Berihun Atinaf

Berihun Atinaf ✨መግቢያም መውጫም "በር" ነው!
በተለይ የባህር ✨ media
(3)

17/12/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Robil Alene Bizuayehu, Abebaw Adamu, Mastewal Birhanu, Berihun Tarekegn Tarekegn, Aberra Wolde, ሙሉጎጃም የአጉንታዋ

የባህል ባለውለታዎቹን              ቤተሰብ እንደግፍ  !ሁለቱ ወጣቶች ለአገው ባህል መተዋወቅና ቋንቋ ብዙ የሠሩና ሠርተው ሳይጠግቡ  በሰው እጅ በአጭሩ ተቀጭተዋል።1/ ዋና ሳጅን ታጠ...
09/12/2025

የባህል ባለውለታዎቹን
ቤተሰብ እንደግፍ !

ሁለቱ ወጣቶች ለአገው ባህል መተዋወቅና ቋንቋ ብዙ የሠሩና ሠርተው ሳይጠግቡ በሰው እጅ በአጭሩ ተቀጭተዋል።

1/ ዋና ሳጅን ታጠቅ ግዛት በጥርባ ባህል ቡድንና በአዊ ባህል ቡድን በዘፋኝነት፣በተወዛዋዥነትና በተለይም የአገውኛ ግጥምና ዜማ ለካሰች አማረ፣ለአወቀ ካሳሁን፣ለአብርሀም ካሣሁን፣ለባንቺአምላክ ይልሀልና ለሌሎች የሠራ ባህል አዋቂና ታታሪ ወጣት ነበር።

ለሙዚቃ ካለው ፍቅር በ90ዎቹ አጋማሽ ከአዊ ባህል ቡድን ጋር ለመለማመድ ከአገው ግ/ቤት እንጅባራ በእግሩ እየመጣ ፣ሲመለስ የአዊ ባህል ቡድን 5 ብር ሰጥቶት በ2ብር ሽሮ በልቶ በ 3ብር በመኪና እየሄደ መስዋዕትነት የከፈለ(እንደ አቶ ለይኩን ምስክርነት) በኋላም በማራ ክልል ልዩ ኃይል ገብቶ በሰሜኑ ጦርነት በውጊያ የተሳተፈ፣ ከተመለሰም በኋላ ብዙ የአገውኛ ዜማዎችን የሠራ ነበር

2ኛ/ ወጣት አልጋነህ ይግዛው ለጥበቡ ካለው ፍቅር በአዊ ባህል ቡድን ተቀላቅሎ ለ4 ዓመት በተወዛዋዥነት መድረክ ሳያገኝ በትዕግስት የጠበቀ(እንደ አቶ ለይኩን ምስክርነት) በኋላም ድንቅ ተወዛዋዥ ሆኖ እያገለገለ ሳለ በዕድገት ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ተቀጥሮ መሪ ተወዛዋዥነት የደረሰ ታታሪ ነበር።በኋላም የአካባቢየን ወጣቶች አሰለጥናለሁ ብሎ በአዊ ባህል ቡድን ዳግም ተቀላቅሎ የውዝዋዜ አሰልጣኝና ኬሪዮግራፈር ሆኖ በርካታ የአገውኛና የአማርኛ ዘፈኖችን የሙዚቃ ክሊፖችን ለጀማሪና ታዋቂ ዘፋኞች የሠራ ፣በተለይም ' ጛርጊ' በሚለው ሙዚቃ ሞዴል ሆኖ የሠራ፣በኋላም ከወንድሙ ደመቀ ቢተው ጋር ሕጻናትን በውዝዋዜ አሰልጥነዋል ።

እነዚህ ወጣቶች ታጠቅ ግዛት የ2 ልጆች አባት ፤አልጋነህ ይግዛው የ1 ልጅ አባት ሲሆኑ ባለቤቶቻቸው ሥራ የሌላቸውና የእነሱን እጅ የሚጠብቁ ነበሩ።

ምን እናድርግ?
1/የዋና ሳጅን ታጠቅ ባለቤት ወ/ሮ አልማዝ፣ የአቶ አልጋነህ ይግዛው ባለቤት ወይዘሮ አዲሴ አካውንታቸውን ከታች ስላስቀመጥን የምንችለውን ገንዘብ ብናግዛቸው።

2/ የሁለቱም የልጅ እናቶች ቤተሰቦቻቸው እሩቅ ያሉና የቤተሰብ ድጋፍ እንኳን በቅርብ የማያገኙ ፣ ልጆቻቸውን ይዘው በእንጅባራ ቤት ተከራይተው ስለሚኖሩ በእንጅባራ ያላችሁ ባለሀብቶችና የድርጅት ባለቤቶች ሰርተው ልጆቻቸውን እንዲያሳድጉ ቅጥር ብታመቻቹላቸው።

3/የእንጅባራ ከተማ አስተዳደርም የመሥሪያ ሼድ በመስጠትና በተለያዩ ድጋፎች ላይ ተካተው ድጋፍ እንዲያገኙ ቢያደርግልን

በአጠቃላይ የአቅማችንን ድጋፍ እንድናደርግ ጥሪ እናቀርባለን
የአዊ ብሔ/አስ/ባህል ቱሪዝም መምሪያና ጓደኞቻቸው።

ለተጨማሪ መረጃ
🎯 የወ/ሮ አዲሴ ግዛት (የአቶ አልጋነህ ባለቤት) ስልክ_ 0960049557
🎯 ወ/ሮ አልማዝ መሀሪ (የዋና ሳጅን ታጠቅ ባለቤት ስልክ _ 0912717889
ወ/ሮ አዲሴ 0960049557

💖ሁሌም ምርጥ መባል ምንኛ መታደል ነው።💖💖💖💖💖💖💖💖💖ዩኒቨርሲቲው የህፃን እድሜን አስቆጥሮ የወጣትነትን ጥንካሬና ቅልጥፍናን፣ የጐልማሳን ብስለትና አሰተሳሰብን የተጐናፀፈው እንጂባራ ዩኒቨሲቲ...
07/12/2025

💖ሁሌም ምርጥ መባል ምንኛ መታደል ነው።
💖💖💖💖💖💖💖💖💖
ዩኒቨርሲቲው የህፃን እድሜን አስቆጥሮ የወጣትነትን ጥንካሬና ቅልጥፍናን፣ የጐልማሳን ብስለትና አሰተሳሰብን የተጐናፀፈው እንጂባራ ዩኒቨሲቲ በተማሪው ዘንድ ተመራጭ ያደረገው የመጀመሪያው በሠላም ተመሳሌት ህዝብ መሀል መገኘቱ፣ የአየር ንብረቱ እጅግ ለጤና ተሰማሚ፣ የትምትርት ጥራትና ብቃት፣ ሙሉ ግቢው ዘመኑን የዋጀ መሆኑ ማለም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቱ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን እንዲሁም ሙሉ ግቢውን ያደረስ፣ እጅግ ንፅህና አረንጓዴ ግቢ፣ ተዘርዝሮ የማያልቅ እምቅ አቅም ለይቶና አሟጦ እየተጠቀመ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ነው፤ ።
ይህ የሆነው ደሞ በምክንያት ነው። "ዱባ እንደመሪው" አይደል የሚባል? ከቀድሞ መሪዎች ጀምሮ እስከ አሁኑ ተናበው፣ ተግባብተው፣ ተሰናስነው በመምራታቸው ተቋሙን በከፍታ ማማላይ ሰቅለውታል።
ከእውቀት እስከ ህንፃ ግንባታ በጥራት የዘለቀ አስደማሚ ግቢ ነው።
ለዚህ ስኬት መብቃት ደግሞ ከጥበቃ እስከ ፕሬዝዳንቶች የጋራ ጥረት በመሆኑ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል።
ከኢትዮጵያ አንደኛ ከዓለም ደግሞ 962ኛ ደረጃ በመያዝ በመያዙ በድጋሜ እንኳን ደስ አለን ማለት እፈልጋለሁ 💖

06/12/2025

በኢልሳቤት አዲሱ ተገጠመ
"ምንው እንደ አላዛር ሞተህ ብትነሳ " Elsabet Addisu

06/12/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Nibret Assefa Z Ethiopia, D Friwu Alebel, Alemu Bey, Amare Molla, Endale Ejigu Amelo, Kirubal Tesfa Kiru, Geyasew Zerihun

  ከኢትዮጵያ አንደኛ ከዓለም 962ኛ ደረጃ ሆኖ ተመረጠ።💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማስተማር ምቹና አረንጓዴ የግቢ ገፅታ በመ...
06/12/2025

ከኢትዮጵያ አንደኛ ከዓለም 962ኛ ደረጃ ሆኖ ተመረጠ።
💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹💖❤️‍🩹
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ማስተማር ምቹና አረንጓዴ የግቢ ገፅታ በመገንባትና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በስፋት በማከናወን በአለማቀፍ ደረጃ በተካሄደ ውድድር ከኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች አንደኛ በመውጣት እውቅና አገኘ።
ህዳር 25/2018 ዓ/ም

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዘላቂ አረንጓዴ ልማት፣ ለግቢያቸው ውበት እና አረንጓዴነት የሚሰጡትን ትኩረት በስድስት ዋና ዋና መስፈርቶች እና በ39 አመላካቾች በመመዘን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያወዳድረው እና እኤአ በ2010 በኢንዶኔዥያ የተመሰረተው የተሰኘ አለማቀፍ አወዳዳሪ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2025 በ105 ሀገራት የሚገኙ 1745 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ያወዳደረ ሲሆን በዚህ ውድድር የተሳተፈው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አንደኛ ከዓለም ደግሞ 962ኛ ደረጃ በመያዝ ተመርጧል።

ዩንቨርሲቲው ከዚህ በፊት ለመማር ማስተማር ምቹና አረንጓዴ ግቢ በመፍጠር እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት ስራዎቹ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እውቅናና ምስጋና የተሰጠው መሆኑ ይታወሳል።

ይህንን እውቅና በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት የዩንቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ ዩንቨርስቲው የጀመራቸውን ግቢውን ለመማር ማስተማር ምቹ የማድረግና የዘላቂ አርንጓዴ ልማት ስራዎች አጠናክሮ እያስቀጠለ መሆኑን ገልፀው ይህ አለማቀፍ እውቅና በዩንቨርሲቲው ሰራተኞችና አመራሮች ያላሰለሰ ጥረት የተገኘ በመሆኑ "መላው የዩንቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።
Injibara University

86 ዓመታትን በፍቅር #የአገውፈረሰኞች
04/12/2025

86 ዓመታትን በፍቅር
#የአገውፈረሰኞች

። ፨ ፨ ፨ ፨ ፨።።። የምስራች፨።። ፨፨፨። ፨ሶፋው ቆሸሸ ብሎ  መጨነቅ ቀረየሶፋዎትን ውበት ወደ ነበረበት እንመልሳለን።።።  #የትም የሶፋ እጥበትና ቤተ ውበት አገልግሎት ።።።።።የትም ሰ...
04/12/2025

። ፨ ፨ ፨ ፨ ፨።።። የምስራች፨።። ፨፨፨። ፨
ሶፋው ቆሸሸ ብሎ መጨነቅ ቀረ
የሶፋዎትን ውበት ወደ ነበረበት እንመልሳለን
።።። #የትም የሶፋ እጥበትና ቤተ ውበት አገልግሎት ።።።።።
የትም ሰርፕራይዝና ዴሊቨሪ ከሰርፕራይዝ በተጨማሪ አሁን ደግሞ እጅግ ዘመናዊ ማሽኖችን በማስመጣት በእንጅባራ ከተማ የመጀመሪያ የሆነውን #የትም #የሶፋ #እጥበትና #ቤተ #ውበት #አገልግሎት በእንጅባራና አካባቢው የሚገኙ የደምበኞቹን ፍላጎት ለማሳካት በዝግጅት ላይ እንገኛለን።
ከእርስዎ የሚጠበቀው
👉📱0962365121
👉 📱0980223510
መደወል ብቻ ነው።
#የትም የሶፋ እጥበትና ቤተ-ውበት አገልግሎት ✅

።።።።።። እንጅባራ ።።።።።።።።

መቼቱ አገው ምድርድንቅ የፍቅር ታሪክ
04/12/2025

መቼቱ አገው ምድር
ድንቅ የፍቅር ታሪክ

 #ትዝታችን 1 በFB #ትንሱ  #አላየበጉ ግን ወንድሙን የለየው ይመስላል 😁😁😁😁
18/11/2025

#ትዝታችን 1 በFB
#ትንሱ #አላየ
በጉ ግን ወንድሙን የለየው ይመስላል 😁😁😁😁

Address

Injibara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Berihun Atinaf posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Berihun Atinaf:

Share