
13/05/2024
የኮንታ ዞን መንግስት ከቀርጫንሼ ኃ/የተ/የግል ማህበር ጋር ከ197 ሚሊዮን 528 ሺ ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድ ስራ ማሽነሪ ግዢ የውል ስምምነት ተፈራረመ።
የመንገድ ስራ ማሽነሪዎች ግዢ ስምምነቱን የኮንታ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ኃላፊ አቶ አግደው አሰፋ ከቀርጫርሼ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ም/ል ስራ አስኪያጅ ከሆኑት ከአቶ አቡበከር ይማም ጋር ተፈራርመዋል::
በፍርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንታ ዞን ም/ል አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የዞኑን ህዝብ የመንገድ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የግንባታ ማሽኔሪዎችን በራስ አቅም ገዝቶ መጠቀም ተገቢ መሆኑን በመግለፅ ለተግባሩ ስኬት ርብርብ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
አያይዘውም አቅራቢው ድርጅት ማሽነሪዎችን በወቅቱ እንደሚያቀርብም እምነታቸውን ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ ረዳት የመንግስት ተጠሪና በብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ የዘማናት የህዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የዞኑ መንግስት ከፍተኛ በጀት በመበጀት ማሽነሪ ፍላጎትን ለማሟላት ያደረገው ጥረት የሚደነቅና ለሌሎች አካባቢዎችም ምርጥ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።