
12/11/2024
ዜናKM+
ሕዳር 03 2017 ዓ.ም
በሶማሊ ክልል ለ2017 በጀት አመት የልማታዊ ሴፍትኔት PSNP የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር ፀደቀ
*********************
በሶማሊ ክልል ለ2017 በጀት አመት የልማታዊ ሴፍትኔት (PSNP) የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር ፀድቋል።
የሶማሊ ክልል የልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) አብይ ኮሚቴ ስብሰባ በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።
በሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ሰብሳቢነት የተካሄደው የልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) አብይ ኮሚቴ ስብሰባ የፕሮጀክቱን የእቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት አመት እቅድ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩ ላይ አብይ ኮሚቴው በክልል ለ2017 በጀት አመት ለልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) የስራ ማስፈፀሚ 14 ነጥብ 5 ቢሊዬን ብር አፅድቋል።
በሶማሊ ክልል ሁሉም ወረዳዎች ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የልማታዊ ሴፍትኔት ( PSNP) የህብረተሰቡን ህይወት በማሻሻል በኩል የጎላ ጠቀሜታ እንደሚያበረክት ተገልጿል።