15/10/2022
?
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ሰላም እንደምናችሁ ዛሬ አንድ እውነት በአእምሮዬ ሲመላለስ ዋለና ይህችን ልጽፍ አነሳሳኝ, ብዙ ጊዜ ሰዎች መስራት ያልቻሉትን ነገር ወይንም ሞክረው ሞክረው ያቃታቸውን አንተ ስትሰራ እንዲሁም ስኬታማ ስትሆን ካንተ ከመማር ይልቅ ለምን እንዴት በማለት ላንተ ከጎንህ ከመቆም ይልቅ አብረው እየበሉ እየጠጡ አርቀው መቀበሪያህን በመቆፈር ምቹ ሰዓትና ጊዜ ይጠብቃሉ! ደግሞ አንተ በፈጣሪ እርዳታ ከተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥም ሆነህ ወርቅ ይዘህ ትወጣለህ ጉድጎዱን ስታዳፍነው እንደ አነር እና ጅግራ ይሆናል!
አነር አንዱ የድመት ወይንም የነብር ዝርያ ሲሆን አንድ ቀን በጣም ይርበውና በዱር ውስጥ የሚበላ ሲያፈላልግ አንድ የቆቅ ዝርያ የሆነች ጅግራ የምትባል አእዋፍ አንድ ጥሻ ውስጥ ተኝታ ያያታል! ታዲያ አነሩ ቀስ እያለ ድምጹን አጥፍቶ ሲጠጋት ይህች ጅግራ ደግሞ በእንቅልፍ ውስጥም ሆና የመስማት እና እራሷን የማትረፍ የሕይወት ክህሎት ስላላት አንዳቻች አካል እየተጠጋት መሆኑን ስለተረዳች ከነበረችበት ተፈተለከች አነሩም በንዴት ቢያሯሩጣት ቢያሯሩጣት ሊይዛት ስላልቻለ ብሎ ጥሏት ሄደ!
አንተም የተቆፈረውን ጉድጓድ ደፍነህ በድል ደልድለህ ስትቆም ቀባሪዎችህ እና ክፉዎች እንደ አነር ትተውህ ይሄዳሉ! ግን ደግሞ አነር ሌላ በሀሪ አለው ተስፋ ሳይቆርጥ ማድፈጡንና ምቹ ሰዓትን ጠብቆ ለመጉዳት ስለሚፈልግ ሁሌም እንደ ጅግራዋ ነቃ ማለት ይጠበቅብሀል!
አንተ ትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር ከማድረግ ወደኋላ ማለት አይገባህም! በይሉኝታ ታፍነህ በውለታ ተተብትበህ ሰዎች ማድረግ እና መስራት ያቃታቸውን ህሊናህን እያመመህ እና እየቆረቆረህ አትተወው የቻልከውን ማድረግ የሚገባህን ስለ እውነት ብለህ አድርግ ሰዎች ሊናደዱ ሊበሳጩ ይችላሉ አንተ ግን ስራህን አታቁም ነገ እውነታው የገባው አንድም ቢሆን የሚበቅል ቡቃያ ታገኛለህ! ያ ቡቃያ ደግሞ ነገ ፍሬ ስለሚያፈራ ተስፋ አትቁረጥ!
!