Berihun page

Berihun page ✨መግቢያም መውጫም "በር" ነው!
በተለይ የባህር ✨ media
(3)

 #ትዝብት ዘእንጅባራ | ​እንጅባራ ከተማ በአማራ ክልል ከሚገኙ ከተሞች በሰላሟ፣ በአየር ፀባያዋ፣ በአቀማመጧ እና በእንግዳ ተቀባይነቷ ተወዳጅና ተመራጭ እየሆነች የመጣች ውብ ከተማ ነች።​በ...
08/08/2026

#ትዝብት ዘእንጅባራ

| ​እንጅባራ ከተማ በአማራ ክልል ከሚገኙ ከተሞች በሰላሟ፣ በአየር ፀባያዋ፣ በአቀማመጧ እና በእንግዳ ተቀባይነቷ ተወዳጅና ተመራጭ እየሆነች የመጣች ውብ ከተማ ነች።

​በመንግሥት እቅድ እና በማህበረሰቡ ተነሳሽነት በተከናወነው የኮሪደር ልማት ሥራ (ከአንድ ኪሎ ሜትር በታች በሆነው) ከተማዋ አዲስ እና ውብ ገጽታን እየተጎናጸፈች ትገኛለች፤ ቀጣይነትም ይኖርዋል በሚል ተስፋ።

​የኮሪደር ልማቶች መሠረታዊ ከሆኑት አካላት መካከል ደግሞ አካባቢውን በሌሊት የሚያደምቁ እና ለዕይታ ውብ የሚያደርጉ የመንገድና የህንፃ መብራቶች መሆናቸው ሌሎች ከተሞች ማሳያ ናቸው። ዳሩ ግን፦

​"ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ..." ሆነብን!

​ልማቱ እጅግ የሚመሰገን እና ማህበረሰቡን ያኮራ ቢሆንም፣ በሂደቱ ውስጥ መስተካከል የሚገባቸው ክፍተቶች መኖራቸው አልቀረም።

​የሀሳቤ ቁንጮ መነሻ፣ የኮሪደሩ አካል ባይሆንም ከአደባባዩ ወደ ቻግኒ መውጫ ያለው መንታ መንገድ አካፋይ መሀል የተተከሉት የመንገድ መብራቶች ቀንድ ይመስል ተወድረው መብራት ግን ናፍቋቸዋል! እናም አፋጣኝ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

​የእንጅባራ ከተማ ከዕለት ወደ ዕለት እያደገች ስትመጣ መሠረተ ልማቶቿም በተመሳሳይ ፍጥነት የተሟሉ ሊሆኑ ይገባል። በመሆኑም የሚመለከተው አካል ይህንን ሕዝብ ያሳተፈ የልማት ሥራ ተንከባክቦ ለመያዝ እና የከተማዋን ውበትና ጸጥታ ሙሉ ለማድረግ፣ የተተከሉትን የመብራት መሶቦች ከባዶ (ከፓውዛ) ተሸካሚነት ወደ አብሪነት እንዲቀየሩ ዘንድ ጥረት ሊያደርግ ይገባል!

​ #እንጅባራ #የኮሪደርልማት #ልማት #ማህበረሰብ #ከተማችን

በአዊበደረሰው የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አደርሰ!በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ አንጓይ ቀበሌ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና  ንብረት ላይ ...
08/08/2026

በአዊበደረሰው የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አደርሰ!

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ አንጓይ ቀበሌ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
በትላንትናው ከቀኑ 7:30 አከባቢ ከባህርዳር ወደ ጃዊ ይጓዝ የነበረ ታርጋ ቁጥር አማ -32365 የሆነ "አባዱላ" የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ በቀሪዎቹ የአካል ጉዳት እንዲሁም በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት አድርሷል።

እናቱ ተገኝታችይህ ህፃን አሁን ከመሸ እንጅባራ 05 ቀበሌ ዉሃ ልማት ጽ/ቤት በሩ አካባቢ ተገኝቷል።     የሚል መልክት በተለጠፈ አጭር ደቂቃ ውስጥ እናቱ መገኘቷ መረጃ ዳርሰናል:: እናመሠ...
07/08/2026

እናቱ ተገኝታች
ይህ ህፃን አሁን ከመሸ እንጅባራ 05 ቀበሌ ዉሃ ልማት ጽ/ቤት በሩ አካባቢ ተገኝቷል።
የሚል መልክት በተለጠፈ አጭር ደቂቃ ውስጥ እናቱ መገኘቷ መረጃ ዳርሰናል:: እናመሠግናለን
Ysefere Genet Lejoch

ይህ ህፃን አሁን ከመሸ እንጅባራ 05 ቀበሌ ዉሃ ልማት ጽ/ቤት በሩ አካባቢ ተገኝቷል።     09879958110960022740በዚህ ስልክ በመደዎል ማግኘት ይችላሉYsefere Genet Lejo...
07/08/2026

ይህ ህፃን አሁን ከመሸ እንጅባራ 05 ቀበሌ ዉሃ ልማት ጽ/ቤት በሩ አካባቢ ተገኝቷል።
0987995811
0960022740
በዚህ ስልክ በመደዎል ማግኘት ይችላሉ
Ysefere Genet Lejoch

የልጅነት ትዝታ እና የዘላለም ወዳጅነት💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙"የልጅነት ጓደኝነት የማይደበዝዝ ወዳጅነት ታሪክ" ⚫ ነገረ አቤዋ ወ ቲና ( Ab & Tina)በኃይሌ አልጋ ተፃፈ ( ሐምሌ 2018 ዓ....
06/08/2026

የልጅነት ትዝታ እና የዘላለም ወዳጅነት
💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙💙
"የልጅነት ጓደኝነት የማይደበዝዝ ወዳጅነት ታሪክ"
⚫ ነገረ አቤዋ ወ ቲና ( Ab & Tina)
በኃይሌ አልጋ ተፃፈ ( ሐምሌ 2018 ዓ.ም)
Haylat Haile
✍️እንጅባራ ብዙ የልጅነት ታሪኮችን በልቧ የያዘች ከተማ ናት። ከእነዚያ ውብ ትዝታዎች መካከል የ Abew Mane የቲና Tensae Simachew ታሪክ አንዱ ነው።ሁለቱም በእንጅባራ ተወልደው ያደጉ፣ የተማሩ፣ የልጅነታቸውን ጊዜያቸውን በጋራ ያሳለፉ አፈር ፈጭተው፣ ውሃ ተራጭተው፣ኮለላና ቻራስታ እንቆቆና እንጆሪ ለቅመው በባሁንክ እና ኮሶበር ትምህርት ቤት አብረው ተምረው ያደጉ Made In Injibara ናቸው :: በአጭሩ 2ቱ ማለት እንደ ጥፍርና ሥጋ የማይነጣጠሉ የልጅነት ጓደኞች... Ab እና ቲና በልጅነታቸው በቤተ ክርስቲያን በመዘምራንነት አገልግለዋል።

✍️ አቤዋ & ቲና በዘጠናዎቹ አጋማሽና በ2ሺዎቹ ዓ.ም. መጀመሪያ፣ በመዘምራን አገልግሎታቸው ወቅት በአምስት የተለያዩ መንፈሳዊ ድራማዎች ላይ ተዋናዮች ሆነው ተሳትፈዋል። እነዚህን ድራማዎች በፈጠራ፣ በጥሩ የካስቲንግ ችሎታና በልዩ የሥነ ጥበብ እይታ ያዘጋጃቸው Coz Blata Nahom (ናሆም ወንድም) ነበር። አቤዋ በአንድ ድራማ መጻጉን፣ በሌላው በርባንን፣ በቀሪዎቹ ደግሞ ሰይጣንን ወክሎ ተጫውቷል። ለእሱ ትወና ሚናን መሸምደድ ብቻ አልነበረም፤ ገፀ ባህሪውን እስኪያሳምን ድረስ ይኖረው ነበር። የእሱን ትወና የተመለከተ ሰው፣ "ሚናውን ተጫውቶ አይደለም፤ ኖሮታል!" ሳይል አይቀርም ነበር።

✍️ በሌላ በኩል ደግሞ ቲና (ትንሳኤ) 3,000 ዲናር ሽቶ ያፈሰሰችውን ማርያም መግደላዊት በሚያስደንቅ ብቃት ተወክሎ ተጫውቷል። ሚናውን በሙሉ እንደተወጣ ያዩት ሁሉ ይመሰክራሉ።እንደ ቀልድ የሚነገረው ግን፣ "ሰባቱ መናፍስት ከድራማው በኋላም እሱን በመውደዳቸውን አብረዉት አሉ አልተዉትም!" የሚለው ነው። 😄

✍️ ናሆም በድርሰት ተዋናይ የመምረጥ ልዩ ተሰጥኦ ነበረው። ተዋናይን ለገፀ ባህሪው የሚመርጠው ስዕል ሰዓሊ ቀለም እንደሚመርጥ በጥንቃቄ ነበር። በእርሱ የተዘጋጁት ድራማዎች በተመልካቾች ልብ ብቻ ሳይሆን፣ በተዋናዮቹም ሕይወት የማይረሱ ትዝታዎችን ተዉ። ዘንድሮ…ዓመታት በፍጥነት አልፈዋል። የልጅነት ጨዋታዎች ወደ ትዝታ፣ የመድረክ ትወናዎች ወደ ታሪክ ተለውጠዋል። ነገር ግን አንድ ነገር አልተቀየረም—የአቤዋና የቲና ጓደኝነት።ዛሬም እንደ ድሮው እርስ በርስ የሚከባበሩ፣ በደስታም ሆነ በፈተና ከጎን የሚቆሙ የረጅም ዓመታት ጓደኞች ናቸው። የልጅነት ሳቃቸው፣ የመድረክ ትዝታቸው እና ያልተቋረጠው ወዳጅነታቸው ዛሬም ሕያው ነው። ድሮ የነበረው መድረክ ተጠናቋል፤ ግን የጓደኝነታቸው ታሪክ እና የልጅነታቸው ትዝታ እስከዛሬ በፈገግታ ይተረካል። እውነተኛ ጓደኝነት በዘመን አይሸነፍም፤ ዓመታት ያልፋሉ፣ ትዝታዎች ይደምቃሉ፣ ወዳጅነት ግን ለዘላለም ይቀጥላል።
ቸር እንሰንብት

05/08/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! ፋሥት መረጃ, Niway Worku, Yechrka Amu, Medi Aneley, Tigest Ephrem, Muluneh Awoke, Muiuye Shibabaw, Mergata Iiuel, Merga Abera Abdisa Jarso, Bini Zigam, Abriham Abaje, Werku Mola, Nahom Alem, Fitsum Yaregal, Endalew Mola, Getnet Bietew, Efrata Te, Abeba Melese, Yemisrach Brte, Sewagegn Ayele, Shegaw Agidew, Abeba Gebeyehu, Tadele Amare, ብርሃነ መስቀል ረዳ, Negeso Bate Negeso Babte

🌱ችግኝ መትከል ፖለቲካ አይደለም! ችግኝ መትከልን ከፖለቲካ ጋር የሚያገናኙ ሰዎች..."?" ናቸው። በነገራችን ላይ ችግኝ ያልተተከለበት ክረምት የለም፤ ባለፉት ዘመነ መንግስታትም በሁሉም ጊዜ...
04/08/2026

🌱ችግኝ መትከል ፖለቲካ አይደለም!
ችግኝ መትከልን ከፖለቲካ ጋር የሚያገናኙ ሰዎች..."?" ናቸው። በነገራችን ላይ ችግኝ ያልተተከለበት ክረምት የለም፤ ባለፉት ዘመነ መንግስታትም በሁሉም ጊዜ ይተከል ነበር። ለአብነትም እኔ "የአማራ ደን መጋዝ" የምለው "የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ" የሚጨፈጭፈው ደን ዝም ብሎ የበቀለ አይደለም። በደርግ መንግስት በአዋጅ የተተከሉ መሆናቸውን የወቅቱ የሰፊው ህዝብ የልማቱ ተሳታፊዎች ይናገራሉ።
​አሁን ግን ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ መናወጥ ሲጀምርና እኛም የገፈቱ ቀማሽ መሆናችን እውን ሲሆን፣ እንደ መንግስት ባለፉት ጥቂት ዓመት "በአንድ ጀንበር..." ንቅናቄ መጀመሩ እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው የሚያኮራና ይበል የሚያስብል ነው። ዳሩ ግን መትከል ብቻውን ግብ አይደለም። በእርግጥ የተዘራው ሁሉ እንደማይበቅለው ሁሉ፣ የተተከለውም ሁሉ ይፀድቃል ማለት አይደለም። መቼም ችግኝ መትከል ካለመትከል ሺህ ጊዜ ይሻላል ባይ ነኝ።
​በሚሊዮኖች ተተክሎ በመቶ ሺዎች መፅደቁ አይቀርምና መትከል ሳይሻል አናቀርም።
በቀጣይም እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ትርፍ፤ በትሪሊዮን ተተክሎ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ትርፍ በቢሊየን ለማፅደቅ ያብቃን!
​ለሀሳቤ መነሻ ደግሞ ከብዙ ፎቶዎች መካከል የዚህን ብላቴና ፎቶ ስመለከት፣ ችግኝ የሚተክል ብቻ ሆኖ አልታየኝም፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ የሚዘራ ትውልድ ጭምር እንጂ። ዛሬ በትንንሽ እጆቹ የተከለው ችግኝ፣ ነገ ለብዙዎች ጥላ፣ ንጹህ አየር እና ሕይወት ይሆናል።
​አንተም እደግ፣ 🌱እነሱም ይደጉ
📸 Admas Union

03/08/2026

With Berihun page – I just made it onto their weekly engagement list by being one of their top engagers!

ባህላዊ ብፌ
02/08/2026

ባህላዊ ብፌ

 #ባህል+
31/07/2026

#ባህል+

Address

Injibara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Berihun page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Berihun page:

Shortcuts

Share