23/11/2025
▫️የሰንበት ቁርስ !
በምን ዉስጥ እያለፍክ እንደሆነ ይገባኛል ፤ ነገሮች ከቁጥጥርህ ዉጪ ሆኑብህ ? በህይወትህ ያልጠበቅካቸዉ ያላሰብካቸዉ ነገሮች ተከስተዉ ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብህ መረዳት አቃተህ ?
አንድ ነገር አስታዉስ
ዝናቡን ማስቆም አትችልም : ዣንጥላ መያዝ ግን ትችላለህ ፤ የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም : መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ።
እዚህ ጋር አንድ የ ’ማርቲን ሉተርን’ አባባል ልጨምርልህ
ከቻልክ ሩጥ ፣ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ ፣ መራመድ ካልቻልክ ዳዴም በል ብቻ ወደፊት መጓዝህን ቀጥል !
መልካም ሰንበት 🙏