﻟﺤﺴﺎﺑﺎﺕ ﺑﻴﻨﻬﻢ ﻭﺑﻴﻦ ﺃﻧﻈﻤﺘﻬﻢ
ﺍﻟﺴﻴﺎﺳﻴﺔ ﻋﻠﻰ ﺣﺴﺎﺏ # ﺍﺛﻴﻮﺑﻴﺎ ﻭﻫﺬﺍ ﻣﺎﻻ ﻧﻘﺒﻞ ﺑﻪ ﺇﻃﻼﻗﺎ !
# ኢትዮጵያ
# Ethiopia
# GERD
# Sudan
# Egypt
# Israel

የደቡብ ዕዝ ለሽብርተኛው ሸኔ ሊደርስ የነበረ ህገ-ወጥ ምግብና መድሃኒትበቁጥጥር ስር አዋለ********************************የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መነሻውን ነገሌ ቦረና...
27/09/2021

የደቡብ ዕዝ ለሽብርተኛው ሸኔ ሊደርስ የነበረ ህገ-ወጥ ምግብና መድሃኒት
በቁጥጥር ስር አዋለ
********************************
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መነሻውን ነገሌ ቦረና አድርጎ ለሽብርተኛው ሸኔ
ሊደርስ የነበረ ልዩ ልዩ ህገወጥ ምግብና መድሃኒት በቁጥጥር ስር ማዋሉን
ገለጸ።
ኮድ 3 አዲስ አበባ 93520 ኤፍኤስአር በሆነ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሽብርተኛው ሸኔ
በብዛት በሚንቀሳቀስበትና በምዕራብ ጉጂ ዞን በምትገኘው ሰራንሰር ቀበሌ
መዳረሻውን ያደረገው ይህ ህገወጥ ክምችት ከምግብና ከመድሃኒት ይዘቶች
በተጨማሪ ብዛት ያላቸውን ደረቅ ብስኩቶች፣ የተለያዩ የገላና የልብስ
ሳሙናዎች፣ ፍራሾች፣ ጤፍ እና ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችን በውስጡ ይዟል።
የደቡብ ዕዝ የኋላ ደጀን አስተባባሪ ኮሎኔል ግርማ አየለ ይህ ህገወጥ ክምችት
ሃይለስላሴ በተባለ የትግራይ ተወላጅ አስተባባሪነት ለሽኔ ቡድን እንዲደርስ
የተዘጋጀና በጉዞ ላይ እንዳለ በቁጥጥር ስር የዋለ እንደሆነ አስረድተዋል።
አካባቢው ተደጋጋሚ ህገወጥ ተግባራት በብዛት የሚከናወኑበት ቀጠና በመሆኑ
ከዚህ ቀደም በርካታ የኮንትሮባንድና የገንዘብ ዝውውሮችን በቁጥጥር ስር
እንዲውሉ መደረጉን ኮሎኔል ግርማ ተናግረዋል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብና የመድሃኒት ክምችት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ
የሚገመት መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ ህገወጥ ተግባር ተሳታፊ በመሆን በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ትንሹ
ጠዴቻ፣ ወጣት ወዴሳ ዲዶ እና ወጣት ጉየ ሁንዴ የሽብርተኛው ሸኔ ቡድን
አመራር ከሆነና ጅማ ከተባለ ሰው ተልከው ሃይለስላሴ ከተባለ የትግራይ
ተወላጅ የተለያዩ የምግብ አቅርቦቶችን ይዘው እንዲመጡ ትዕዛዝ
መቀበላቸውንና ትዕዛዙን መፈፀም ካልቻሉ ግን እንደሚገደሉ እንደተነገራቸው
መግለጻቸውን የደቡብ ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን
ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
የመዝናኛ ቻናላችን የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ የመዝናኛ
ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCp9pS23Vw1n8Wpc
pZBDJNmA
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን
ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

27/09/2021

Eritrean cyclist becomes the first black African to win in World
Championship
- Africa to host the world championship for the first time in
2025.
24 Sep 2021 – (EP) History maker Biniam Girmay hailed a
landmark moment for Eritrea and all of Africa after winning the
silver medal in the U23 men's road race at the UCI Road World
Championships.
The 21 years old rising star burst clear of a reduced bunch to
place second in Leuven, just a couple of seconds after solo
winner Filippo Baroncini. In doing so, he made history,
becoming the first Eritrean and the first black African to win a
medal at the Road World Championships.
"For me, for my nation, also for Africa, this means a lot,"
Girmay said as his section of the post-race press conference
outlasted that of the world champion to his left.
"I'm really happy. I'm really proud of my nation, so I say
congrats to all Eritreans and also to all Africans."
He made his name as a future cycling star when he took a
clean sweep of the African national championships in 2018.
After helping his country to the team time trial relay, he
romped to the individual TT title by almost a minute and then
won the road race title from a two-up sprint.
Biniam is the newest of the Eritrean World Tour group after
signing for the Belgian Intermarché-Wanty-Gobert last month.
His first win for them came soon afterward at the Classic
Grand Besançon Doubs after he made it into a group of
attackers that included Thibaut Pinot and Nairo Quintana.
Meanwhile, Africa will host the world championship for the
first time in 2025, with the sport's governing body the UCI
rubber-stamping Rwanda Capital Kigali's candidacy on Friday.

Address

Hosanna

Telephone

+251918659093

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share