የሃዲያ ልጆችና ወዳጆች ሚዲያ

  • Home
  • የሃዲያ ልጆችና ወዳጆች ሚዲያ

የሃዲያ ልጆችና ወዳጆች ሚዲያ ሚዲያው የሃዲያ እና የሃዲያ ወዳጆችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖሎቲካዊ እሴቶችን ይዳስሳል፤ አዳዲስ መረጃዎችንም በፍጥነት ያደርሳል።

 ! 📸  Butisha
01/06/2025

!
📸 Butisha

 !በዓለ ሆሳዕናን በሆሳዕና ከተማ ሃማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።
13/04/2025

!

በዓለ ሆሳዕናን በሆሳዕና ከተማ ሃማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።

ርዕሰ መስተድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት  የክላስተር ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ ማኖሪያ መረሀ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል...
09/03/2025

ርዕሰ መስተድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የክላስተር ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ ማኖሪያ መረሀ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፤

ሆሳዕና ፡ የካቲት 30/2017ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ዶ/ር በክልሉ በ 7ቱም የክላስተር ማዕከላት ለአገልግሎት መስጫ ህንፃ ግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ በዛሬ ዕለት በሆሳዕና ከተማ ያኖራሉ፡፡

መረሀ ግብሩ በአራት ነጥብ ሶስት ቢሊየን ብር በሆሳዕና ፡ ቡታጅራ ፡ ወራቤ ፡ ወልቂጤ ፡ ቁሊቶ ፡ ዱራሜና ሳጃ ከተሞች ነው የአገልግሎት መስጫ ቢሮ ህንፃዎቹ ግንባታ ለማስጀመር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን፣የክልልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ፍጤ ሰርሞሎ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፤ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱን ጨምሮ የክልሉ አስተባባሪ አካላት እና የሀዲያ ዞንና የሆሳዕና ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ወንድማማቾችን በፍቅር ያገናኘ ታሪካዊ ዝግጅት በውቢቷ ሻሸመኔ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።የሻሼዎች እንግዳ ተቀባይነት ከወትሮ ለይት ብሎብኛል። የነበረው የደስታ ድባብም ምናለ እንዲህ ዓይነት የቤ...
15/02/2025

ወንድማማቾችን በፍቅር ያገናኘ ታሪካዊ ዝግጅት በውቢቷ ሻሸመኔ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የሻሼዎች እንግዳ ተቀባይነት ከወትሮ ለይት ብሎብኛል። የነበረው የደስታ ድባብም ምናለ እንዲህ ዓይነት የቤተሰብ ጥየቃ በየዓመቱ በኖረ ያስብላል። በአጠቃላዩ በዝግጅቱ ኢትዮጲያዊነት በተደጋጋሚ የተነሳበት የሃዲያ አንድነት የታየበት፣ የሃዲያና የኦሮሞ ህዝብ ወንድማማችነት የተመሠከረበት ነበር።

ይሄን ዝግጅት ላዘጋጁና ላስተባበሩ የሻሸመኔ ቤተሠቦች ምስጋናችን ወደር የለውም።

 ዘፈን መዝፈን እንደ ነውር በሚታይበት አከባቢና ዘመን ቦያ ሰለሜን ጨምሮ እጅግ ተወዳጅ የሆኑትን ዘፈኖች በመዝፈን  ሃዲያን ከተቀረው ዓለም ጋር ያስተዋወቀ ተወዳጅ አርቲስት፤ በኮሎኔል በዛብ...
09/02/2025


ዘፈን መዝፈን እንደ ነውር በሚታይበት አከባቢና ዘመን ቦያ ሰለሜን ጨምሮ እጅግ ተወዳጅ የሆኑትን ዘፈኖች በመዝፈን ሃዲያን ከተቀረው ዓለም ጋር ያስተዋወቀ ተወዳጅ አርቲስት፤

በኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ሀውልት ምርቃት ዕለት ጨምሮ በተለያዩ ውቅት በጥበባቸው ያዝናኑን፣ በችሎታቸው ያስደመሙን፣ የህዝቡን ስሜት በመኮርኮር ያስለቀሱንን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አርቲስቶችን በኪነ ጥበቡ ዘርፍ አስተምሮ ያበቃ ምርጥ መምህር፤

የብሄር ብሄረሰቦች የባህል ልብስ መልበስ እንደዘረኝነት በሚታይበት በዛን ዘመን የሃዲያን የባህል ልብስ /ሰሬዋናን በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በመልበስ ያስተዋወቀ የባህል አምባሳደር፤

በሃዲያ ህዝብ ዘንድ የማይፋቅ አሻራ ጥሎ ያለፈ ነገር ግን የሚገባውን ክብር ያላገኘ ጀግና አርቲስት፣ መምህርና የባህል አምባሳደር አቡሎ ጡሞሮ በህይወት ዘመኑ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች በርካታ ስራዎችን ሰርቶ የለፈን ባለውለታ የሚገባውን ክብር ባለመስጠታችን ምን ይሰማን ይሆን?

በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለዞናቸው የባህል እድገት አበርክተዋል በሚል የክብር ዶክተሬት የሚሰጣቸው አርቲስቶች ከዚህ አርቲስቲ የተሻለ ስራ ስለሰሩ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? ባለቤቱ የናቀው... እንደሚባለው እንዳይሆን ነገሩ ዋቸሞ ዪኒቨርስቲ፣ የሃዲያ ዞን አስተዳደር፣ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በመነጋገር ለዚህ ታላቅ ባለሙያ በአጭር ጊዚያት ውስጥ የሚገባውን ክብር ይሰጡታል የሚል ሙሉ እምነት አለን።

ጀግናችን ነፍስህ በሰላም ትረፍ!🙏🙏🙏

የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የምክር ቤት አባለት ምርጫ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መንገድ አካሂዷል።በዚሁ መሰረት ከሀዲ...
03/02/2025

የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የምክር ቤት አባለት ምርጫ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መንገድ አካሂዷል።

በዚሁ መሰረት ከሀዲያ ዶ/ር ድላሞ ኦቶሬ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

እንዲሁም አቶ መለሰ ዓለሙ ፣ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ አቶ አክልሉ ታደሰ እና አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ከሀዲያ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባለት ሆነው ተመርጠዋል።

መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ !!

" " የፎንቆ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን በማስተባበር የገቢ ማሰባሰብያ የተለያዩ  ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።የገቢ ማሰባሰቢያ የማጠቃለያ ቴሌቶን ዝ...
22/12/2024

" "
የፎንቆ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን በማስተባበር የገቢ ማሰባሰብያ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

የገቢ ማሰባሰቢያ የማጠቃለያ ቴሌቶን ዝግጅትን ታህሳስ 20/2017 ዓ/ም በፎንቆ ከተማ ስለሚያደርግ ሁላችንም የሃዲያ ልጆች እንዲህ ዓይነት የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ታሪክ እንስራ! በዚህ የተቀደሰ ስራ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሃዲያ ልጆችና ወዳጆች ከስር በተዘረዘሩት የባንክ አካውንት ቁጥሮች የድርሻዎትን ይወጡ!
👇👇
CBE #1000662253198
WOGAGEN 0833047230102
NIB 7000065642161
Awash 013201087207401

#ኑ ሁላችን ተባብረን ከተሞቻችንን እንገንባ!

ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን አጎልብተን ከተባበርን አይደለም ሆሳዕናን መላው የሃዲያ ከተሞችን ከዚህ በላይ ውብ አድርገን እንሰራለን!በሆሳዕና ከተማ 36 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ የማስጀመ...
15/12/2024

ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን አጎልብተን ከተባበርን አይደለም ሆሳዕናን መላው የሃዲያ ከተሞችን ከዚህ በላይ ውብ አድርገን እንሰራለን!

በሆሳዕና ከተማ 36 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ የማስጀመር መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

@ምስሉ የኮሪደር ልማቱ ሲጠናቀቅ በሆሳዕና ከተማ አንዳንድ ቦታዎች ሊኖራቸው የሚችል ከፊል ገጽታ ነው።

ታህሳስ 06/2017 ዓ/ም
ሆሳዕና

30/11/2024
Atakaa'n hiimoo Fuliixxi hiimooአተካን ሂሞ እና ፉሊጥ ሂሞበሃዲያ ብሔር መስከረም 15  ውብ ባህላዊ ገጽታ ያለው ምሽት ነው። በዚህ ምሽት ከሚከወኑ ክዋኔዎች መካከል የአተካ...
25/09/2024

Atakaa'n hiimoo Fuliixxi hiimoo
አተካን ሂሞ እና ፉሊጥ ሂሞ

በሃዲያ ብሔር መስከረም 15 ውብ ባህላዊ ገጽታ ያለው ምሽት ነው። በዚህ ምሽት ከሚከወኑ ክዋኔዎች መካከል የአተካና ምግብ ዝግጅት እና ፉሊጥ ከጃ ተጠቃሽ ናቸው።

አተካና የራሱ የሆነ አዘገጃጀትና የአመጋገብ ሥርዓት ያለው ነው፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ምሽት ወጣቶች ቤት ለቤት እየዞሩ ያሆዴን ይጨፍራሉ፡፡ የያሆዴ በዓል ዋና መገለጫ የሆነዉ አተካና በቡላ ወይም በቆጮ ተዘጋጅቶ በባህላዊ መመገቢያ ቁሶች ማለትም በቢጥራና በእንሰት ቅጠል ተደርጎ በስርዓት ይቀርባል፡፡ ጎን ለጎን የቀንድ ማንኪያና ናቃሮ/ዳጣ/ አብሮ ቀርቦ ይመገባሉ፡፡ ወጣቶችም ከተመገቡ በኃላ ይመርቃሉ፡፡ ምሽቱን ሙሉ እየዞሩ ይጨፍራሉ ይመርቃሉ።
Hadiya.TV
Hadiya zone Government Communication Affairs Department የሀድያ ዞን የመ/ኮ/ጉ መምሪያ
Hadiya zone Culture and tourism department
Hadiya zone culture tourism& sport department
Mizan Media ሚዛን ሚዲያ
Hadiya Media Network-HMN
Feta Link ፈታ ሊንክ
Hadiyyi Lichchi Xaaxxitte - ሀድያ ልማት ማህበር - Hadiya Development Association

እንደው በያሆዴ ማግስት በመስቀል ዋዜማ በዚህ ዓመት ወይም ከአሁን በኋላ የሃዲያ ልጆች ቢሆንልን ብዬ የማስበውን ነገር ለዓመታት የትግል ሜዳዬ በሆነችው ገጼ ላይ ላስፍር። የሃዲያ አባቶች ለዓ...
25/09/2024

እንደው በያሆዴ ማግስት በመስቀል ዋዜማ በዚህ ዓመት ወይም ከአሁን በኋላ የሃዲያ ልጆች ቢሆንልን ብዬ የማስበውን ነገር ለዓመታት የትግል ሜዳዬ በሆነችው ገጼ ላይ ላስፍር።

የሃዲያ አባቶች ለዓመታት በትግል አስከብረው ያቆዩልንን አንድነታችንን ለማስቀጠል በራችንን ዘግተን የመመካከር፣ የመነጋገር፣ ይቅር የመባባል፣ ለችግሮቻችን መፍትሄ የማበጀትና ተባብሮ በመስራት በተለያዩ ችግርና ፈተና ውስጥ ለዓመታት የተበደለውን ህዝባችንን በልማቱ የመካስና እና የማስደስት ዘመን ቢሆንልን ደስ ይለኛል!

ይኼን ከላይ ያሰፈርኩትን ሀሳብ የማይደግፉ፣ እንዳይሆንም ባለ ባሌለ አቅማቸው የሚታገሉ እነማን ናቸው የሚለውን መለየት ተገቢ ግን ይመስለኛል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባለኝ የዓመታት ልምድ በፌክ አካውንት ጭምር ሃዲያን የሚበጠብጡ አብዛኞቹ የሃዲያን ሰላም፣ ዕድገት፣ ልማትና አንድነት የማይፈልጉ ሃዲያ ያልሆኑ ከሃዲያ ዞን ውጭ የሚኖሩ ከ4 እና 5 የማይበልጡ ግለሰቦች ሲሆኑ በብሄር ሃዲያ የሆኑ ለራሳቸው እንጂ ለሃዲያ ጭራሽ የማይጨንቃቸው ጥቂት የኛ ሆዳሞችም ይገኙበታል።

የሃዲያ ምድር የእምነት፣ የተስፋና የፍቅር ምድር ናት። በመንፈሳዊ ዓለም በሁሉም ሃይማኖቶች ፀሎት በማድረግና ፈጣሪዋን በመለመን የሚደርሳትም የለም። በፖሎቲካውም ቢሆን እንደ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሀሳብ ሞግቶ የሚያሸንፍ ጀግና የፈጠረች ወደፊትም የምትፈጥር የተባረከች አከባቢ ናት። እና ለምንድነው በራችንን ዘግተን ከመነጋገር ይልቅ በየጥጋጥጉ ጫጫታ የምናበዛው? በችግር ውስጥ የሚኖረውን ህዝባችንን ሠላም የምናውከው? ለትንሹም ለትልቁ ኡኡኡኡ ማለት መጮኽ፣ ማስጮኽ የምናበዛው? ደግሞም እኮ ሃዲያ ያልሆኑ ሰዎች በሚሰጡን ሰላም አደፍራሽ አጀንዳዎች ነው መደማመጥ ያቃተን!

እስቲ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች፣ እልኽኞች፣ የጎሳ ነፃ አውጪዎች ሰከን እንበልና ወደራሳችን እንመለስ! (ሁሉም ሃዲያ እኮ አንድ ነው አንተ ከማነው ማንን ነፃ የምታወጣው? እስቲ ወንድ ከሆንክ እኔ ተውልጄ ያደኩበት አከባቢ በሞጋሳ ኦሮሞ የሆኑ ሃዲያዎችን ነፃ አውጣ!)

አባቶቼ ሽማግሌዎች እስቲ ታሪክ ስሩ የተጣሉ ካሉ አስታርቁ፣ ያጠፋውንም ቅጡ፣ የተበደለ ካለ እንዲካስ አድርጉ፣ ከሰፈርና ጎጣ ጎጥ ውጡ ልጆቻችሁንም አስወጡ፣ ወደ ክልልና የሀገር ሽማግሌነት ከፍ በሉ፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አጥፍተው ፣ እንደቀደምት የሃዲያ አባት ሽማግሌዎች ለእውነት ሙቱ፣ ይሄ የእውነት፣ የፍቅርና የአንድነት መንገድ ብቻ ነው ሊያፀድቃችሁ እንኳ የሚችለው!

ሙሁራን ሆይ ዝምታ ገዳይ መሆኑን እንዳትረሳ፣ ለመናገር ክፉን ለመገሰጽም በጭራሽ አትፍራ! ከጎጥ ከሰፈርም ውጣ፣ ጎረቤቶችህ እየተጣሉም እየተፋጩም የህዝባቸውን አንድነት አስጠብቀው የአባቶቻቸውን አደራ እየተወጡ ይገኛሉ። ተባብረውና አስተባብረው የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየሰሩ ለትውልድ የሚተላለፍ ድንቅ ስራ በመስራት ታሪክ እየፃፉ ይገኛሉ። አንተስ የት ነህ??? ምንስ እየሰራህ ነው???? እውነቴን ነው የምልህ ከሞት የማይተናነስ እንቅልፍ ውስጥ ተኝተሀል። ለዚህም ማሳያ ከ10 ዓመት በላይ የተጀመረ የባህል ማዕከል ግንባታህ የሚያየው ጠፍቶ እየፈረሰልህ ይገኛል።

እንግዲህ እኔ ጨርሻለሁ ማለቴ የዛሬውን ነው። ጽሁፉም ለጥቂት አፈንጋጮች የተፃፈ ነው። ጨዋ የሃዲያ ልጆችን እንደማይገልጽ ይሰመርበት። አንተም ከቤራ ነኝ ባይ እወነተኛ ከቤራና ሃዲያ ከሆንክ ቁጭት ይሰማህና የአንድነት ጎራ ላይ ተቀላቀል። አንተኛው የሃዲያ እንድነት ፀር ከሆንክ ደግሞ በዛ በሚቀረሸው በጎሰኝነት ግም አፍህ ስደበኝ። እኔ ደግሞ ማንነትህን ሁሉ ሳይቀር በመግለጽ በሃዲያ ስም እምላለሁ እጠራርግሀለሁ።

መልካም በዓል ይሁንልን
አንድ ሃዲያ!

በሃዲዮማ የማይደራደር ምርጥ ቤተሰብ!  kiina Shomoro ፈጣሪ አንተንና ቤተሰብህን ይባርክ! ልጆችህንም ያሳድግልህ! ! Mizan Media ሚዛን ሚዲያ Feta Link ፈታ ሊንክ
23/09/2024

በሃዲዮማ የማይደራደር ምርጥ ቤተሰብ!
kiina Shomoro ፈጣሪ አንተንና ቤተሰብህን ይባርክ! ልጆችህንም ያሳድግልህ!
!
Mizan Media ሚዛን ሚዲያ Feta Link ፈታ ሊንክ

Address


Telephone

+251979920436

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሃዲያ ልጆችና ወዳጆች ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የሃዲያ ልጆችና ወዳጆች ሚዲያ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share