Health info and vaccancy news

Health info and vaccancy news HIVN media adresses health related news, vacancies and health educational topics
(2)

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ መወሰኑን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀበዚህ ማሻሻያ፦ 1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4760...
18/08/2025

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ መወሰኑን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ

በዚህ ማሻሻያ፦

1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

2. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

3. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።

4. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ ይደረግበታል ተብሏል።

18/08/2025

"ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል"፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

"ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል"፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን*******ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ...
18/08/2025

"ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል"፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
*******

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡

በዚህ ማሻሻያ፦
1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

2. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

3. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።

4. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል፡፡ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል። ይህ የደመወዝ ጭማሪ ካለን የልማት ፍላጎት አንጻር አገልግሎቶችና መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የሚያስፈልገንን ሀብት የሚሻማ ቢሆንም፣ የመንግሥት ሠራተኛውን ኑሮ ማሻሻል ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ የተወሰነ ነው። ከዚህም ባሻገር የመንግሥት ሠራተኛው ችግር በደመወዝ ማሻሻያ ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ በቀጣይ የቤት አቅርቦትን እና የጤና መድን ሽፋንን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሔዎች ይወሰዳሉ፡፡

መንግሥት ይሄንን የደመወዝ ማሻሻያ ሲያደርግ ጭማሪው በቂና የመጨረሻ ነው ብሎ በማመን አይደለም፡፡ በቀጣይነት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማሻሻያው እየተተገበረ ሲሄድ ውጤትን መሠረት ያደረጉ ማሻሻያዎች ይደረጋሉ፡፡ በተጨማሪም የጀመርነው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ይበልጥ ውጤት እያስመዘገበ በሄደ ቁጥር፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የትሩፋቱ ተቋዳሽ ይሆናል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በተገቢ ደረጃና መጠን ለመክፈል ከተፈለገ፣ ያንን የሚሸከም ሀገራዊ ኢኮኖሚ መገንባት አለብን፡፡ ኢትዮጵያ ለአገልጋዮቿ ተገቢውን ክፍያ እንድትከፍል የሚያስችላትን ኢኮኖሚ የመገንባት ኃላፊነት ደግሞ፣ በመንግሥት ሠራተኛው ላይ ጭምር የተጣለ ብሔራዊ ግዴታ ነው፡፡ ካልተከልነው ዛፍ ፍሬ፣ ካልዘራነው ሰብል ምርት ልናገኝ አንችልምና፡፡ ኢኮኖሚያችን ካላደገ፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ሊያድግ አይችልም፡፡ ለአብነት የታክስ ገቢያችንን በአንድ በመቶ ብናሳድግ እንኳን፣ ከ3ዐዐ ቢሊዮን በላይ ተጨማሪ ሀገራዊ ገቢ እናገኛለን፡፡ ይሄንን ለማሳካት ደግሞ በየመስኩ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ፡፡

በአጠቃላይ ዘላቂና ትርጉም ያለው የኑሮ ደረጃ መሻሻል እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዓይናችንን ለአፍታም ቢሆን ከሀገራዊ ሕልማችን ሳንነቅል መረባረብ አለብን። በዚህ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያውያን የሚከፍሉት የውዴታ መሥዋዕትነት አለ፡፡ ይህ መሥዋዕትነት ለነገ ሲባል የሚከፈል መሥዋዕትነት ነው፡፡ ለተሻለ ነገ ስንል የተወሰኑ ፍላጎቶቻችንን እንተዋለን፡፡

ውድ ዕውቀታችንን፣ ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን እንሠዋለን፡፡ ያደጉ ሀገራት ሁሉ የከፍታ ማማ ላይ የደረሱት በአንድ ወቅት መሥዋዕትነት በከፈሉ ትውልዶቻቸው ትከሻ ላይ ነው፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን በነጻነት የምንኖረው፣ ከመኖር ለሚበልጥ ሀገራዊና ሕዝባዊ ክብር ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን በሠው ዐርበኞቻችን ምክንያት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የመንግሥት ሠራተኞች የድካማቸውን ያህል ክፍያ እንደማያገኙ ይታወቃል፡፡ ይሄም ለተሻለች ኢትዮጵያ እየተከፈለ ያለ መሥዋዕትነት እንደሆነ መንግሥት ዕውቅና ይሰጣል። ስለሆነም በዚሁ አጋጣሚ፣ በአነስተኛ ክፍያ ሕዝብና መንግሥት የሰጣቸውን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ለሚገኙ አገልጋዮች መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

በመጨረሻም ሕዝባችንን በንጽሕናና በትጋት በማገልገል፤ ከሚገባንና ከሚጠበቅብን በላይ በመሥራት፤ ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመታገል፤ ከዕቅዶቻችን በላይ በማከናወን፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና እንደምናረጋግጥ መንግሥት ጽኑ እምነት አለው፡፡ የብልጽግና ጉዟችን በቀጠለ መጠን፣ በየምዕራፉ ሁላችንም የብልጽግናን ትሩፋት መቋደሳችን አይቀሬ ነው፡፡ ለዚያ ደግሞ ሁላችንም ወገባችንን አጥብቀንና ታጥቀን መትጋት አለብን፡፡ ይህ ሲሳካ ነጻነታችንን በደማቸው እንዳጎናጸፉን ቀደምት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሁሉ፣ እኛም ሀገራቸውን ለማበልጸግ ዋጋ የከፈሉ ትውልዶች ተብለን ታሪክ ሲዘክረን ይኖራል።

Urgent Vaccancy announcement 12/12/17Required professions:-1. Laboratory technologist       Education: BSC in laboratory...
18/08/2025

Urgent Vaccancy announcement 12/12/17
Required professions:-
1. Laboratory technologist
Education: BSC in laboratory, with COC with a minimum work experience of 6month and above.
Type: Full time
Salary: Negotiation

Work place:
44 Mazoriya, in sheger city oromia on the street of sendafa
NB!!!!
Female applicants, a person living around Tafo area and who can speak Afaan Oromo will get ptiority.

Intersted apllicants can send CV on telegram by the following adress:
0931355338
NB!! Calling is not acceptable just send CV on telegram with all necessary documents

ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች(ዲግሪ) ስያሜ ማስተካከያ ትግበራን ይመለከታል147 የነበሩት ቅድመ ምረቃ የዲግሪ ስያሜዎች ወደ 54 ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል::ትምህርት ሚኒስቴር
17/08/2025

ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች(ዲግሪ) ስያሜ ማስተካከያ ትግበራን ይመለከታል

147 የነበሩት ቅድመ ምረቃ የዲግሪ ስያሜዎች ወደ 54 ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል::

ትምህርት ሚኒስቴር

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ | ቦረና ዩንቨርስቲ ለጤና ባለሙያዎችና ሌሎችም ሙያ መደቦች ያወጣው ለ  #43 ክፍት ስራ መደቦች የወጣ
17/08/2025

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ | ቦረና ዩንቨርስቲ

ለጤና ባለሙያዎችና ሌሎችም ሙያ መደቦች ያወጣው ለ #43 ክፍት ስራ መደቦች የወጣ

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ | አዳማር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ
17/08/2025

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ |
አዳማር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ

ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል። ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2...
17/08/2025

ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።

ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡

ተቀራራብ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።

በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

🦷 ስለ ጥርስ መቦርቦር፡ ማወቅ የሚገባን ነገሮች 🦷የጥርስ መቦርቦር በዓለም ላይ በጣም ከተለመዱ የጤና ችግሮች አንዱ ሲሆን ከህጻናት እስከ አዋቂዎች ድረስ ሁሉንም ሰው ያጠቃል። የጥርስ መቦር...
17/08/2025

🦷 ስለ ጥርስ መቦርቦር፡ ማወቅ የሚገባን ነገሮች 🦷

የጥርስ መቦርቦር በዓለም ላይ በጣም ከተለመዱ የጤና ችግሮች አንዱ ሲሆን ከህጻናት እስከ አዋቂዎች ድረስ ሁሉንም ሰው ያጠቃል።

የጥርስ መቦርቦር ማለት የጥርስን ውጫዊ እና ውስጣዊ ጠንካራ ክፍል (ኢናሜል እና ዴንቲን) በባክቴሪያ አማካኝነት እንዲበሰብስ እና እንዲጎዳ የሚያደርግ ሂደት ነው። ይህ ችግር ካልታከመ ወደ ከፍተኛ ህመም፣ ኢንፌክሽን አልፎ ተርፎም ጥርስን እስከማጣት ሊያደርስ ይችላል።

የጥርስ መቦርቦር መኖሩን ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ፡-

• የጥርስ ቁርጥማት፦ ለቅዝቃዛ፣ ለሞቃት ወይም ለጣፋጭ ነገሮች ጥርስ ሲነካ የሚሰማ ከፍተኛ ስሜት።
• የሚታይ ቀዳዳ ወይም ነጠብጣብ፦ በጥርስ ላይ የሚታይ ጥቁር፣ ቡናማ ወይም ነጭ ቀለም ያለው ነጠብጣብ ወይም ግልጽ የሆነ ቀዳዳ።
• ህመም፦ ምግብ በምንበላበት ጊዜ ወይም ያለምንም ምክንያት የሚሰማ የማያቋርጥ ወይም ድንገተኛ ህመም።
• መጥፎ የአፍ ጠረን፦ የባክቴሪያ መራባትና የምግብ ቅሪት መከማቸት የሚያስከትለው የማይለቅ መጥፎ የአፍ ሽታ።
• በምግብ ወቅት ህመም፦ ጣፋጭ፣ ጎምዛዛ ወይም ጠንካራ ነገር ሲበሉ የሚሰማ ህመም።

🔍የጥርስ መቦርቦር በዋነኝነት የሚከሰተው በሚከተሉት ተያያዥ ምክንያቶች ነው፦
• ፕላክ (Plaque) መፈጠር፦ በአፋችን ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎች ከምግብ ቅሪትና ከምራቅ ጋር ተቀላቅለው ጥርስ ላይ የሚፈጥሩት የሚጣበቅ ቢጫ ሽፋን (ፕላክ) ነው።
• የስኳር እና ካርቦሃይድሬት ፍጆታከፍተኛ መሆን፦ በፕላክ ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎች ስኳርነት ያላቸውን ምግቦችና መጠጦች (ለምሳሌ፡- ለስላሳ፣ ከረሜላ፣ ኬክ) በመመገብ አሲድ ያመነጫሉ።
• የአሲድ ጥቃት፦ ይህ የተመረተው አሲድ የጥርስን ጠንካራ ገለፈት (Enamel) በማጥቃት ማዕድናቱን ያሟሟል።
• የቦርቦር መፈጠር፦ የአሲድ ጥቃቱ ከቀጠለ የጥርስ ገለፈቱ ተበልቶ ቀዳዳ ይፈጠራል። ይህም ቦርቦር ይባላል።

ሌሎች አጋላጭ ሁኔታዎች፦
• የአፍ ንጽህና ጉድለት፦ ጥርስን በአግባቡ አለመቦረሽ እና የጥርስ ክር አለመጠቀም።
• አፍ መድረቅ፦ ምራቅ አሲድን ስለሚያጠፋ እና ምግብን ስለሚያጸዳ፣ የምራቅ እጥረት ለቦርቦር ያጋልጣል።
• በቀን ውስጥ ተደጋጋሚ ምግብ መመገብ፦ በተደጋጋሚ መመገብ ባክቴሪያዎች አሲድ የሚያመርቱበትን ጊዜ ያረዝመዋል።

🧑‍⚕️ የህክምና አማራጮች (Treatment)
ህክምናው እንደ ቦርቦሩ ጥልቀትና ስፋት ይለያያል።

• የጥርስ ሙሌት፦ መቦርቦሩ ገና ሲጀምር የተበላሸውን ክፍል በማጽዳት በልዩ ሙሌት እንዲዘጋ ማድረግ።
• መድሃኒትና ማስታገሻ:- በተለይ መቦርቦሩ ህመም እና እብጠት ካመጣ መድሃኒት ያስፈልገዋል::
• ክራውን (Crown) ወይም ቆብ፦ ቦርቦሩ ሰፊ ሆኖ አብዛኛውን የጥርስ ክፍል ካበላሸው፣ ጥርሱን ሸፍኖ የሚይዝ ቆብ ይደረግለታል።
• የጥርስ ስር ህክምና (Root Canal Therapy)፦ ቦርቦሩ ወደ ጥርስ ስር (ነርቭ) ከደረሰና ከባድ ህመም ካስከተለ፣ የስሩን ነርቭ በማውጣትና በማጽዳት ጥርሱን ማዳን።
• ጥርስን መንቀል (Extraction)፦ ጥርሱ በጣም ተጎድቶ ሊድን በማይችልበት ደረጃ ላይ ሲደርስ የመጨረሻው አማራጭ ነው።

🛡️ መከላከያ መንገዶች
የጥርስ መቦርቦርን ለመከላከል እነዚህን ቀላል መንገዶች መከተል ወሳኝ ነው፦
• ትክክለኛ የጥርስ አቦረራሽ፦ በቀን ሁለት ጊዜ (ጥዋት እና ማታ) በፍሎራይድ የጥርስ ሳሙና ቢያንስ ለሁለት ደቂቃ መቦረሽ።
• የጥርስ ክር መጠቀም (Flossing)፦ በየቀኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ በጥርሶች መካከል የተጣበቁ ምግቦችን በክር ማጽዳት።
• ጤናማ አመጋገብ፦ ስኳር የበዛባቸውን ምግቦችና መጠጦች መቀነስ፤ በአንጻሩ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና የወተት ተዋጽኦዎችን ማዘውተር።
• በቂ ውሃ መጠጣት፦ ውሃ የአፍ ንጽህናን ለመጠበቅና የምግብ ቅሪቶችን ለማስወገድ ይረዳል።
• መደበኛ የጥርስ ምርመራ፦ በየ6 ወሩ ወይም በዓመት አንድ ጊዜ የጥርስ ሀኪም ዘንድ በመሄድ ምርመራና የጥርስ እጥበት ማድረግ ይመከራል።

ማሳሰቢያ:- የጥርስ መቦርቦር የድድና ጉንጭ አካባቢ እብጠት ካመጣ ጥርስ ስር ሕክምናም ሆነ ከመነቀሉ በፊት በመድሃኒት መታከም አለበት:: ይህም የተፈጠረው ኢንፌክሽን በደም እንዳይሰራጭ ያደርጋል:: ስለዚህ ይህ ችግር ሲገጥም ወዲያውኑ ወደህክምና ተቋም መሄድ አለብን::

ይህ መረጃ በቻናላችን Health info and vaccancy news አድሚን ሐኪሞች የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን::

ለማነኛዉም ጥያቄና አስተያየት በአስተያየት መስጫ ሳጥን ወይም ኮሜንት ላይ ያድርሱን::

ጤና ይስጥልኝ ዶ/ር ሙፊድ አብዱ፣ የኦርቶዶንቲክስ የጥርስ ህክምና ስፔሻሊስት በአፔክስ ኢንዲያን የቀዶ ጥገናና የውስጥ ደዌ ህክምና ማዕከል እና የጥርስ ልዩ ክሊኒክ ከነሐሴ 21፣ 2017 ዓ....
17/08/2025

ጤና ይስጥልኝ

ዶ/ር ሙፊድ አብዱ፣ የኦርቶዶንቲክስ የጥርስ ህክምና ስፔሻሊስት

በአፔክስ ኢንዲያን የቀዶ ጥገናና የውስጥ ደዌ ህክምና ማዕከል እና የጥርስ ልዩ ክሊኒክ

ከነሐሴ 21፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
• ለህጻናት፣ ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች የኦርቶዶንቲክ ህክምና
• የጥርስ ብሬስ (ሜታሊክ እና ሴራሚክ) እና በግልጽ የማይታይ የጥርስ ማስተካከያ (ኢንቫሊዛይን)አገልግሎቶች
• የመንጋጋ አቀማመጥ፣ የመንከስ እና የማላመጥ ችግሮች ህክምና
• ለታዳጊ ህጻናት የጥርስ እና የፊት አጥንት ህክምና
• ፈገግታን እና የፊት ሚዛንን የማስተካከል ህክምና
• ዘመናዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም የሚደረግ የላቀ እንክብካቤ
ተመራጭ የሚያረግን
• በኦርቶዶንቲክስ እና ዴንቶፋሻል ኦርቶፔዲክስ የላቀ ልምድ ያላቸው ስፔሻሊስት
• አስተማማኝ፣ ውጤታማ እና ምቹ የህክምና ሂደቶች
• ምቹ እና እንግዳ ተቀባይ የሆነ ቦታ ላይ መገኘታችን
ፈገግታዎን ይለውጡ፣ የጥርስ እና አፍ ጤንነትዎን ይጠብቁ!

ቀጠሮዎን ዛሬውኑ ያስይዙ!
በ +251949001133 +251935101018 +251116680403 ይደውሉልን

አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ሰሚት፣ ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት

የስራ ቅጥር | ዶ/ር ደስታ መካከለኛ ክሊኒክ ብዛት ላላቸው የጤና ባለሙያዎች ያወጣው የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
17/08/2025

የስራ ቅጥር |
ዶ/ር ደስታ መካከለኛ ክሊኒክ
ብዛት ላላቸው የጤና ባለሙያዎች ያወጣው የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ |  የጂንካ አጠቃላይ ሆሲፒታል   #ጠቅላላ ሀኪም (GP)  ለመቅጠር ይፈልጋል ስለሆንም ከዚህ በላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት እንደትመዘገቡ ታጋብዛችኋዋል ።
17/08/2025

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ | የጂንካ አጠቃላይ ሆሲፒታል

#ጠቅላላ ሀኪም (GP) ለመቅጠር ይፈልጋል
ስለሆንም ከዚህ በላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት እንደትመዘገቡ ታጋብዛችኋዋል ።

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
0000

Telephone

+251912389356

Website

https://bit.ly/3UUq6al

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health info and vaccancy news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Health info and vaccancy news:

Share