Injibara FM 104.1

Injibara FM 104.1 fm injibara 104.1
"ከአገው ምድር እስከ ሀገር!"
"From the land of Agaw Midir to the country!"

11/01/2025

Big shout out to my newest top fans! Abebaw Bogale, Work Hard, Amsalu Niguse, Destaw Alemu

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል እን...
06/01/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል እንዲሆን ይመኛል።

መልካም በዓል!!
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም

05/01/2025

Big shout out to my newest top fans! Abebaw Bogale, Work Hard, Amsalu Niguse, Destaw Alemu
እናመሠግናለን 🙏

ህብረተሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን ማጠናከር እና ማስፋት እንደሚገባ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ  አቶ የኔዓለም ዋሴ ገለፁ።**...
28/12/2024

ህብረተሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን ማጠናከር እና ማስፋት እንደሚገባ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ የኔዓለም ዋሴ ገለፁ።
*************
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈፃፀም ሂደት ግምገማ አካሂዷል።

በመድረኩ የእንጅባራ ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ የኔዓለም ዋሴ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰላም ማስፈን ጎን ለጎን የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የጤና መድህን ተደራሽነቱን ለማስፋፋት እየሰራ ይገኛል። ህብረተሰቡ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ስራን ማጠናከር እንደሚገባም አቶ የኔዓለም አስረድተዋል ።

የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ዜጎች ለከፍተኛ ወጪ ሳይዳረጉ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው በቀጣይ በአገልግሎቱ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የማህበረሰቡን የጤና ዋስትና የተጠበቀ እንዲሆን በትጋት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ወርቅነህ በላይነህ በበኩላቸው በከተማው እስከ አሁን ከ11 ሺህ 500 በላይ ነዋሪዎች አባል በማድረግ የጤና መድህን ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።ከመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅመው እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

በመድረኩ የ2017ዓ.ም የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ከተማው በአጭር ሳምንታት ውስጥ 68.3በመቶ ንጥር አፈፃፀም እንዳለው የጠቆሙት ሀላፊው ቀጣይ ዕቅዱን ሙሉ ለሙሉ ለመፈፀም ርብርብ ይደረጋል ብለዋል ።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ማዐጤመ የመክፈልና የመታከም አቅም የሌላቸው ወገኖች ሲታመሙ ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ አንዱ ለሌላው የሚቆምበት የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል የሚዳብርበት መሆኑን አክለዋል ።

በዚህም መነሻነት በከተማው መክፈል የማይችሉ 100ለሚሆኑ ወገኖች በባለሀብቶች እና በጎ አድራጊዎች ክፍያ በመፈፀም ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዊ ብሄ/አስ ስራና ስልጠና መምሪያ ሀላፊዜጎች የጤና ዋስትና በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር የጤና መድህን ተደራሽነትን በቁጭት ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል። በአገር ውስጥ ሀብት የመሸፈን አቅምን የሚያሳድግ እና መተባበርን መሰረት ያደረገ የጤና ስርዓት በመሆኑ ባለሀብቱም እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በጤና መድህን በተደጋጋሚ የሚነሱ ውስንነቶች ላይ ከመታጠር ይልቅ ከአገልግሎቱ የሚገኙ ጠንካራ ጎኖች ላይ ልናተኩር ይገባናል ብለዋል። በህብረተሰብ ተጠቃሚነት ላይ በማተኮር አስፈላጊው ሁሉን ርብርብ ልናደርግ ይገባል ብለዋል ።

እንደ ከተማ አስተዳደሩ በዚህ አመት የቀበሌዎች አፈፃፀም
ባሳ፣05፣ቢዳ ፣ቻባ አረንጓዴ ላይ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣04፣03፣ቢጫ ደረጃ ሲገኙ
ባታ፣02፤ዐ1፥አካይታ ቀይ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

በግምገማ መድረኩ ከተማ አስተዳደሩን የሚደግፉ ዞን አመራሮች፣ የከተማዋ ኮር አመራሮች፣ ኃላፊዎች፣ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል።
አዊ ኮሙኒኬሽን ዘግቦታል

የፅንፈኛው ኃይል በትናንትናው ዕለት ማለትም ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም በባንጃ ወረዳ አስኩና ቀጠና በተሽከርካሪ ላይ የቃጠሎ ጉዳት አደረሰ።በአማራ ክልል እራሱን "ፋኖ" በማለት ሰያሜ የሰጠው...
15/12/2024

የፅንፈኛው ኃይል በትናንትናው ዕለት ማለትም ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም በባንጃ ወረዳ አስኩና ቀጠና በተሽከርካሪ ላይ የቃጠሎ ጉዳት አደረሰ።
በአማራ ክልል እራሱን "ፋኖ" በማለት ሰያሜ የሰጠው የፅንፈኛው ኃይል በክልልሉ በተለያዩ ጊዚያት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እቀባዎችን ቢያደርግም ከአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና ከተማ እንጅባራ ወደ ቻግኒ አቅጣጫ ያለው የትራፊክ እንቅስቃሴ አንድም ቀን ተቋርጦ የማያውቅ መሆኑ እሙን ነው። ነገር ግን ከህዳር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ የፅንፈኛ ኃይል ባወጣው የተሽከርካሪ እቀባ ተከትሎ የጎጃም መስመር እንቅስቃሴ ቢቆምም ከእንጅባራ ወደ ቻግኒ የሚወስደው መንገድ በተለመደው ሁኔታ እንቅስቃሴ አለመቋረጡ ይታወቃል። ነገር ግን ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም በባንጃ ወረዳ አስኩና ቀጠና ባለቤትነት የአካባቢው ነዋሪ የሆነ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ላይ የቃጠሎ ጉዳት አድርሰው መሰወራቸው ታውቋል።

____________የሌማት ትሩፋት__________==================================                  በበርሃዋ ገነት ፈንድቃበአዊ ብሔ/አስተዳደር ፈንድቃ ከተማ ...
13/12/2024

____________የሌማት ትሩፋት__________
==================================
በበርሃዋ ገነት ፈንድቃ

በአዊ ብሔ/አስተዳደር ፈንድቃ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች የከተማዋን ሠላም ከማሥከበር ጎን ለጎን የልማት ስራውንም አቀናጅተው በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
የከተማዋን ወጣቶች በማደራጀት በሬ በማድለብ እና ዶሮ በማርባት የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸዉ ተደርጓል። ከተማው ለሌማት ትሩፋት ትልቅ ፀጋ ያለው በመሆኑ ተጨማሪ ሥራዎችን በመፍጠር ወጣቶችን የሥራ እድል ከመፍጠር ባሻግ ማህበረሠቡን የሌማቱ ተቋዳሽ በማድረግ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያሳያል።
"ድምፃችን ለማህበረሰባችን ለውጥ!"

"የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው"የአዊ ብሔ/አሰተዳደር ርዕሰ መዲና እንጅባራ ገና በለጋነት እድሜዋ በፍጥነት እያደጉ ካሉት የክልሉ ከተሞች መካከል ትጠቀሳለች። ለኑሮ ተስማሚ የአየር ንብረት ባለቤቷ...
12/12/2024

"የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው"

የአዊ ብሔ/አሰተዳደር ርዕሰ መዲና እንጅባራ ገና በለጋነት እድሜዋ በፍጥነት እያደጉ ካሉት የክልሉ ከተሞች መካከል ትጠቀሳለች። ለኑሮ ተስማሚ የአየር ንብረት ባለቤቷ እንጅባራ ፍፁም ሠላማዊ መሆኗ ተወዳጅ እና ተመራጭ ያደርጋታል። በዚህም ሳቢያ ወደ ከተማዋ የሚጎርፈው ህዝብ ከአቅሟ በላይ በመሆኑ ለማስተናገድ እየተገዳደራት የሚገኝ አንድ ጉዳይ አለ፤ ውሃ።
ከተማዋ ዙሪያዋን በምንጮቿ እና በወንዞቿ የተከበበች እና በከርሰ ምድር ውሃም የማትታማ ብትሆንም በየጊዜው እየጨመረ የሚመጣውን የህዝብ ቁጥሯን ያላማከለ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ግን ፈተና ሁኖባታል። ታዲያ የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው ማለት ይሄ አይደለምን?

ፎቶ እና የፁሁፉ መነሻ ሀሳብ አዊ ኮሙኒኬሽን

ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በአዊ ብሔ/አስተዳደር እንጅባራ ከተማ እየተከበረ ነው።የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና በዓል በፓናል ውይይት በእንጅባራ ከተማ ላይ እየተከበረ ነው። ...
06/12/2024

ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በአዊ ብሔ/አስተዳደር እንጅባራ ከተማ እየተከበረ ነው።

የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና በዓል በፓናል ውይይት በእንጅባራ ከተማ ላይ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ፣በአገር ደረጃ ለ20ኛ
"ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል ፣የነገን ስብዕና ይገነባል።"በሚል መሪ ቃል በብሔረሰብ አስተዳደር ደረጃ በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣የሴክተሩ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ባለድርሻዎች እንዲሁም ተጋባዢ እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዊ ብሔ/አስተዳደር ም/አስተዳዳሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አይተነው ታዴ ፥ሙስናና ብልሹ አሰራር በህዝቦች ዘንድ ኢ- ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ከማድረጉ በላይ ለስደትና ለእንግልት የሚዳርግ ፥ በጥቅሉ የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት ወደ ኋላ የሚያቀጭጭ በሽታ እንደሆነ ተናግረዋል ።

በብሔ/አሰተዳደሩ የተጀመረውን የፀረ- ሙስና ትግል ዳር ለማድረስ ሁሉም ማህበረሰብ ሚናውን መወጣት እንደሚገባ አቶ አይተነው አሳስበዋል ።

በዓሉን በተመለከተ የፓናል መወያያ ጽሁፍ በአዊ ብሔ/አስ ፀረሙስና መኮንን በወ/ሮ ወይንሸት ግርማ እየቀረበ ይገኛል።በፓናል ውይይቱ የፀረ -ሙስና ትግል እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
ዘገባው የአዊ ኮሙኒኬሽን ነው

"ኢትዮጵያ ብዝሃ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግ እና ብዝሃ ታሪክ በአንድነት ከሚኖሩባቸው አገራት ውስጥ አንዷ ናት"የአቶ ቴዎድሮስ እንዳለው"ሀገራዊ መግባባት ለኀብረብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ...
28/11/2024

"ኢትዮጵያ ብዝሃ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግ እና ብዝሃ ታሪክ
በአንድነት ከሚኖሩባቸው አገራት ውስጥ አንዷ ናት"
የአቶ ቴዎድሮስ እንዳለው
"ሀገራዊ መግባባት ለኀብረብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዛሬ ተከበረ::
በዓሉን በንግግር የከፈቱት የአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው ብዝሃ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግ እና ብዝሃ ታሪክ በአንድነት ከሚኖሩባቸው አገራት ውስጥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ተጠቃሽ እንደሆነች ተናገሩ። አያይዘውም የራስን ወግና ባህል ማሳደግ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ብሔረሰቦች ቋንቋ፣ ወግና ባህል ማክበር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ መሆኑን ገልፀዋል::

ብልፅግና እውን ከሆነ ጀምሮ ዜጎች በሀገሪቱ ሉአላዊነት እኩል የመወሰን መብትና ኃላፊነት አግኝተዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ብልፅግና በአፈፃፀም ጉድለት የተገኙትን እያሞላ ትክክለኛ ኅብረ ፌዴራሊዝም ተግባራዊ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል ተብለዋል።

የአገው ህዝብ ሰላምን የሚወድና በአብሮነት የሚኖር ህዝብ እንደሆነ የጠቆሙት አስተዳዳሪው ይህንን መልካም እሴቶቻችንን በኖረውና በቆየው አንድነታቸው ከሌሎች ብሔሮችና ህዝቦች ጋር በመሆን ያጋጠመንን የችግር ጊዜ መሻገር እንደሚገባም አሳስበዋል።

አቶ ቴድሮስ አክለውም ወግ ባህል እሴታችንን ለመላው አለም የምናስተዋውቅበት የፊታችን ጥር ወር የሚከበረው 85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ተሳታፊ እንዲሆኑ ከወዲሁ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

የአዊ ብሔረሰብ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ሙሉአዳም እጅጉ በበኩላቸው ፥የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ስናከብር የእርስ በእርስ ትውውቅን ለማጎልበት እድል ይሰጠናል። የዘንድሮውን በዓል እያከበርን የምንገኘው እያጋጠመን ያለውን የሰላምና የደህንነት ስብራት ለመጠገን እየሰራን ባለንበት ወቅት ነው ያሉት አፈጉባኤዋ አብሮነትን ለማፅናት ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ፣ወንድማማችነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
በበዓሉ ፓናል ውይይት ቀርቦ ውይይቶችም ተካሄዷል።
fans

የአገው ህዝብ ባህላዊ አለባበስ👍@
26/11/2024

የአገው ህዝብ ባህላዊ አለባበስ👍
@

እንጂባራ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ የምዘና ማዕከል ሥራ ጀመረ።ዩኒቨርሲቲው በቱሪዝም ሆቴል ማኔጅመንት ስልጠና በመስጠት በዘርፉ በርካታ ባለሙያዎችን ያበረከተ ሲሆን በቱሪዝምና ሆቴል ...
19/11/2024

እንጂባራ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ የምዘና ማዕከል ሥራ ጀመረ።

ዩኒቨርሲቲው በቱሪዝም ሆቴል ማኔጅመንት ስልጠና በመስጠት በዘርፉ በርካታ ባለሙያዎችን ያበረከተ ሲሆን በቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ስር የስልጠና እና ምዘና ማዕከል በማቋቋም በዛሬው ዕለት በይፋ ለሥራ ክፍት ሆኗል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሙያ ብቃትና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ያገኘ ሲሆን እዉቅና ባገኘባቸዉ ዘርፎች የአካባቢዉን ማህበረሰብ ተጠሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
የሥራ ማስጀመያ መርሃ ግብሩ በጉብኝት የተጀመረ ሲሆን ፕሮግራም በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶክተር) የቱሪዝም ሴክተር የሚፈጥረው የሥራ ዕድል እና ኢኮኖማያዊ እድገት በመገንዘብ ዩኒቨርሲቲው ዘርፉን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገለፀው አካባቢውን ከአጎራባች ከተሞች ጋር በማስተሳሰር በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ ገልፀዋል። እንዱስትሪውን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሻሻል ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በመግንባት የትምህር ክፍሉ ለማዘመን ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
በመጨረሻው ለሥራው መሳካት የላቀ ድርሻ ለተወጡ የክፍሉ ሰራተኞች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

          አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው  የአዊ ብሔ/አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪAwi communication
23/10/2024


አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው
የአዊ ብሔ/አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ
Awi communication

23/10/2024

Big shout out to my newest top fans! Abebaw Bogale, Amsalu Niguse, Destaw Alemu, Work Hard

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በአዲስ ወደ ብሄረሰብ አስተዳሩ የመጡ  የጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን አቀባበል እያደረገ ነው።እንጅባራ ፦ጥቅምት 5/2017ዓ.ም በዛሬው ዕለት የብሄረ...
15/10/2024

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በአዲስ ወደ ብሄረሰብ አስተዳሩ የመጡ የጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን አቀባበል እያደረገ ነው።
እንጅባራ ፦ጥቅምት 5/2017ዓ.ም

በዛሬው ዕለት የብሄረሰብ አስተዳደሩን ሰላም በአጭር ጊዜ ወደ ቀደመ ሰላም ለመመለስ ግዳጅ የተሰጠውን ሃይል በዛሬው ዕለት አቀባበል እየተደረገለት ነው።
ስነ-ስርዓቱም የዞን አስተዳደር፣የባንጃ ወረዳ እና የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የበሬ ሰንጋዎችን አቅርበዋል።
ስነ- ስርዓቱ የዞን፣ ባንጃ ወረዳና የእንጅባራ ከተማ ኮር አመራሮችና የፀጥታ መዋቅር የተገኙ ሲሆን፤
በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የአዊ ብሄ/አስ/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው፥የአዊ ህዝብ ሁሌም ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሆነና ወደፊትም አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ብሄረሰብ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ሰላሙን እንዲያረጋግጥ እንሰራለን ብለዋል።
#የ73ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ድባቤ በበኩላቸው የተሰጠንን ግዳጅ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ፈፅመን በአጭር ጊዜ የብሄረሰብ አስተዳደሩን ሰላም እናረጋግጣለን ብለዋል።
ዘገባው የአዊ ኮሙኒኬሽን ነው

የመንግስት ሰራተኛዉን የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር እና አባይ ባንክ  የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረሙ፡፡የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛዉ ለቤት ግንባታ እ...
09/10/2024

የመንግስት ሰራተኛዉን የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር እና አባይ ባንክ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛዉ ለቤት ግንባታ እና ግዥ እንደሁምለመኪና መግዣና ለሌሎች አግልግሎቶች ላይ ለማዋል በደሞዙ ብድር አግኝቶ ተጠቃሚ እንዲሆን የመንግስት ሰራተኞች ተወካይ፣የመምህራን ማህበር ተወካይ ፣አመራሩና ሌሎች ማህበራት በተገኙበት ከአባይ ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የአባይ ባንክ ስራ-አስኪያጅ አቶ አንሙት አማረ እንዳሉት ይህ የመግባቢያ ሰነድ ሦስት የብድር አማራጮችን የያዘና የጋራ ጠቀሜታ ያለዉ በመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ያሉትን ገቢዎች በአባይ ባንክ በኩል ሲያስተላልፍ ባንኩ ደግሞ የከተማ አስተዳደሩን ሙያተኞች በ7% ወለድ ለቤት መስሪያና ግዥ ከጥሮታ መዉጫ ጊዜዉ አንድ ዓመት ተቀንሶ በ25 ዓመት የሚመለስ የቤቱን የመሃንዲስ ግምት 95% ብድር ይሰጣል በማለት ገልጸዋል፡፡

አቶ አንሙት ለተሽከርካሪ መግዥ ከሆነ ደግሞ የመኪናዉ የስሪት ዘመን ከ10 ዓመት ያልበለጠ ሆኖ የመሃንዲስ ጠቅላላ ግምቱን 90% የሚበድር ሲሆን የብድር መመላሻ ጊዜዉም ለአዲስ መኪና 15 አመት ላገለገለ መኪና ደግሞ10 አመት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ለግል አገልግሎት የሚዉል ብድር ከሆነ ቋሚ ንብረት አስይዞ የደሞዙን ጣሪያ በግማሽ ወይም የባልና ሚስት ደሞዝ ጣሪያዉ ተደምሮ ግማሽ ደምወዝ በ60 ወር ተባዝቶ በ5 አመት የሚመለስ እስከ 500,000 ብር ባንኩ ብድር ይሰጣል ብለዋል፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የመሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ምህረት እንዳሉት ይህ ስምምነት ካለብን ችግር አንፃር የዘገዬ ቢሆንም የመንግስት ሰራተኛችን በከፍተኛ የኑሮ ዉድነት እየተሰቃዬ ያለ በሆኑ በፍጥነት ወደ ተግባር ተገብቶ ባለሙያዉ እንደየፍላጎቱ የሚመጥነዉን ብድር ወስዶ ኑሮዉን እንዲያሻሻል መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

በተለይም የፍላጎት መጠኑ ከፍተኛ ሊሆን ስለሚችል ፍታሃዊነትን ለማስጠበቅ በምን መልኩ ወረፋ መያዝ እንዳለበት በፍጥነት ከሚቴ ተዋቅሮ ሰራተኛዉን ማወያየትና ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ባንኩ አሁን በደሞዝ አከፋፈል ላይ ያለዉን ስነ-ምግባርና አገልግሎት አስጠብቆ ብድር ፈልገዉ የሚመጡ ሰራተኞችንም ቢሮክራሲ ሳያበዛ ህጉ በሚፈቅደዉ መሰረት ፈጣን አግልግሎት እንዲሰጥ አሳስበዉ ወኪሎች በተገኙበት ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡

ዘገባው የእንጅባራ_ኮሙኒኬሽን ነው

ለዘመናት  የህዝብ ጥያቄ  የነበረው የመብራት ሳቭስቴሽን  መፈቀዱ ተገለፀ ።መንግስት ለአዊ ብሔ/አስተዳደር የፈቀደውን የመብራት ሀይል ሳቭስቴሽን በማስመልከት   የብሄረሰብ  አስተዳደሩ እና ...
03/10/2024

ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት ሳቭስቴሽን መፈቀዱ ተገለፀ ።

መንግስት ለአዊ ብሔ/አስተዳደር የፈቀደውን የመብራት ሀይል ሳቭስቴሽን በማስመልከት የብሄረሰብ አስተዳደሩ እና የእንጅባራ ከተማ አስ/አመራሮች በተገኙበት ከእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድረገዋል ።

በውይይት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው እንደገለፁት መንግስት ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት ሳቭስቴሽ በመፈቀዱ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው ሰብስቴሽኑን ለመገንባት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል ።

በአካባቢው የፀጥታ ችግሮቸ በመፍጠር ልማት እንዳይስተጓጎል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ይህ ፕሮጀክት በታቀደው ጊዜና ወቅት ከተጠናቀቀ መንግስት ሌሎችንም የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል ።

ማንኛውም ልማት የሚመለሰው በመደማመጥ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ቴዎድሮስ የብሄረሰብ አስተዳደሩ ባህልና እሴት ያልሆኑ አንድነትንና አብሮነትን የሚሸረሽሩ ልማዶችን ማህበረሰቡ ማውገዝ እንደሚገባው ጥሪ አስተላልፈዋል ።

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ሰውነት በበኩላቸው የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ህዝብ የልማት አርበኛ በመሆኑ የልማት ጥያቄ በግልፅ የሚጠይቅና መልሱን በትዕግስት የሚጠብቅ አስተዋይ ህዝብ መሆኑን ገልፀዋል ።

ይህ በጣም ግዙፍ ፕሮጅክት በፀጥታ ችግር እንዳይደናቀፍ ሁሉም ማህበረሰብ ዘላቂ ሠላም እንዲረጋገጥ የበኩሉን ሚና መጫወት እንደሚገባው አቶ አለሙ አሳስበዋል ።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ የኔዓለም ዋሴ እንደተናገሩት ይህ ፕሮጀክት ለእንጅባራና ለአካባቢው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች ዞኖችንም ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈታ ወደር የሌለው ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት የቅያሳ ባለሙያ አቶ ካሳዬ ግዛው እንደገለፁት በእንጅባራ አካባቢ የሚገነባው የመብራት ሀይል ሳቭስቴሽን በወርልድ ባንክ በጀት ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው ከፍተኛ የሰብስቴሽን የሀይል ያለው እንደሆነም አብራርተዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት ሃይል ሳቭስቴሽን በመፈቀዱ በእጅጉ ደስተኛ መሆናቸውን የተናገሩት ተሳታፊዎቹ በእንጅባራ ከተማ የተገነቡ ፋብሪካዎች በሀይል እጥረት አገልግሎት ባለመስጠታቸው ምክንያት ብዙ ችግሮች እየተስተዋሉ እንደሆኑ ተናግረዋል ።

የሳቭስቴሽን ቴክኒካል ስራውን ለመስራት ለመጡት ባለሙያዎች ከእንጅባራ ነዋሪዎች የአገዎች ባህላዊ አልባሳት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።
ዘገባው:-የአዊ ኮሙኒኬሽን ነው

የአገው ህዝብ መስቀል በዓል
27/09/2024

የአገው ህዝብ መስቀል በዓል

25/09/2024

Address

Injibara

Opening Hours

Monday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00
Tuesday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00
Wednesday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00
Thursday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00
Friday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00
Saturday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00
Sunday 08:00 - 12:00
16:00 - 00:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Injibara FM 104.1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share