Yahode Events

Yahode Events ታማኝነት ለራሳችን

 #ያሳዝናል ከተወዳጁ ድምጻዊ ሙሉጌታ ሱጋሞ አንደበት # #አንዳዴ እንዲህ ነው !!👉 እንዴት እስቲ እንዴት ብትሉኝ.... በአንድ ማንነት ውስጥ እየኖርን ፣ ቢያንስ ሰው መሆናችን እየታወቀ ፣...
28/11/2024

#ያሳዝናል ከተወዳጁ ድምጻዊ ሙሉጌታ ሱጋሞ አንደበት
# #አንዳዴ እንዲህ ነው !!
👉 እንዴት እስቲ እንዴት ብትሉኝ.... በአንድ ማንነት ውስጥ እየኖርን ፣ ቢያንስ ሰው መሆናችን እየታወቀ ፣ የአብራካቸው ክፋይ ሆነን ሳለን እና ወገን ዘመድ ቤተሰብ እያለን በስራችን (በሙያችን) ምክንያት በነጻነት ለመኖር ሆነ ሰርተን ለማግኘት እንዴት እናንተ " የእንጀራ እናት ልጆች" ናችሁ ሲሉን መሆናችንን እንዴት አምኜ ልቀበል ......እውነት ነው ....ሳይሻገሩ ሊያሻግሩን በሚፈልጉ የሰዎች ማዕበል ውስጥ እንዳለሁ እንዲሰማኝ አድርገውኛል ... 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
👉👉👉 ለሁሉም ጊዜ አለው....
👉👉👉 እስካለን ሂወት ይቀጥላል...

 #የቀድሞ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው ዝና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአምባሳደራችን ሀዲያ ሆሳዕና መለዮ  እንዴት ናቸው።
22/11/2024

#የቀድሞ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው ዝና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአምባሳደራችን ሀዲያ ሆሳዕና መለዮ እንዴት ናቸው።

 #የሄጦ ቀበሌ ነዋሪዎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ቀናት በማብራት እጦት አየተቸገሩ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገለጹ።ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት በዚህ ግዜ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎቻችን መብራት በሚፈልግበት ...
07/11/2024

#የሄጦ ቀበሌ ነዋሪዎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ቀናት በማብራት እጦት አየተቸገሩ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገለጹ።
ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት በዚህ ግዜ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎቻችን መብራት በሚፈልግበት በዚህ ግዜ እንኳን ለአምስት ተከታታይ ቀን አይደለም ለአንድ ቀን እንኳን መጥፋት የለበትም ድንገት ቢጠፋ እነሰኳን ወዲያውኑ መፍትሔ ሊፈለግ ይገባል።

 🔆ከ720 km በላይ ተጉዘው መንገድ ላይ በርካታ ችግሮች አጋጥሟቸው ጨዋታ ከጀመረ በኋላ ድሬዳዋ ደርሰን ከነድካማችን ከሚገባን በላይ ለእናንተ ድጋፍ የሰጠነው  #ሃዲያ ለሚባል አምባሳደር ለ...
27/10/2024


🔆ከ720 km በላይ ተጉዘው መንገድ ላይ በርካታ ችግሮች አጋጥሟቸው ጨዋታ ከጀመረ በኋላ ድሬዳዋ ደርሰን ከነድካማችን ከሚገባን በላይ ለእናንተ ድጋፍ የሰጠነው #ሃዲያ ለሚባል አምባሳደር ለሆነ ከሃዲያ ህዝብ ልማት ከሚሰራ ገንዘብ ተቆርጦ ሆኖ የተሻለ ነገር እንዲመጣ ነው!

🔆ቢያንስ ለደጋፊው ክብር መስጠትን ማወቅ ተገቢ ነው
ከሚገባ በላይ ዋጋ ከፍሎ ተጉዘው ሜዳ ለተገኙ ደጋፊዎች መጥታችሁ አጠገባቸው ማጨብጨብ ክብር መስጠት ሲገባችሁ ባላየ መሄድ ተገቢ አልነበረም!

🙄

24/10/2024

#የተፈጥሮ ውሃ ጤና ውሃ
ለሁሉም ...🙏🙏🙏🙏

 #ሁሉን ነገር ኮፒ ማድረግ አይሰለቻችሁም
24/09/2024

#ሁሉን ነገር ኮፒ ማድረግ አይሰለቻችሁም

በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በነገው ዕለት /ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ለፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ለሚካሄ...
18/09/2024

በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በነገው ዕለት /ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ለፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ለሚካሄደው የሻማ ማብራት ስነ- ስርዓት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

" ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል " - ሀድያ ዞንየጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር ነገ ...
18/09/2024

" ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል " - ሀድያ ዞን

የጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል።

የፕሮፌሰሩ አስክሬን በህክምና ሲረዱ ከቆዩበት ኬንያ ናይሮቢ ትላንት ምሽት ነው አዲስ አበባ የገባው።

የቀብር ስርዓቱን ለማስፈጸም የተቋቋመ አብይ ኮሚቴ ሊኢብኮ በሰጠው ቃል ፤ የፕሮፌሰሩ ስርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም አሳውቋል።

በሌላ በኩል በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ነገ ሐሙስ ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

መላው የዞኑ ነዋሪ ሕዝብ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ በመገኘት በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እንዲገልጽ ጥሪ ቀርቧል።

ፕሮፌሰር በየነ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዕንቁ ምሁራን መካከል ከቀዳሚቹ ተርታ ይጠቀሳሉ። ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የፖለቲካ ውስጥ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ነበሩ፡፡

ነፍስ ይማር !

ቀብር 💔   | የጋራድ ሀንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ሐሙስ 8:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።የክብር ሽኝትከሳሪስ አደያ አ...
18/09/2024

ቀብር 💔

| የጋራድ ሀንሳር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ሐሙስ 8:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

የክብር ሽኝት
ከሳሪስ አደያ አበባ አዲስ ሠፈር መኖሪያ ቤታቸው ይጀምራል፤
ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሽኝት ይከናወናል።

😭 ቤተሰቦቻቸው 😭

የተከበሩ ገራድ - ጎምቱው መምህርና ፖለቲከኛ ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አረፉ   | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋ...
17/09/2024

የተከበሩ ገራድ - ጎምቱው መምህርና ፖለቲከኛ
ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አረፉ

| ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ ብለዋል።

በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ ተመኝተዋል።

መጭዉን ያሆዴን በዓል ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አየተጠናቀቀ መሆኑን የሀዲያ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለፀ።መጭዉን የያሆዴን በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግ...
14/09/2024

መጭዉን ያሆዴን በዓል ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አየተጠናቀቀ መሆኑን የሀዲያ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለፀ።

መጭዉን የያሆዴን በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የሀዲያ ዞን በህል ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል።

ይህንንም በማስመልከት የሀዲያ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ቦጋል ከሀዲያ ቴሌቪን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ያሆዴ የአንድነት፣ የመተባበር፣ የፍቅር እና የሰላም በዓል ነዉ ብለዋል።

በዓሉንም ከዞኑ ዉጪ የሀድያ ብሄር ተወላጆ በብዛት በሚኖሩባቸዉ ከተሞች ለማክበር በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት በድሬዳዋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ በማክበር መጀመሩን ገልፀዉ በቀጣይም በሐዋሳ እና በአዲስ አበባ እንድሁም ከሀገር ዉጭም ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በሌሎች ሀገራት በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት እንደሚከበርም ገልጸዋል።

በዓሉ ከሀድያ ዞን ውጭ መከበሩ የሀዲያን ባህል ለሌሎች ከማስተዋወቅም ባለፈ በህዝቦች መካከል አብሮነትን፣ፍቅርንና መተዋወቅን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

በዓሉንም ህዝባዊ መሠረት ለማስያዝ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳዳሮች ከመስከረም 6/2017 ዓመተ ምህረት እስከ መስከረም 9/2017 ዓመተ ምህረት ድረስ በተዘጋጀዉ ቅደም ተከተል መሠረት ከዚህ በፊት ከነበሩት የያሆዴ በዓላት ለየት ባለ መልኩ እንደሚከበር ኃላፊዉ ተናግረዋል።
ከዚህም አከባቢዉን የሚገልጹ ነገሮች የሚሰበሰብበት አንደሆነም በማከል።

በዞኑ ሀዲይ ነፈራ መስከረም 10-11/2017 ዓመተ ምህረት ለሚከበር የማጠቀለያ መርሃ ግብርም በበዓሉ ለሚሰተፉ አካላት ጥሪ የማድረስ፣የሰላምና ፀጥታ፣ የአከባቢዉ ንጽህናን ጨምሮ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቀ መሆኑንም ኃላፊዉ ተናግረዋል።

የያሆዴን በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብም የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸዉን የገለጹት አቶ መስፍን ለዚህም ስኬታማነት ሁሉም በኔነት ስሜት ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

  የጎዳና_ለይ ሩጫና_የሙዚቃ_ኮንሰርት_ተዘጋጅቷል።                    ⚡️⚡️⚡️የሀዲያ ዞን አስተዳደር ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር በጋራ በመሆን በሆሳዕና ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይ...
12/09/2024

የጎዳና_ለይ ሩጫና_የሙዚቃ_ኮንሰርት_ተዘጋጅቷል።
⚡️⚡️⚡️
የሀዲያ ዞን አስተዳደር ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር በጋራ በመሆን በሆሳዕና ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይነቱ ለየት ያለ የባህል ፌስቲቫል የጎዳ ለይ እሩጫና የሙዚቃ ኮንሰርት በሀዲይ ነፈ መስከረም 10 እና 11 አዘጋጅቷል።
#የዘንድሮ ያሆዴ ይለያል
#የክብር ስፖንሰር ስንቄ ባንክ

Address

Hossana

Telephone

+251934783050

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yahode Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yahode Events:

Share