
23/08/2025
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የራያ ሴቶች በአሸንዳ በአል ላይ እጃቸውን በማጣመር ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገለፀ፡፡ የአሸንዳ በአል በተለያዩ አካባቢዎች በደመቀ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በደቡባዊ ትግራይ ግን ለየት ያለ ይዘት እንደነበረው ትግራይ ሄራልድ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው በመሆኒና ሌሎችም የደቡባዊ ትግራይ ዞን ከተሞች ላይ ልጅ አገረዶች ከጨዋታና ጭፈራ በተጨማሪ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ሴቶቹ ‹‹አትግደሉን፣ አታፍኑን፣ አታሸብሩን›› የሚሉ ድምፆችን ማሰማታቸውንና እጃቸውን ከፍ አድርገው በማጣመር ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን ዘግቧል፡፡ አንዲት የመሆኒ ነዋሪ የሆነች ሴት ለትግራይ ሄራልድ ስትናገር ‹‹የዘንድሮው አሸንዳ አዲስ ልብስ አድርገን የምንጨፍርበት በአል ብቻ ሳይሆን የታሰርንበት ሰንሰለት እንዲበጠስ ጥያቄ ያቀረብንበት ነው፡፡
የህወሀት የጦር አዛዦች እያደረሱብን ያለው ጥቃት እንዲቆም ድምፃችንን አሰምተናል›› ብላለች፡፡ በደቡባዊ ትግራይ ዞን የህወሀት ከኮር በላይ የሆኑ ወታደራዊ አመራሮች በዘረጉት ኔትወርክ ነዋሪው እንደሚገደል፣ እንደሚታፈንና ፆታዊ ጥቃት እንደሚደርስበት ዘገባው አውስቷል፡፡
#ዘገባው የ ዘሀበሻ ነው