02/08/2022
የሙስጠፌ አግቸር የሰብዓዊ ጉዳዮች አማካሪ አህመድ እስማኢል ይባላል፡፡ ሙስጠፌ ከሌሎቹ አማካሪዎቹ ይበልጥ ይህኛውን ያቀርበዋል፤ ይሰማዋል፡፡ ወንድምየው ዳሮድ እስማኢል ይባላል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመት የበለጸገና ሚልዮነር የሆነ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው ከሙስጠፌ አግቸር ታላቅ ወንድም ጋር በመሆን የክልሉን ኮንትራቶችን የተቆጣጠረ ሰው ነው፡፡ እነዝህ ሁለት ወንድሞች ሌላ ሶስተኛ ወንድም አላቸው አብድኑር ይባላል፡፡ በክልሉ ውሃ ቢሮ የሎጅስትክስ ኃላፊ ነው፡፡
የነዝህ ሶስት ልጆች አባት እስማኢል ሀሩን (ሁሴን) ዋናው የአል ሸባብ የደህንነት ኃላፊ ነው፡፡ ይህ ሰው በአል ሸባብ አመራሮች ዘንድ ከፍተኛ ተዓማኒነት ያለው በመሆኑ የአል ሸባብ ዋና ከተማ የሆነችውን ጅልብ የደህነቱን መዋቅር ይመራል (ፎቶውን ታች ይመልከቱ)፡፡ በአሁኑ በኢትዮጵያ ላይ የተካሄደው ጦርነትም የደህንነት መረጃዎችን በማቅረብ በበላይነት እየተከታተለ ያለ የአል ሸባብ ሁነኛ ሰው ነው፡፡
እነዝህ ልጆች ከአባታቸው ጋር ቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ የአባታቸውንም ክፉ ስራ አንድም ቀን ስቃወሙትና ስኮንኑት አልታዩም፡፡ እንደሚነገረው ልጆቹ ለአባታቸው ቅርብ ረጂና ደጋፊ ናቸው፡፡ የሙስጠፌ ደግሞ ቅርብ ሰዎች፤ የሚተማመንባቸው፡፡
ስለዝህ አል ሸባብ ኢትዮጵያን ስያጠቃ የነዝህ ልጆች አስተዋጽኦ ምን ነበር? ሙስጠፌ የነዝህን ልጆችና አባት ግንኙነት ያውቅ ነበርን?
የክልሉ ጸጥታ አካላት እንድሁም ረጆ ሚድያ ያነጋገረቻቸው የክልሉ ባለስልጣናት ሙስጠፌ አግቸር ስለ ልጆቹ ግንኙነት በሚገባ ያውቅ እንደነበረ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ይበልጥ የሚያሳዝነው የክልሉ ልዩ ፖሊስ ኃይሎች በገፍ እንድገደሉ ሆነ ተብሎ የተሸረበ ሴራ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ በዝህ ጦርነት ቢያንስ 500 እስከ 600 የሶማሊ ክልል ኃይሎች ተሰውተዋል፡፡ ለዝህ ደግሞ ተጠያቂ የተደረገ አንድም ሰው የለም፡፡ ይታያችሁ በአንድ ቦታ (አቶ) ሁለት ጊዜ ጥቃት ተደርጎ ብዙ ሰው አልቆብናል፡፡ አል ሸባብ (አል ቁሻሽ) አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ ዘልቀው ገብተው እየተደራጁ ነው፡፡ ይህ አደባባይ የሞቀው እውነታ ሆኖ ሳለ ሙስጠፌ አግቸር አሁንም “ደመሰስናቸው” እያለ በውሸት ሰዉን ለማደንዘዝ ይፈልጋል፡፡ ለምን ቢባል እውነታው ከተገለጸ ሙስጠፌ ለአል ሸባብ ወደ ኢትዮጵያ መግባት የተጫወተው ሚና ይጋለጥበታል!!!