
18/09/2025
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እና የኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት የስራ ኃላፊዎች በሆሳዕና ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች ምልከታ እያደረጉ ነው
(ሆሳዕና፣መስከረም 8/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በክልሉ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ ነው።
ይህን ተከትሎም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሆሳዕና ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።
ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ በግንባታ ላይ የሚገኙ የክልል ተቋማት ፣የአብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም ግንባታ እና ሌሎች ለበአሉ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ የዝግጅት ስራዎችን አፈጻጸም ተመልክተዋል።
በልማት ስራ ምልከታው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣
በኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት የመንግስታት ግንኙነት የዲሞክራሲ አንድነት የህገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሀፊ ወ/ሮ ባንቺ ይርጋ መለሰ እና ሌሎች የክልል እና የፌደራል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተስፋዬ መኮንን
ለተጨማሪ መረጃ ‼️
📌 በዌብሳይት https://www.cergcab.et/
📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB
📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL
📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678
📌 በቲክቶክ tiktok.com/
📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/?si=Ipdg3R3A3hpPQEUV
📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !!