25/07/2025
በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም ማጠቃለያ ክንውን ሪፖርት ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ተገመገመ።
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''ሐምሌ 18/2017 ዓ/ም
*****************የዱና ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት
የመድረኩ አስፈላጊነቱን በተመለከተ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ክንውን ሪፖርት ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት መሆኑን የዱና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ገልጿል።
የዱና ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደዊት ጥጌቦ እንደገለፁት፥የተቋሙን አፈጻጸም ከፍ ለማድረግ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን መገምገም እንዲሁም ክፍተቶችን በማረም ለቀጣይ ዕቅድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የየራሳቸዉን ድርሻ ወስደው በተጠናከረ መልኩ መሥራት እንደሚገባቸው በመግለጽ መድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የተግባር ሥራ አፈጻጸምና የ2018 እቅድ ለማቀድና ለመተግበር እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ አብራርተዋል።
በግምገማ መድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፓርት የጤና ጽ/ቤት ሁሉም የዘርፉ አስተባባሪዎች እንደየዘርፋቸዉ አቅርበዋል።
ከተሳታፊዎች መካከል እንዳነሡት የ2017 በጀት ዓመት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መነሻ በማድረግ በቀጣይ አቅጣጫ ግቦችን ለማሳካት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባቸው አስተያየት ተሠጥቶ የዕለቱ ዉይይት ተጠናቋል።
በመድረኩ የዱና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደዊት ጥጌቦ ፣ የዱና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ እዉቀቱ ደስታ፣የጤና ጽ/ቤት ማኔጅመንት አባላት፣ባለሙያዎች፣የጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና የቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ፎካሎች ተገኝተዋል።
ዘገበው የዱና ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።