10/07/2025
ታላቅ የምስራች!
| ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪካዊ ምዕራፍ ተቀዳጀ፡ የመጀመሪያው የአንጎል ዕጢ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ አከናወነ!
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታላቅ ስኬት በማስመዝገቡ ኩራት ይሰማዋል፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የአንጎል ዕጢ ቀዶ ህክምና በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል! ይህ ታሪካዊ ክስተት ለማህበረሰባችን የምንሰጠው ልዩ የህክምና አገልግሎት ትልቅ መሻሻል ማሳያ ነው።
ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ቁርጠኛ ሰራተኞች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ለመስራት ያላችሁ የማያወላውል ቁርጠኝነት በእውነትም ህይወትን እየለወጠ ነው። በሆስፒታላችን አገልግሎት እምነት ላሳዩን ታካሚ እና ቤተሰቦቻቸው ከልብ እናመሰግናለን።
በዚህ ታሪካዊ ቀዶ ህክምና የተሳተፉት ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው፦
ዶ/ር ተመስገን ወልዴ-የአንጎል እና የህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት
ዶ/ር አክበረት ለሜሳ (የቀዶ-ህክምና ረዚደንት)
የአንስቲዚያ ቡድን: ሙሁዲን፣ ታምሩ፣ አባይነሽ፣ መሀመድ
የነርሲንግ ቡድን: ብርሀኑ፣ነጋ፣ነፃነት፣ብርቱካን
Congratulations!!!
Historic Milestone at Wolkite University Comprehensive Specialized Hospital: First Brain Tumor Surgery!
Wolkite University Specialized Hospital is proud to announce a monumental achievement: the successful performance of it’s first-ever brain tumor surgery! This landmark event represents a significant advancement in delivering specialized medical care to our community.
We extend our deepest commendation to the entire dedicated staff of Wolkite University Hospital. Your unwavering commitment to excellence is truly transforming lives. Our sincere gratitude also goes to the patient and their family for placing their trust in our services.
Key participants in this groundbreaking surgery included:
Neurosurgeon: Dr. Temesgen Wolde
Assistant: Dr. Akberet Lemesa (GSR-3)
Anesthesia: Muhudin,Tamiru, Tajir, Cherinet, Abaynesh, Mohammed
Nursing team : Birhanu, Nega, Netsant, Birtukan