02/12/2025
አዲስ አበባ ባለፈው ሳምንት ሦስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ ኹነቶች አስተናግዳለች፤
ከሕዳር 16- 21 ዓ.ም ባሉት ቀናት ሦስት ታላላቅ ዓለማቀፍ ኹነቶችን አስተናግዳለች ይኽም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የMICE (Meeting, Incentive, Conference, and Exhibition) መዳረሻ መሆኗን ከሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራት አንዱ ነው።
እነዚህም የምስራቅ አፍሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር (EALS) 30ኛው ዓመታዊ ጉባዔና ጠቅላላ ጉባዔ፤ 4ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤቶች ሲምፖዚየም እና 3ኛው የኢጋድ (IGAD) ሚዲያ ሽልማትና ሲምፖዚየም ናቸው።
የአፍሪካ ከፍተኛ ዳኞች፣ የሕገ-መንግስት ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊቃነ መናብርት፣ የህግ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች አዲስ አበባ የከተሙበት ሳምንት እንደመሆኑ ልዑካኑ የአዲስ አበባ የሚገኙ ታሪካዊ እና አዲስ የተገነቡ መስህቦችን ለመጎብኘት ዕድል አግኝተዋል።
ይህ የስብሰባዎች መጠን እና ጥራት እንዲሁም እንግዶች በከተማዋ የመቆየት ፍላጎት አዲስ አበባ ለትላልቅ የዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ያላትን ጠንካራ አቅም ያሳያል።