
08/09/2022
አዲስ ተመራጩ የኬንያ ፕሬዚዳንት ለበዓለ ሲመታቸዉ ኢትዮጵያን ጋበዙ
አዲስ ተመራጩ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የፊታችን ማክሰኞ መዲና ናይሮቢ ላይ በሚካሄደዉ በዓለ ሲመት ላይ የኬንያ 5ኛው ፕሬዝዳንት በመሆን መንበረ ሥልጣኑን ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ይረከባሉ።
ዊሊያም ሩቶ ማክሰኞ መስከረም 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደዉ በዓለ ሲመ ት ላይ ከ40 በላይ የሃገራት መንግሥታት እና የመንግሥታት ተጠሪዎችን መጋበዛቸዉን የኬንያዉ ዴሊኔሽን ዘግቧል። በሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙት መካከል፤ የኢትዮጵያ፤ ግብጽ፤ ዩጋንዳ፤ ናይጀሪያ፤ ጋና እና፤ የደቡብ አፍሪቃ መሪዎች ይገኙበታል።
ከዚህ በተጨማሪም የአውሮጳ ህብረት፣ የአፍሪቃ ህብረት እና መንግሥታዊ የልማት ጉዳይ ባለሥልጣናት ተወካዮች በሥነ-ስርዓቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወቅታዊ ሀገሪዊ እና አለማቀፋዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇👇
Telegram channel :-https://t.me/wollomedianet