NO PEACE NO WAR

NO PEACE NO WAR Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from NO PEACE NO WAR, Digital creator, ወራቤ, Hossana.

RIP
15/09/2025

RIP

❗️ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር የት አለፈ ?

" ዘንድሮ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እየተገለጸ ይገኛል።

በዘንድሮ አመት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል ተብሏል።

ከፍተኛ ተማሪዎችን ያሳለፉ ክልሎች ፦
- አዲስ አበባ፣
- ሐረሪ
- አማራ ክልል ናቸው።

ዘንድሮ " የተፈታኙ ቁጥር ቀንሷል ያለፈው ተማሪ ቁጥር ግን ጨምሯል " ያሉት ትምህርት ሚኒስትሩ ዘንድሮ በአጠቃላይ 48,929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው አመት ያለፈው ተማሪ ቁጥር 36,409 ነበር።

በጾታ ስብጥር ፦
30,451 ወንድ ተማሪዎች አልፈዋል።
18,478 ሴት ተማሪ አልፏል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት

ወንድ 591/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
ሴት 579/600 ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ
ወንድ 562/600 አምቦ አምቦ ቦርዲንግ ስኩል።
548 /600 ሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት።

አማካይ ውጤት
71 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች
25.9 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች
30.6 በመቶ የመንግስት ትምህርት ቤቶች
51 በመቶ የግል ትምህርት ቤት ውጤት

https://t.me/+uXs4lxNd76QyMThk

ሳንኩራ,ዳሎቻ*ሁልባራግ እና ምዕ/አዘርነት ወረዳዎች ላይ የ2017ዓም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የለም ነዉ ወይ ዝም ጭጭ ብለዋል !!!!
15/09/2025

ሳንኩራ,ዳሎቻ*ሁልባራግ እና ምዕ/አዘርነት ወረዳዎች ላይ የ2017ዓም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የለም ነዉ ወይ ዝም ጭጭ ብለዋል !!!!

16/08/2025
16/07/2025
27/05/2025

# #«210 የሞሪታኒያ ሑጃጆችን አሳፍሮ ወደ መካ ሲጓዝ የነበረ ፕሌን ቀይ ባህር ላይ ተከስክሷል!» በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዟዟረ የሚገመው ዜና ውሸት ነው።

ሁሉም የሞሪታኒያ ሑጃጆች በሰላም ወደ ቅድስቲቷ ምድር ደርሰዋል። አል-ሐምዱ ሊላህ!

መረጃዎችን ከማሰራጨታችን በፊት እናጣራ። ከምናውቀው ሰው ቢፖሰቱ እንኳ ማስረጃና መረጃ መኖሩን ሳናረጋግጥ እኛም ጉዳዩን ወደማስተጋባት አንሂድ።

The rumor circulating about a Mauritanian pilgrims’ plane crashing off the Red Sea coast is false, the government has said.

Mauritania’s Director of Hajj at the Ministry of Islamic Affairs, El Waly Taha, denied the claim, confirming that all Mauritanian pilgrims are safe and have arrived in the holy lands without incident.

Likewise, Mauritania Airlines confirmed that all pilgrims were transported safely and securely to Saudi Arabia, with no incidents reported on any of the scheduled flights.

The company clarified that it operated three outbound flights for this year’s Hajj season.

||

በሳንኩራ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ በዛሬዉ ዕለት ዉይይት ማድረጉን በተለመደዉ የኮሚኒኬሽን ሚዲያ ለጥፏል ዉይይቱ አሪፍ ነዉ በተለይም አጀንዳዉ የሀገረመንግስት ግንባታና ሀገረ ግ...
27/05/2025

በሳንኩራ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ በዛሬዉ ዕለት ዉይይት ማድረጉን በተለመደዉ የኮሚኒኬሽን ሚዲያ ለጥፏል ዉይይቱ አሪፍ ነዉ በተለይም አጀንዳዉ የሀገረመንግስት ግንባታና ሀገረ ግንባታዉ ላይ የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ነዉ ሆኖም #በፖስቱ ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች የሚል ነገር አነበብኩና ወደ ፎቶዉ ሲሄድ የተለመደዉ የቀበሌ ስራአስኪያጅና የልማት ጣቢያ ባለሙያ &የስራ ዕድል ፈጣራና እንተርፕራይዝ ባለሙያዎችን አየሁ በጣም የሚገርመዉ ደሞ ወረዳዉ ላይ ከየት ይምጡ የማይታወቁ ደቃቃዎች ከፊትለፊት ደቅ ብሏል ሃሃሃ...ድንቄም ተሳክቶላት ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣት መረጠች አልኩ ¡¡

16/01/2025
08/01/2025

"እየበሉ ማውራት ሳይቻል አንዳንዴ
አወራሁ ለሆዴ ፣ አወራሁ በሆዴ "
ደጋፊ ወይም ተቃዋሚ መሆን መብት ነው ። የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው ሊባልም ይችላል። በበሉበት መጮህ ግን የቦቢ ተፈጥሮ ነው።
እና ምን መሰለህ : ብልፅግና ፍልስፍና የለውም። "ርዕዮተ ዓለም" አይደለም።
መደመር ማለት : የፅኑ ምኞት መቋጫ ቃል ነው እንጂ የተጠና የሂሳብ ስሌት አይደለም።

ኢህአዴግ :መርህ ነበረው። ክፉም ይሁን ደግ አጥፊም ይሁን አልሚ፣ የሚመራበት መርህ ፣ የምታጠናው ሀሳብ ፣ የምትመራመርበት ፍልስፍና ፣ አምነህ የምትጠመቅበት፣ አብዮታዊ ዴሞክረሲ የተባለ :" አብዮት እና ዴሞክራሲን ምን አገናኛቸው?" ብለህ ሳትጠይቅ፤ እንደሃይማኖት ተቀብለህ ፣ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ሶስትነት እና አንድነት አምነህ የምትጠመቅበት ስርዓት ነበረው።

ኢህአዴግን ፈጣሪዋ ህወሀት መሆኑን እያወቅክ፣ ይችው ህወሃት የወንድም ድርጅቶች እህት ሆና ስትመጣ፣ እንደ ፓርቲ ምስጢር ጠብቀህ፣ እንደ ማህተም በልብህ አኑረህ የምትሰለፍበት ከላይ ታች፣ ከላዕላይ እስከ ታህታይ የምጠነራረፍበት ገራሚ ሰንሰለትም ነበረው።

አፈንጋጭ ስትሆንም፣ እንደ ኮሪደር ልማት ፈርሰህ የምትታደስበት፣ አስደናቂ አፍርሶ መስሪያ ጥበቦች፣ ደንብ እና ስርዓትን ተከትሎ ሞጋች በሆኑ ሀሳቦች ማስተንተን የሚችል ተፈጥሮዋዊ ቁመና ነበረው።

አሁንስ አትለኝም? ፖለቲካ እና ፍልስፍና ጀርባ ተሰጣጥተዋል። ክርክር እና ውይይት ጠፍተው በማሳ ዙሪያ መንሸራሸር ዋና ስራ ሆኗል።

የማሳ ፖለቲካ፣ የጓሮ አትክልት እና የኮሪደር ልማቱ የሚሳለጠው: በመንገድ እና የትራንስፖርት ሚኒስተር እና በግብርና ሚኒስተር መስሪያ ቤቶች መሆኑ ቀርቶ የሀገሪቱ መሪ ዋነኛ ተግባራት ሆነው ተገኙ።

ህገመንግስቱ ተሻ ። የጠቅላይ ሚኒስትር የስራ ድርሻ ተዘነጋ፤ እሱ ብቻም አይደለም፣ ካድሬዎች የሚመገቡት ፍልስፍና ሲያጡ ሁሉንም ሀብት እንደ አንበጣ መመገብ ስራቸው ሆነ።

በደጉ ዘመን አንድ ካድሬ ስለ አብዮታዊ ዴሞክራሲ አበጥሮ የሚያስረዳህ እና የቤት ስራ መስጠት የሚችልበት አእምሮ ነበረው።

ያሁኖቹ ካድሬዎች ንግግር ባያውቁ አትፍረድባቸው። የጨበጡት ፍልስፍና ሳይሆን ገንዝብ ብቻ ነው። ለክተው የሚያውቁትየተሰጣቸውን መሬት ነው። ብልፅግና የሚያስጠናቸው መርህ፣ የሚግታቸው ፅንሰ ሀሳብ የለውም ። መሬት ሰጥቶ መሬት ያደርጋቸዋል። መሬት ተቀብሎ መሬት መሆንን የመሰለ አሸርጋጅነት የለም።

ያ እጆቹን አጣምሮ በደላችንን በዓለም አደባባይ የገለፀልን ፈይሳ ሌሊሳ፣ በክንዶቹ መሬት ለክተው ቢሰጡት: እጆቹን ደብቆ እግሮቹን አነሳብን።
ይሁና ከማለት ሌላ ምን ይባላል?
ላንዱ ምሬት ለሌላው መሬት እየሰጡ ማበላለጥ ግን ያስተዛዝባል።

አስራት ከገብረ ጉራቻ

Address

ወራቤ
Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NO PEACE NO WAR posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share