
18/07/2025
አስደሳች የምስራች ለሆሳዕናና አከባቢዋ የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪያን በሙሉ!!
ከስፖርቱ በተጓዳኝ በተለያዩ ህዝባዊና ግብረሰናይ ተግባራት በንቃት በመሳታፍ የሀገርና የወገን አለኝታነቱን ከምስረታው ማግስት ጀምሮ በተግባር እያስመሰከረ የሚገኘው አንጋፋው፣ ተወዳጁና የሆሳዕና ከተማ ተቀዳሚ አምባሳደር የሆነው የሆሳዕና ጤና ቡድን ከወቅቱ የ14ኛው ሀበሻ ሚዲያ ካፕ ሻምፒዮኑ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬት እግር ኳስ ቡድን አቻው ጋር የፊታችን እሁድ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በአቢዮ ኤርሳሞ ስቴዲየም ይጫወታል።
የሰላምና የፍቅር ተምሳሌት በሆነችው ውቢቷ ሆሳዕና ከተማ እሁድ ቀን የሚደረገው ተጠባቂ ጫወታ የስፖርት ቤተሰቡን ከማዝናናት ባሻገር በከተማዋ የሚገኙ አቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን በገንዘብ ለመርዳት ታቅዶ የተዘጋጀ ልዩና ትልቅ ፋይዳ የሰነቀ ውድድር በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በስፍራው ተገኝቶ ሁለንተናዊ ድጋፉን እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላላልፈዋል።
ከዚህ ባሻገር ለስፖርቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር፣ ጨዋነታችንና የከተማችንን በጎ ገፅታ ለማሳየት የሚያስችልም መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል።
"የሆሳዕና ጤና ቡድን !!"