Agew AWI Times

Agew AWI  Times Agaw Awi is relatively flat and fertile, whose elevations vary from 1,800 to 3,100 m above sea level, with an average altitude of about 2,300 m.

water features include two crater lakes, Zengena and Tirba, one of the most productive in the Amhara Region. AWI ZONE IS one of the most richest in fertile soil better for living things ! have lots of natural,cultural and historical places including the most descent peoples ......Ethiopian history tells us about each and everything .like this Agew Awi (Amharic: አገው አዊ) is one of 10 Zones in the Am

hara Region of Ethiopia. Agew Awi is named for the Awi sub-group of the Agaw people, some of whom live in this Zone. Agew Awi is bordered on the west by Benishangul-Gumuz Region, on the north by Semien Gondar Zone and on the east by Mirab Gojjam. The administrative centre of Agew Awi is Injibara; other towns include Chagni, and Dangila,Tilili,Addiskidam,Gimjabet,Azena,Jawi,etc

አፄ ምኒልክ ለጦርነት ወደ ሀረርጌ በሄዱበት ጊዜ ራስ ጎበና በአዲስ አበባ ሆነዉ መንግስት ሊገለብጡ ነበር ተብለዉ ተከሰሱ። በመኳንንቱ ዘንድም ጥፍተኛ ተብለዉ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸዉ።አፄ ም...
24/08/2025

አፄ ምኒልክ ለጦርነት ወደ ሀረርጌ በሄዱበት ጊዜ ራስ ጎበና በአዲስ አበባ ሆነዉ መንግስት ሊገለብጡ ነበር ተብለዉ ተከሰሱ። በመኳንንቱ ዘንድም ጥፍተኛ ተብለዉ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸዉ።

አፄ ምኒልክም ፍርዱን እንዲያፀኑ ሲጠየቁ "ጎበናን እዚ ለማድረስ ሰላሳ አመት ፈጅቶብኛል። ለአንድ ቀን ጥፋቱ ብዬ የሰላሳ አመት ድካሜን አላበላሽም። ምሬዋለዉ። እንደ ጥንቱ ይኑር" ብለዉ ይቅርታ አደረጉ።

#ምኒልካዊነት አስተሳሰብ ነዉ

እንኳን ተወለዱ ዐጤ ምኒልክ😍

13/07/2025

ከመንጋና ደቦ ፍርድ እንላቀቅ ይሆን?

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያን ውስጥ በጋራ እንደ ገደል ማሚቶ ብንጮህ የማይቀዬረው መንግስትና ኑሮ ብቻ ነው::ሌላው ግን ይወርዳል ይወጣል ይፈታል ይታሰራል ይሰቀል ይሰቀል ብንል እንደ አይሁዶች የሚሰቀል አይታጣም::

ከደቦ ፍርድ እንወጣ ይሆን?

የፍትህ ተቋማት ፍትህን ሳያዛቡ በመረጃና በማስረጃ ያለምንም ልዩነት ይሰጡ ይሆን?
የእውነት የፍትህ ተቋማት ከግለሰቦች ነፃ ወጥተዋልን?

ኑሮው የማይሻሻለው ደመወዝተኛ በተለይም (መምህር:ሀኪም:ፖሊስ:ወታደር) በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ያለው ትልቅ ድርሻ አስትወላችሁት ታውቃላችሁ?

ፍትህ ራሷ ከደቦ ፍርድ ትላቀቅ ይሆን????

አሁን ላይ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት ምግብና ልብስ ወይስ የባህር በር?

ንፁህ ወኃና መጠለያ ወይስ መዝናኛ ስፍራ?

ሰላምና ፍትህ?
ወይስ የወንዝ ዳር መናፈሻ?

ፍላጎቶቻችን እና አቅርቦቶቻችን ተጣጥመው ወይስ ተጣመው ???
ሁላችንንም ተፋፍረንና ታፍነን እንጅ ቸግሮናል::
ለማን አቤት ይባላል???

እባካችሁን ምንም የማያውቁ ህፃናት እንዲሁም አሮጋውያን ያለጥፋታቸው አይቀጡ::እባካችሁን በሁለት ገልጃጃ መሪዎች ብዙዎች አይሰቃዩ::ተው እንኑርበት?ተው ይኑሩበት?
15/06/2025

እባካችሁን ምንም የማያውቁ ህፃናት እንዲሁም አሮጋውያን ያለጥፋታቸው አይቀጡ::

እባካችሁን በሁለት ገልጃጃ መሪዎች ብዙዎች አይሰቃዩ::

ተው እንኑርበት?
ተው ይኑሩበት?

የምንወዳት አርቲስት ከጠፋች አመታት ቢያልፉም ድንገት በአካል ተገናኜን::
15/06/2025

የምንወዳት አርቲስት ከጠፋች አመታት ቢያልፉም ድንገት በአካል ተገናኜን::

15/06/2025

ይድረስ ለእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና ከፍተኛ አመራሮች

#እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረት ጥቂት አመታት ውስጥ ብዙ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እንደሰራ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን እንዳከናወነ::በተለይም ለመምህራን ክብርና ጥቅም እንደሚታትር በቅርበት አውቃለሁ::ነገር ግን የእጅባራና አካባቢዋ ምሁራንና ተመራማሪዎች ወደ ማህበረሰባቸው ተዛውረው ሳይማር ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ለማገልገል በሚጠይቁበት ጊዜ አንድም በጉርብትናና ዝምድና በሌላም በገንዘብ የሚካሄድ እጅግ ያፈነገጠ አሰራር ተንሰራፍቷል::በዚህም የተነሳ አንድ መምህር በሳምንት ማስተማር ካለበት ሰዓት ሁለትና ሶስት እጥፍ ትርፍ ሰዓት በመያዝ ከሰኞ እስከሰኞ ከጠዋት እስከማታ እያስተማረ ይገኛል:: መረጃው ከተፈለገ ይለጠፋል::ይህ በትምህርት ጥራት አሉታዊ ተፅኖ አለው::መምህሩም ተመራማሪ መሆኑ ቀርቶ መምህር ብቻ ይሆናል::

ይታሰብበት???

ዝውውር ይፈቀድ?
ቅድሚያ ለችግረኞች ይሰጥ?

የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰቡ እንጅ የግለሰቦች አይደለም::
እንጅባራ ዩኒቨርሰቲ የገ/ቁ/ብ/ህ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወ.
Injibara University

ይቺ አሮጊት አትርሱኝ ብላለች በግድሲጀመር ከትዳርሽም ከቤተሰብሽም ያጣላሽ ፀባይሽ እንጅ እምነትሽ አሊያም አስተሳስብሽ አይደለም:: አንቺ ከከፈሉሽ ሁሉንም ትተውኛለሽ በቅርበት ስለማውቅሽ አይ...
20/04/2025

ይቺ አሮጊት አትርሱኝ ብላለች በግድ

ሲጀመር ከትዳርሽም ከቤተሰብሽም ያጣላሽ ፀባይሽ እንጅ እምነትሽ አሊያም አስተሳስብሽ አይደለም:: አንቺ ከከፈሉሽ ሁሉንም ትተውኛለሽ በቅርበት ስለማውቅሽ አይገርመኝም ለቁራሽ ዳቦ ስትይ ብኩርናሽን የምትሸጭ በሃያ ሺህ ብር እህትሽን ጭምር የተጣላሽ ለቃቃሚ ሴትነሽ::አትርሱኝ አትበይ እንዳውም ባልሽን አመስግኝው::ውለታቢስ

ተነስቷል ክርስቶስ ተነስቷል!መልካም ትንሳኤ::የክርስቶስ ቤተሰቦች በሞቱ ሞታችንን የሻረልን:የድንግል ማርያም ልጅ የቀራኒዮው በግ የአብ ልጅ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የአገራችንን ትንሳኤዋን ያ...
20/04/2025

ተነስቷል ክርስቶስ ተነስቷል!
መልካም ትንሳኤ::

የክርስቶስ ቤተሰቦች በሞቱ ሞታችንን የሻረልን:የድንግል ማርያም ልጅ የቀራኒዮው በግ የአብ ልጅ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የአገራችንን ትንሳኤዋን ያሳዬን::

ክርስትና እና ክርስቲያናዊነት ብዙ ፈተና ብዙ ስቃይ ብዙመገፋት ብዙ ችንካር አለው ያመኑት አምነውም የፀኑት በመልካም ምግባር የተመላለሱት ትንሳኤን ያያሉ::

በቤቱ ያፅናን ቀናልብ እዝነ ልቦና ይስጡን::

መልካም በዓል የትንሳኤውን ብርሃንያሳዬን!!

ስለቲክቶከሯ መረጃ ከሌላችሁ ዝም በሉ #ይች ልጅ ወደ ትወናው ወደ ፊልም አለም ለመቀላቀል ሁሉንም ትሞክራለች::ይህ የትወና ልምምድ የቀረፃ ቪዲዮ ተዋዶ ያለብሽ ክርስቲያን እስላሙ በሚለው ሙዚ...
16/04/2025

ስለቲክቶከሯ መረጃ ከሌላችሁ ዝም በሉ

#ይች ልጅ ወደ ትወናው ወደ ፊልም አለም ለመቀላቀል ሁሉንም ትሞክራለች::ይህ የትወና ልምምድ የቀረፃ ቪዲዮ ተዋዶ ያለብሽ ክርስቲያን እስላሙ በሚለው ሙዚቃ የተሰራ ማይም ነው::

ስለዚህ አታሳስቱ
ሲጀመር ተዋህዶ ተመርጠው ተፈቅዶላቸው የሚኖሯት እንጅ በጫጫታና በጅምላ በደቦ የሚቀላቀሏት አይደለችም::

 #ስለ አህያ   #ይህንንያውቃሉ?👇1)የራስ ወዳድ እና የስግብግ ሰዎች ፍላጎት እንጂ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" በጭራሽ አህያ አላለችም2)አህያ እንደሌሎች እንስሶች የሰው ማሳ ውስጥ ገብ...
16/04/2025

#ስለ አህያ #ይህንንያውቃሉ?👇

1)የራስ ወዳድ እና የስግብግ ሰዎች ፍላጎት እንጂ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" በጭራሽ አህያ አላለችም

2)አህያ እንደሌሎች እንስሶች የሰው ማሳ ውስጥ ገብታ የሠው ሰብል አትበላም

3)አህያ በረሀብ ትሞታለች እንጂ የጫነችውን እህል ንክች አታደርግም

4)ብዙ ሰዎች አህያ የማታውቅ ቢመስላቸውም፣ የሄደችባቸውን አቅጣጫ እና መንገድ ሁሉ ከሁሉም እንስሳ በላይ አሳምራ ታውቃለች

5)የገጠር አህያ የከተማ መውጫ መግቢያ አንዴ ካየች እድሜ ልኳን አትረሳም
6)አህያ እስከ 60 ኪሎ ሜትር የሚሰማ፡ጆሮ ስላላትኃይለኛ ዝናብ ከመምጣቱ በፊት ታውቃለች

7)የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከመከሠቱ በፊት ጬኸት በማሰማት ሰዎችን ታተርፋለች።

8)በናሽናል ጂኦግራፊ የእንስሳት ማህደር በጣም ትሁት፣ጨዋ እና አስተዋይ ተብለው የተመዘገቡት ዶልፊን፣ ፖንዳ፣ ዝሆን፣ ፈረስ፣ እርግብ እና አህያ ናቸው፡፡

9)አህያ ለዘመናት ሰዎችን በታማኝነት ሳይታክት የሚያገለግል ታታሪ ሰራተኛ ሆኖ እያለ ለሰነፍ ሰው፣ ደካማ ሰው ወይም ገልቱ ሰውን ለመግለፅ 'አህያ'ተብሎ መሰደቡ የአህያን የዘመናት ውለታ መካድ ነው፡፡

10)የሰዉ ልጆች ዋነኛ አገልጋይ አህያ ቢሆንም የአህያን ክብር አንኳሶ፣ ምንም አገልግሎት ለማይሰጠን ለአንበሳ የተለየ ክብር መስጠታችን የተፈጥሮ ሚዛን የጎደለን መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

11)አህያ 20 ሰአት ሠውን እያገለገለ የአህያ ቀለቡ ዱላ ሲሆን የድመት ግን ወተት ነው።

12)አህያ አገርና ህዝብን እያገለገለች ከዱላ እና ስድብ ውጪ አንዴም ተሞግሳ አታውቅም፡፡የውለታ አልቦው ትዕቢተኛው አንበሳ ግን ሙገሳና ውዳሴ ይቸረዋል፡፡

13)በእኛ አገር ክብር ባይሰጠውም በእንግሊዝ አህያ ላይ ጉዳት ማድረስ ፍርድ ቤት ገትሮ ዘብጥያ ያስወርዳል፡፡የአህያ መብት ተሟጋችም በእንግሊዝ ከተቋቋመ ቆይቷል፡፡

14) በአሜሪካ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ምልክት አህያ መሆኑ የአህያን ውለታ በማሰብ ነው፡፡

ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ አንበሳ ነን ብለው ለሚፎክሩ የእኛ አገር ፖለቲከኞች ጥሩ ምሳሌ ነው (ከገባቸው) አይገባቸውም እንጂ የፖለቲካ ፖርቲዎች ለምርጫ ሲወዳደሩ የአህያን ምስል በምልክትነት ቢጠቀሙ ጥሩ ነው፡፡

15) "እንደ ሰው የሚያስብ አህያ ባላውቅም እንደአህያ የሚያስ ሰው አውቃለሁ"የሚለው አባባል ደደብ ሰዎችን ለመግለፅ የሚያገለግል ቢመስልም የአህያን ኢንተለጀንሲ በማያውቁ ሰዎች የተገለጸ አባባል ነው።

16)በአንበሳ እንጂ በአህያ ሆቴል እና ንግድ ቤት መክፈት የማይወዱት የእኛ አገር ነጋዴዎች 'አህያ ሆቴል' ወይም "አህያ ንግድ ቤት" "አህያ ሱፐርማርኬት" ብለው ቢሰይሙ የታታሪዋን እና የጨዋዋን እንስሳ ስያሜ መጠቀማቸው እንጂ ስድብን የሚገልፅ አለመሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡ሚያዚያ 30 የአህያ ቀን ነው።

ከዛሬ ቀን ጀምሮ አህያ ብሎ የሚሳደብ ሰው ካለ ራሱ ምንም የማያውቅ በናሽናል ጅኦግራፊ መመዝገብ ያለበት የዱር እንስሳ ነው::

ክብር ለአህዮች

ምንጭ፦ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

13/03/2025

የኢትዮጵያ ምሁራን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች ሰላም ናችሁ?

09/03/2025

ቅጠሩኝ? #እርዳታችሁን ይፈልጋል።

ብቻ ለእለት ጉርስ ለአመት ልብስ እና ለቤት ኪራይ እንዲሁም ከመንገድ ዳር ቁጭ ብለው ለሚጠይቁኝ ምስኪን እናቶቼና ህፃናት እጀን የምዘረጋበት ከተረፈኝ ደግሞ ...ለሚፈልጉኝ እና ለምፈልገው የምከፍለውን ብቻ ክፉሉኝ።
ብቻ ቅጠሩኝ?

******ይህ መልእክት ለእኔም ለመሰሎቼም ለመንግስት ተቀጣሪዎች እንዲሁም ለስራአጦች የጋራ መልእክት ነውና

ለሁሉት ቀን ብቻ ወደፈለጋችሁት አገራት ያለምንም ቪዛና ትራንስፖርት ዶክመንት መውጣት ብትፈቅድ እመኑኝ አየር መንገዱ #የታክሲ ሰልፍን ያስንቃል።
ሁላችንም ተማረናል ነገር ግን ተምረናል
ሀገር አለን ወገን አለን ብለን ያውም ከአውሮፓ ምድር አሻፈረን ብለን ኮብልለን መጠናል አሁን ላይ ግን ኑሮና የአገራችን የሰላም ሁኔታ ተደማምረው የእውነት ወደሊቢያ ጭምር ለመሰደድ ፍላጎታችን ጨምሯል።

በቃ ቅጠሩኝ?

በተማርኩትም ይሁን ባልተማርኩት በችሎታዬም ይሁን በክህሎቴ አሊያም ተምሬ ለመስራት ዝግጁ ነኝ።

ከመሰደዴ በፊት ቅጠሩኝ?

የእውነት በቅርብ አንድ ወንድማችሁን በስደት ታግቶ ብር አዋጡ ከመባላችሁ በፊት ቅጠሩኝ???

ይህንን መልእክት የላከልኝ የራሴ የቅርብ ጓደኛ ነው።

እባካችሁ ስራ ያላችሁ ተባበሩት በውስጥ አናግሩኝ።

09/03/2025

ኢትዮጵያን ለግብረሰዶማውያን መፈንጫ ለማድረግ የምትፍጨረጨሩ ቡድኖች ስርዓታችሁን ያዙ።

የእውነት ትገርማላችሁ

Address

Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agew AWI Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share